Connect with us

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ አንድ ጥናት ጠቆመ

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ አንድ ጥናት ጠቆመ
Photo: Social media

ጤና

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ አንድ ጥናት ጠቆመ

በአፍሪካ የኮቪድ 19 ክትባትን ለመውሰድ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ አንድ ጥናት ጠቆመ

– ወጥ የሆነ የክትባት አቅርቦት እና የክትባት ግብአተቶች ክፍተት እንዳለ  ጥናቱ ጨምሮ ጠቅሷል,

parternship for evidence based responce for covid 19 (PERC)የተባለ ተቋም በ9ሀገራት ላይ ባደረገው ጥናት የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በሆኑ 9 ሀገራት ላይ ያተኮረ ሲሆን  78 በመቶ የሚሆኑት በጥናቱ ከተካተቱት ለክትባቱ ፍላጎት አሳይተዋል ነው ያለው፡፡

ሆኖም እስከ ህዳር 2021 ባለው መረጃ 7 በመቶ የሚሆኑት ብቻ በአፍሪካ አህጉር ክትባቱን ወስደዋል ::

በጥናቱ ከታየው በመነሳትም የፍላጎት እና የአቅርቦት ከፍተኛ ልዩነት እንዳለ እና በአፍሪካ ወጥነት ያለው የክትባት አቅርቦትን መፍጠር እና  የክትባት ፕሮግራሞችን መደገፍ እንደሚገባም ነው የተጠቆመው፡፡

PERC በሪፖርቱ እንዳለውም ፍትሀዊ ያልሆነ የክትባት ስርጭት አፍሪካን እንደአህጉር በቂ ክትባት እንዳታገኝ አድርጓል፡፡

ጥናቱ ጨምሮም የኮቪድ 19 ክትባትን የመውሰድ አስፈላጊነት እንዳለ ሆኖ በሽታውን ለመከላከል የሚያግዙ የማስክ አጠቃቀም እና ርቀትን መጠበቅ አሁንም ተግባራዊ መሆን አለባቸው ብሏል፡፡

የአፍሪካ የበሽታ መከላከል  እና መቆጣጠር ዳይሬክተር ዶ/ር  ጆን ኒኬንጋሶንግ  እንዳሉት  ጥራቱን የጠበቀ እና ውጤታማ ክትባትን በማቅረብ እንዲሁም ፍትሀዊ  የክትባትን አጠቃቀም በመፍጠር በፍላጎት እና   አቅርቦት ላይ ያለውን ክፍተት መሙላት ይገባል ፡፡

በጥናቱ ተካተተው ከነበሩ 5 ሀገራት ጊኒ፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ ፣ቱኒዚያ እና ዙንባቢዌ 90  በመቶ በላይ የክትባት ፍላጎት ታይቷል፡፡የክትባት አቀባበል ፍላጎት ደግሞ መንግስታትን ለበሽታው የሚሰጡትን ምላሽ ከማመን እና በሽታው አደጋ ይጥልብኛል ከሚል የግል እምነት የመነጩ ናቸው ነው የተባለው፡፡

በጥናቱ ከመላሾቹ 20 በመቶ በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ ያላቸው ለበሽታው ብዙ አደጋ አያደርስም በሚል አመለካከት ሲሆን  24 በመቶ ከመቶ ስለክትባቱ በቂ መረጃ የሌላቸው 17 በመቶ በመንግስታቸው ላይ እምነት ማጣት ከመላሾች የተገኙ ናቸው ፡፡

ታማኝ በሆኑ የመረጃ ምንጮች መረጃዎችን በመስጠት እንዲሁም በበቂ ሁኔታ እና ወጥነት ባለው መልኩ ክትባቱን በማቅረብ ለክትባቱ ያለው ፍላጎት እንዲጨምር ማድረግ ይቻላል ሲል መረጃው ምክረሀሳቡን አስቀምጧል፡፡

በጥናቱ ክትባትን በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ አስቸጋሪ ሁኔታዎች መካከል ወጥ የሆነ እና በቂ የክትባት አቅርቦት አለመኖር እና ሰዎች ለክትባት ርቀት ቦታ መሄዳቸው መሆኑም ተቀምጧል፡፡

በጥናቱ ከተለዩ ችግሮች ባሻገር በአፍሪካ የክትባት ፕሮግራሞችን በወጥነት መደገፍ የኮቪድ መከላከያ መንገዶችን አጠናክሮ መቀጠል አለምአቀፍ መንግስታት እና ሀገራት በበቂ ሁኔታ ለጤና በጀት መመደብ እንዳለባቸው በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡

 

Click to comment

More in ጤና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top