Connect with us

ምረጥ ወገን የቅኝ አዙር ባርነት ወይም ነጻነት ?!

ዛሬና ትናንት የብዙ ሰዎችና የመገናኛ ብዙሃን ትኩረት የሳበ ጉዳይ በመሆኑ የግል ምልከታዩ እነሆ:-
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ምረጥ ወገን የቅኝ አዙር ባርነት ወይም ነጻነት ?!

ምረጥ ወገን የቅኝ አዙር ባርነት ወይም ነጻነት ?!

(ሙሼ ሰሙ)

ከ1884 እስከ 1914 የዘለቁት የአውሮፓ ቅኝ ገዢዎች “ፓርቲሽን ኦፍ አፍሪካ” ብለው በሰየሙት ወረራ አማካኝነት አፍሪካ ውስጥ የፕሮቴክቶሬት፣ የቅኝ ግዛትና በነጻ መሸቀጫና ሸቀጥ ማራገፊያ ምድር መስርተው ነበር፡፡ ዓላማቸውም በአስራ ዘጠነኛው ከፍለ ዘመን የባርያ ንግድ መዳከም ያስከተለባቸውን የኢኮኖሚ ድቀት ለማካካስ ሲሆን በተለይ ደግሞ ብሔራዊ ጥቅማችን በማለት ከባርያ ፈንጋይነት ወደ ቅኝገዥነት የተሸጋገሩበት ዘመን ነበር።

አውሮፓውያን ፒፓቸውን እያጨሱና እየተንጎራደዱ ጠረጴዛቸው ላይ በዘረጉት ካርታ አፍሪካን በምናብቸው ተቀራምተዋል፡፡ እጅግ ኃላ ቀር የነበረውን አፍሪካዊ እጀግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ጨፍጭፈው፣ የአፍሪካውያን ጉልበት በመበዝበዝና የተፈጥሮ ሃብታቸውን በማሟጠጥ፤ ዛሬ ላይ የሚመኩበትን  የበለጸገ” ኢኮኖሚ በጥቁሮች ደምና ላብ ገንብተዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ “ከእናንተ ነፍስ የኛ ነፍስ” ይበልጣል በሚል መርሃቸው መሰረት ለኢኮኖሚ የበላይነታቸውን ዘምተውብናል፡፡  

መቶ ሰላሳ ዓመት ካስቆጠረ አሳፋሪ ታሪካቸው በኃላ አውሮፓውያንና አሜሪካውያን፣ እራሷን በራሷ የዓለም ፖሊስ አድርጋ በሾመችው አሜሪካ ጋሻ ጃግሬነት እየተመሩ “ኃላ ቀርና ደካሞች” ያሉንን “ጥቁሮች” ማሰልጠን፣ ማብቃት፣ ማልማትና ዴሞክራታይዝ ለማድረግ በሚል ሽፋን፣ የብሔራዊ ጥቅማችን ስጋትና አጋሮችን እየለዩ መንግስታትን በማፍረስ፣ ሕዝቦችን እየከፋፈሉና እርስ በርስ እያዋጉ በተለይ ነጭ (caucassian) ለሆኑ ዝርያዎቻቸው የተመቻቸ ምድር ለመፍጠር ብዙ ሀገሮችን አፍርሰዋል፡፡ ዛሬ ደግሞ የጥቁር ሕዝቦች ተምሳሊት የሆነቸው ኢትዮጵያ ተረኛ ገፈት ቀማሽ ሆናለች፡፡

እንደሚታወቀው አሜሪካውያን አውሮፓውያን ሴክቴሪያኒዝምን (ኢራቅ፣ ሲሪያ) በባልካናይዜሽንን (አርሜንያና አዘርባጃን) ግብ አድርገው ሕዝብን እርስ በርስ በማባላትና መንግስታትን በመገልበጥ አሻንጉሊት መንግስታትን ማስቀመጥ ችለዋል፡፡ ኢትዮጵያ ላይም ለ27 ዓመት ያገለገላቸው ስርዓት መወገድ ስላልተመቻቸው አዲስ ታዛዥ መንግስት ለማንገስ ቆርጠው እንደተሱ ተረድተናል። በሌላው ሀገር ላይ እንደለመዱትም የጥብቆ መንግስት ለመመስረት የሚረዳቸውን “የኮንፌዴሬሽንና የፌደራሊስት ፓርቲ” አቀናጅተውና አደራጅተው አዲስ አባባ ከዛሬ ነገ ይፈርሳል በሚል ምኞት ለሃጫቸውን እያዝረበረቡና ቀን እየቆጠሩ ይገኛሉ፡፡

እቅዳቸው ድብልቅ (Hybrid) ዘመቻ ነው። በመጀመርያ በመገናኛ ብዙን አማካኝነት የተቀናጀ ስም ማጥፋት በሀገራችን ላይ በመክፈት ቀጥሎ የጦር ሜዳ ነባራዊ ሁኔታውን ለመለወጥ የሚያስችል የጦር ሜዳ መረጃ በማቀበልና በጦር መሳርያ እርዳታ በመታገዝ የሀገራችንን ቅርጽ፣ ይዘት፣ ታሪክ፣ ባህል፣ ስነልቦናና፣ ጂኦ ፓለቲካዊ ሉሉዕላዊነታችን መለወጥ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ሕወሃትና ሽኔና መሰል ጋሻ ጃግሬዎቻቸው መሳርያ ለመሆን ችለዋል። ይህ ስለማይበቃም መዳረሻ ስብስብም መስርተዋል።

ወገን አዲስ የተቋቋመው የፌዝ ድርጅት አላማው ይህው ነው።

ስብስቡ መስራች ጉባኤውን ያደረገው በመገናኛ ብዙሃን የጉዳዩ ባለቤቶች ኢትዮያውያን ሳይጋበዙ ብሔራዊ ጥቅማችን ተነካብን ያሉ አሜሪካውያንና ኤጀንቶቻቸው በተገኙበት በድብቅ ነው፡፡ የስብስቡ ስምም የወደፊት ግብሩን ፍንትው አደርጎ በሚገልጽ መልኩ የተቀመረና የአሜሪካን ናሽናል ኢንተረስት በሚያስጠብቅ መልኩ ኢትዮጵያን በኮንፌዴሬሽን ለመከፋፋል ያቀደ እንደሆነም ከወዲሁ ያወጀ ነው፡፡

ወገን በቅድም አያቶችህ፣ በአባቶቻችን በእናቶቻችን ተጋድሎ በታሪክ ምዕራፍ የተመዘገበችው ሀገራችንን፤ ለአሜሪካን ብሔራዊ ጥቅም ስጋት ስለሆነች ከነክብሯ እንዳትኖር ተፈርዶባታል ፡፡ ከዚህ በኃላ ጦርነቱን በማያሻማ መንገድ ከማሸነፍ ውጭ ድርድርና ውይይት ይዘው የሚመጡት የተሻለ የሰላም አማራጭ አለመኖሩንም ግልጽ አድርገውልናል።

ለንግግር በር ብንከፍትም እንኳን አዲስ “ኮንፌዴሬትድና የተበጣጠሰች” ኢትዮጵያን ማዋለድ እንጂ ሎዕላዊ ኢትዮጵያ እንደማትኖር አስገንዝበውናል። በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ከባርነት ያልተናነሰ የእጅ አዙር ቅኝ አገዛዝና ነጻነትን መምረጥ ጠረጴዛ ላይ ቀርቧል። ምረጥ ወገን የቅኝ አዙር ባርነት ወይም ነጻነት ???!!!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top