Connect with us

የባለድል ሀገር ልጆች ነን

የባለድል ሀገር ልጆች ነን
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የባለድል ሀገር ልጆች ነን

የባለድል ሀገር ልጆች ነን

(ሚካኤል አለማየሁ ~የእናኑ ልጅ)

ኢትዮጵያ በየትውልዱ ህይወቱን አካሉን ንብረቱን ዕወቀቱን ጉልበቱን ባጠቃላይ ያለውን ሁሉ ሰቶ ነፃነቷን የሚጠብቅ ልጅ አላት። እኛ ወድቀን ሀገር የምናቆም ነን።

የኢትዮጵያ ዋስትና በልጆቿ ውስጥ ያለው የአርበኝነት ስሜት መሆኑ ተርጋግጧል። በህብረት ቢያሴሩም ባንድም ቢያሰልፉ የሚሸነፍ የኢትዮጵያዊነት መንፈስ የለም የሚያሸንፍ እንጂ። ፈተናውን ያከብደዋል እንጂ ኢትዮጵያውያንን ማሸነፍ አይደለም በእውን በህልም አይሞከርም። እኛ የባለድል ሀገር ልጆች ነን።

ከሽንፈታቸው የማይማሩት ባንዳ እና የውጭ ጠላቶቿ እንዲያው ይቀጥላሉ ኢትዮጵያም እያሸነፈች ትቀጥላለች። መቼም ለሽንፈት የፃፈው ምን ይሆናል ያው ውርደቱን ነው የሚቀበለው።

እኛ ኢትዮጵያውያን ከበርሊን የተነሳውን የቅኝ ግዛት ማዕበል ድል የነሳን የጥቁር ፈርጦች ነን። ለዚህ አድዋ ትመስክር። እኛ እኮ በበቀል የመጣን ፋሽስት ጣሊያንን ከግብር አበሮቹ እንግሊዝ እና ፈረሳይን ጋር ሽንፈት  ያከናነብን ነን። የመንግስታቱን ህብረት አድሎ በማይጨው ላይ የረታን ጀግኖች ነን። አሜሪካም ጁቡቲም የይምሰል ምክንያት ደርድረው ለሱማሌው ጦርነት አቅም ቢያሳጡንም ኢትዮጵያ ወይም ሞት ብለን ተነስተን የካራማራ ባለድል የሆንን ነን። በኤርትራ ላይ የተቀናጀነው ድላችን ጠላት ሆኖ ለመጣብን ሁሉ ክንዳችን ድል እንጂ ሽንፈተ እንደማያቅ ያረጋገጥንበት ነው። እኛ ያሁን ትውልድ የዚህች የባለድል ሀገር ልጆች ነን።

ጠላትና ባንዳ ከሽንፈትና ከታሪክ መማር ካልቻለ እንግዲህ ምን እናረጋለን እኛ በአዳዲስ ድሎች ታሪክ እየሰራን እንቀጥላለን። እነሱም አዳዲስ ሽንፈቶች እየተመዘገበባቸው ይቀጥላሉ። ኢትዮጵያ በአሸናፊነት ትቀጥላለች።

ኢትዮጵያ

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top