Connect with us

አውሮፓ ሕብረት-አውሮፓ ጥፋት፤ በሰው አህጉር ድርቅ ብሎ ሀገር የማመስ ደንቆሮ ዲፕሎማሲ!

Social media

ነፃ ሃሳብ

አውሮፓ ሕብረት-አውሮፓ ጥፋት፤ በሰው አህጉር ድርቅ ብሎ ሀገር የማመስ ደንቆሮ ዲፕሎማሲ!

አውሮፓ ሕብረት-አውሮፓ ጥፋት፤
በሰው አህጉር ድርቅ ብሎ ሀገር የማመስ ደንቆሮ ዲፕሎማሲ!

(ስናፍቅሽ አዲስ~ ድሬቲዩብ)
አውሮጳ ባይኖር የዓለም ሰላም እንዴት ሸጋ ይሆን ነበር፤ ዘርፎ መበልጸግን እንደ ክብር የሚቆጥር አህጉርና ህዝብ ነው፡፡ አፍሪካ ላይ የፈጸሙት በደል በኗቀቸው ግን ከእነሱ በተሻሉ አፍሪካውያን ይቅርታና ምህረት ተረስቶ እንጂ ሰው እኩል መሆኑን ያላጤኑ አፈ ቀላጤዎች እኮ ናቸው፡፡

ሁሉ አህጉር በሌላ ሀገር ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ በማያውቅበት የዓለም ታሪክ ስልጣኔያቸው ሁሉ አስሶ መውረር፣ ወርሮ መዝረፍ የሆነ፣ ከማጋዝና ከመንጠቅ ከፍ ያለ ጥበብ የሌላቸው አውሮፓውያን አይናቸውን በጨው አጥበው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ይሆናሉ፡፡

አውሮፓውያን እጃቸው ንጹህ የሆነበት የአፍሪካ ትርምስ መች ኖሮ ያውቃል፡፡ ለስግብግብ ሆዳቸው በሚያሴሩት ተንኮል ሚሊዮኖች ይሞታሉ፣ ብዙ ሚሊዮኖች ይሰደዳሉ፡፡ መላው እጃችን ላይ እያለ የሚያጣሉም የሚያስታርቁም እነሱ ናቸው፡፡ ነውራቸውን ሳይቀር ሸፍነን ስንኖር እነሱ ስልጡን እኛ ኋላ ቀር ተብለን እንታያለን፡፡

በኢትዮጵያ እያደረጉ ያሉት ለእኛ እንግዳ አይደለም፤ ውል አዛብቶ ሊረግጥ ለፈለገ አምባገነን ቀለማችን ብሎ ጎኑ የቆሙ ከቀለማቸው ርቀው ለማሰብ እድል ፈንታ የሌላቸው ናቸው፡፡ ባህላችንን እሴታችንን ክብራችንን ካልበረዙ ክብር የሌላቸው የሚመስላቸው ናቸው፡፡

በዓለም ታሪክ ጠረጴዛ ከበው ሀገር ለመካፈል እጣ የመጣጣል ታሪክ ካላቸው የግዛት ተኩላዎች ፍትህ አንጠብቅም፡፡ እነሱ የፈጸሙት ለመናዘዝ ዘለዓለም ቢሰበሰቡ ጊዜ የደቂቃ ያህል የሚያጥርባቸው ሆነው የእኛን የውስጥ ችግር ለማተራመስ ግን በሳምንት አስር ቀን ጉባኤ ካልገባን ብለዋል፡፡

ይህ የሰብአዊ መብት ጥሰት ጉዳይ ካልመከረ ያሉት የዛሬ ስብሰባ ተጋልጠው ተዋርደውበታል፡፡ ግን ውርደት ምሳቸው ነው፡፡ እነሱ ከሞተ ሳይሆን ከገደለ ወገን ቆመው የሚጮሁት ገዳይነት ጸጋቸው ስለሆነ ነው፡፡

እኛ ክንደ ብርቱ ብቻ ሳይሆን በፈጣሪ የምንታመን ህዝቦች ነን፡፡ ድሆች ብንሆንም ዘርፈን መበልጸግ ክብር ነው አንልም፡፡ አውሮፓ ህብረት ከጥፋታች ጎን ቆሟል፡፡ አውሮፓ ጥፋት ሆኖብን ስቃያችን እንዲበዛ እና መከራችንን እንድናይ እያሴረብን ነው፡፡

ይሄ በጎረቤት ሀገር ጉዳይ የተገባ ጣልቃ ገብነት አይደለም፤ ሩቅ መጥተው አህጉር ተሻግረው ስህተትም ነውርም እየፈጸሙ ያለበት የዲፕሎማሲ ድንቁርና ነው፡፡ ከጎናችን ስለቆሙት ሀገራት ክብር አለን፡፡

አውሮፓ ህብረት ሊያጠፋን ሲባዝን እኛ ግን ከአፍሪካ ጋር ልንለማ ቱርክ ዘልቀናል፡፡ ድል ለእውነትና እውነተኞች፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top