Connect with us

የህወሓት ኘላን ቢ ?!

የባለድል ሀገር ልጆች ነን
እሱባለው ካሳ

ነፃ ሃሳብ

የህወሓት ኘላን ቢ ?!

የህወሓት ኘላን ቢ ?!

(እሱባለው ካሳ)

የህወሓት ወራሪ ሰራዊት በጥምር ሀይሉ አከርካሪውን ከተመታ በኋላ ያው “ተሸንፈናል” ላለማለት “ያፈገፈግነው ለስትራቴጂ ነው” የሚል ጭዌ ውስጥ ገብቷል። ህወሓቶች ገና ወሎን ሲይዙ “ጦርነቱ አልቋል፣ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው” እያሉ ላልተጠየቁት ድርድር መልስ ሲሰጡ እንደፊኛ ልባቸውን ወጥረው ነበር። 

ይህ  የተወጠረ ልባቸው በሰሞኑ የጥምር ሀይሉ መብረቃዊ ምት ተንፍሷል። በሀፍረት አንገታቸውን የደፉት በአውሮፓና በአሜሪካ የሚገኙ አባልና ደጋፊዎቻቸው ብቻ ሳይሆኑ የቡድኑ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ጭምር ነው። በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ በየሚድያው እየወጣ “አዲስአበባን ልንጨብጥ ነው” እያለ ይቀደድ የነበረው ግለሰብ ወራሪው ሽንፈቱን ተከናንቦ መፈርጠጥ ከጀመረ በኋላ ራሱን ከሚድያ ሰውሯል።

አንዳንዶች ፈርጣጩ ህወሓት ወደመቀለ ተመልሶ መሰባሰብ መጀመሩን ክፉኛ ይፈሩታል። ምናልባት አፈር ልሶ ሊነሳ ይችላል የሚል ግምት እና ስጋትም አላቸው። በእርግጥ ወራሪው ትንፋሽ ካገኘ የተራረፈውን ሀይል ሰብስቦ በቀጣይ እዝህም እዚያም የሽብር ጥቃት ሊፈፅም የሚችልበት አቅም ያጣል ብሎ መገመት አይቻልም። 

ህወሓት ይህን እድል ሊያገኝ የሚችለው ግን ሁለት ነገሮች ከተፈፀሙ ብቻ ይሆናል። የመጀመሪያው  የጥምር ሀይሉ ወደትግራይ አልገባም ብሎ፣ ወራሪውን እንደሰርገኛ ሸኝቶ ትግራይ ድንበር ላይ ከተቀመጠ ወይንም ህወሓቶች “ከማን ጋር ነው ለድርድር የምንቀመጠው፣ ጦርነቱ አልቋል” የሚለውን ትእቢት ምንተእፍረታቸውን አስቀምጠው በስመ ድርድር ጊዜ መግዛት የሚችሉበት አንዳች ተዐምራዊ ዕድል ለማግኘት ጥረው ከተሳካላቸው ብቻ ነው።

በግሌ ግን በጠ/ሚ እና የጦር ሀይሎች ጠ/አዛዥ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የሚመራው ጥምር ሀይሉ ለእነዚህ ፀረ ሰላም ሀይሎች በየትኛውም መልኩ ትንፋሽ ማግኛ እድል ይሰጣል ብዬ አላስብም።  የወገን ጥምር ሀይል ህወሓት ስጋት በማይሆንበት መልክ የመቅበር ህዝባዊ አደራ ተጥሎበታል። እናም ግስጋሴው ይህን ወራሪ ሀይል ዳግም አፈር ልሶ በማይነሳበት ሁኔታ መትቶ አርቆ መቅበር ይሆናል። እናም ወራሪው ህወሓቶች በእጃቸው  የየያዙት ኘላን ቢ ሆነ ኘላን ሲ ሊፈፅሙ  የሚችሉት  ሲኦል ወርደው  ይሆናል ማለት ነው።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top