Connect with us

አንተ የምትመጻደቀው ማን ነህ?

Social media

ነፃ ሃሳብ

አንተ የምትመጻደቀው ማን ነህ?

አንተ የምትመጻደቀው ማን ነህ?
(ኦሀድ ቤንአሚ)

ተመልካች የለም፤ ግን ለካሜራው እንንጠባረር፤
48 ከመቶ መሬትህን አስረክበህ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችን አስጨርሰህ፤ የማታሸንፈው ጦርነት ከፍተህ፤ ሕዝብ ተፍቶህ ኦባሳንጆ ደርሶልህ፤ ወጣቶችህ በየቦታው እየረገፉ ድልን የምትመኝ የትግራይ ታጋይ ሆይ አሁንም ቆም ብሎ ማስተዋል አይሻልም፤ ኢትዮጵያውያን ቆርጠዋል፤

አንተ የህወሓት አድናቂ ተከታይ ሆይ፤ ራሱ በከፈተው ጦርነት ረመጥ ውስጥ ከትቶ ለውድቀት የዳረገህን የማይሆን ድልን እያለምክ ሞትን የምትናፍቅ ሆይ አይበቃህም ወይ?

ደብረጺዮን ትግራይ ላይ ሆኖ ያዘመታቸው ወታደሮች ሰላማዊ ዜጎችን እየረሸኑና ሴቶችን እየደፈሩ አገር እያስመረሩ ነው፤ የሕዝብ ቁጣ ገንፍሎ ህወሓትን መቅበር የሚፈልገው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥርና ቁርጠኛነት በየቀኑ እየጨመረ እየሄደ እንዲህ አይነቱ መንጠባረር ምን ይሉታል? የካሜራ ሌንስ አጋጣሚ ወይስ የሕዝብ ንቀት?

25 ጊዜ ሚሌን ለመስበር ሞክረህ እየተሰበርክ የበረሃ ፀሓይ ስጥ ሆነህ የቀረህ እንዲህ አይነቱን መንጠባረር ምን ይሉታል?

የማይ ካድራ ምስኪኖች ደም ለፍትህ አየጮኽብህ፣ የአፋር ህጻናት ነፍሶች ለፍርድ እየተጣራ መንጠባረር ምን ይሉታል?

አብሮ መኖርና ወገንን በፍቅር መማረክ አቅቶህ የትላንት ወገንን ጠላት አድርገህ ነጻነት እያሉ መመጻደቅና መንጠባረር ምን ይሉታል?

በውድቀት አፋፍ ላይ ሆነህ አገርን ይዤ ካልወደቅኩ እያልክ እያቅራራህ ሕዝብ በእብደትህና በእብሪትህ እያዘነብህ መንጠባረርህን ምን ይሉታል?

አገርን ለእኩይ ምዕራባውያን ፍላጎት እየሸጥክ፣ ለነሱ አጀንዳ እየተዋጋህ ክልልህን እየቀበርክ፣ የወጣቶቿን ህይወት ለሞት እየቸበቸብክ አንተ የምትመጻደቀው ማን ነህ?

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top