Connect with us

ቁስሌ በሻረና ጦርነቱ ሳያልቅ ደግሜ በገባሁ ከሚል ሀገር ወዳድ ሠራዊት ጋር በደብረ ብርሃን!!

ቁስሌ በሻረና ጦርነቱ ሳያልቅ ደግሜ በገባሁ ከሚል ሀገር ወዳድ ሠራዊት ጋር በደብረ ብርሃን!!
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ቁስሌ በሻረና ጦርነቱ ሳያልቅ ደግሜ በገባሁ ከሚል ሀገር ወዳድ ሠራዊት ጋር በደብረ ብርሃን!!

ቁስሌ በሻረና ጦርነቱ ሳያልቅ ደግሜ በገባሁ ከሚል ሀገር ወዳድ ሠራዊት ጋር በደብረ ብርሃን!!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)

ወደ ሰሜን ሸዋ አቀናን፡፡ ሰብሰብ ብለን የሀገር መከላከያ ሠራዊቱን እንዴት ነህ ለማለት ነው፡፡ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ደርሰን ወደ ቅጥሩ ገባን፡፡

እዚህ የእኔን ቁስል የቆሰሉ፣ የእኔን ጉዳት የተጎዱ ወገኖቼ አሉ፡፡ የሀገር ልጅ ሲመለከቱ ዳግም ቁጭታቸው የሚግል፡፡ ዳግም ለሀገር መታገልን መርህ ያደረጉ፡፡

ጓደኞቼ ደጀን እንሁን ብለው መከሩ፡፡ ጥሪ አቅርበው ኑ አለን እንበል አሉ፡፡ አለሁ ያለ፣ ያለውን ሰጠና ያንን ይዘን እዚህ ደረሰን፡፡ በቅጥር ግቢው ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚሆኑ ብርድ ልብሶችን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶችን አስረከብን፡፡

አንዳንዶቹ የገባችባቸውን ጥይት ለማስወጣት ቀዶ ጥገና ቀናቸውን ይጠብቃሉ፡፡ ወረፋው እስኪደርሳቸው ቸኩለዋል፡፡ በማግስቱ ግንባር መድረስ ናፍቀዋል፡፡ ለሀገር መሞት ክብር እንደሆነ እየነገሩን ነው፡፡ 

የሠራዊቱ ተወካዮች አመሰገኑ፡፡ ደጀን አለን፤ እናንተ ከጎናችን ስለሆናችሁ እኛ ከፊት ብንጋፈጥ ክብር ነው ሲሉ ልባችንን አሞቁት፡፡ እዚህም እዚያም ተበታትነው ያገኘኋቸው የመከላከያ ሠራዊት አባላት ቀላል ጉዳት ገጥሟቸው እንደ ልብ እየተንቀሳቀሱ ህክምናቸውን የሚከታተሉ ናቸው፡፡ ብዙዎች ጦርነቱ ከማለቁ በፊት እናት ሀገርን በመታደጉ ዘመቻ ዳግም መፋለምን መርጠዋል፡፡ ያን ቀን ናፍቀዋል፡፡

ሀገራቸው እንደምታሸንፍ እምነታቸው ልባቸው ውስጥ ነው፡፡ በሙሉ ልብ የድል ብሥራት ዜናን ናፍቀው ሬዲዮን ይዘው የሚሽከረከሩ አይቻለሁ፡፡ 

አሁንም ግን ደጀን አለሁ ማለት ያለበት ጉዳይ እንዳለ ታዝቤያለሁ፡፡ በተለይ ብርድልብስ በጣም ያስፈልጋል፡፡ ደብረ ብርሃን ብርድ ናት፤ እዚያ ላይ ቁስል ሲኖር ስሜቱ እንዳይከብድ ስለ እኛ ለቆሰሉት አሁንም አለሁ ማለት ደግነት ሳይሆን ብድር መመለስ ነው፡፡ ሁሉም የቻለውን ማድረግ አለበት፡፡ ይሄንን እናደርግ ዘንድ ያገዙንን እናመሰግናለን፡፡

ደብረ ብርሃን ግርግር ነው፤ ብዙ ሰው አለ፡፡ በትህነግ ወረራ ከያለበት ወደ ደጋማዋ መዲና የገባው ሰው ብዙ ነው፡፡ እዚህ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡና በትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች አሉ፡፡ እዚህ ቤታቸው ናፍቋቸው በሰሞኑ የድል ዜና ልባቸው ሞቆ ቀዬያቸአውን ዳግም የናፈቁ አሉ፡፡ ሁሉም መልካም ይሆናል፡፡

ቀሪ ጉዞው ወደ ሸዋሮቢት ነው፡፡ 

የድል ብሥራት ዜናው ተናፍቋል፡፡ እያንዳንዷ ምሽት አንድ ሰበር ዜና እንደ ራት ይዛ ብቅ ትላለች፡፡ ዛሬ ምሽት የሚሰማውን ለማድመጥ የጓጓ የሀገሬ ሰው እያየሁ ወደ ፊት ጉዞአችን ቀጠለ፡፡

ገና እነግራችኋለሁ፤ የራሳን ጀግንነት ትሰማላችሁ፤ የፋኖን ጀብድ ታደምጣላችሁ፤ የጠላትን ክፋት ምን ድረስ እንደሆነ አሳያችኋለሁ፡፡ የመከላከያ ሠራዊት የአማራና አፋር ልዩ ሃይሎች፣ ፋኖና ሚኒሺያ የሰሩትን ጀብዱ፣ በአንድ አውደ ውጊያ ሆነው ያስገኙትን የድል ውጤት ከጉዞዬ ጋር ታጣጥሙታላችሁ፡፡ ግንባር ላይ የሚዋጉት በመካከላቸው ልዩነት የሌለ እነሱ የኢትዮጵያ ህዝባዊ ሠራዊት ናቸው፡፡ ኢትዮጵያን ለድል አብቅተዋታል፡፡ ድሉ ይቀጥላል፤ መንገዱም….

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top