Connect with us

አንተ ምን አደረክ ?

አንተ ምን አደረክ ?
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አንተ ምን አደረክ ?

አንተ ምን አደረክ ?

(ዮሐንስ መኮንን)

የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ የአማራ ሚሊሺያ፣ ፋኖ፣ የአፋር ልዩ ኃይል እና የአፋር ሚሊሺያዎች ኢትዮጵያን ከፊቷ ተደቅኖ ከነበረው ጥልቅ ጉድጎድ አፋፍ ለማትረፍ የከፈሉትን የሕይወት እና የአካል መስዋእትነት በወጉ ተረድተኸው ቢሆን ኖሮ እንኳንስ አቃቂር ልታወጣላቸው ልታመሠግናቸው ቃላት ያጥሩህ ነበር።

የኢትዮጵያ ኃይሎች መስዋእትነትን በዩቲዩብ እና በፌስቡክ ብጥስጣሽ ዘገባዎች ፈጽሞ ልትረዳው አትችልም። ግንባር ድረስ ዘልቀህ ለሀገር ሉዓላዊነት፤ ለወገን ክብር በየአንዳንዷ ሰከንድ በነፍሳቸው እና በአካላቸው ተወራርደው በእሳት መካከል እየተወረወሩ ከባንዳ ሠራዊት ጋር አንገት ለአንገት ተናንቀው ሲወድቁ ለማየት ዕድሉ ገጥሞህ ቢሆን ኖሮ ምስጋናህን በብርዕ ቀለም ሳይሆን በእንባህ ትጽፈው ነበር።

ይኽንን ሁሉ ዋጋ እየከፈሉ ያሉት የኢትዮጵያ ኃይሎች የላመ የጣመ ሳይበሉ፤ የሞቀ እና የደመቀ ሳይለብሱ፤ ደረቅ ኮቾሮ ቆርጥመው በብርድ እና በቁር ተቆራምደው ሀገር እያቆሙ መሆኑን በአካል ግንባር ተገኝተህ ለማየት ዕድል ገጥሞህ ቢሆን ኖሮ አንተም ከእነርሱ እኩል “ኢትዮጵያዊ ዜጋ” ተብለህ መጠራት ራሱ ያሳፍርህ ነበር።

ከቻልክ በግንባር ከኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር አንገት ለአንገት እየተናነቁ ላሉት የኢትዮጵያ ኃይሎች ለእግራቸው ካልሲ፣ ለእጃቸው ጓንት፣ ለአንገታቸው ፎጣ፣ ለቁስላቸው መድኃኒት አሰባስበህ ይዘህ ግንባር ድረስ ሂድ ወይንም ላክላቸው። ለክብርህ እና ለሉዓላዊነትህ ሲፋለሙ የቆሰሉትን ሆስፒታል ሄደህ ጎብኛቸው፣ አግዛቸው፤ አጽናናቸው።

አሁን ጥያቄው ግልጽ ነው!  ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን የህልውና አደጋ ለመቀልበስ ዜጎች በሚችሉት ሁሉ እየተረባረቡ ነው።  አንተስ ምን እያደረግህ ነው? ምን ኃላፊነት ወሰድክ? ምን አዋጣህ?

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top