Connect with us

ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!!

"ጠላት በመረጠው የውጊያ ስልት ከፍተኛ ኪሳራ እያስተናገደ ይገኛል" የመከላከያ ሕዝብ ግንኙነት
መከላከያ ሚኒስቴር

ዜና

ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!!

ከሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ!!

“አሸባሪው ህወሀት የጀመረውን ማጥቃት ፤ በማያዳግም ሁኔታ እንቀለብሳለን ! “

ህወሀት በሰሜን እዝ ሠራዊታችን ላይ ወረራ ( ጭፍጨፋ ) ከፈጸመ በኋላ መንግስት በወሰደው ህግን የማስከበር ዘመቻ የጠላት አከርካሪ ተሰብሮ ጁንታው ተደምስሶና የተረፈው ተበትኖ ዋሻ ገብቷል ፡፡ መንግስት ለ8 ወር ትግራይን የማረጋጋትና የመልሶ ግንባታ ስራ እየሰራ ነበር ፡፡ TPLF ግን ከተበተነበት እየተሰበሰበ በክልሉ ውስጥ ቀውስ የማባባስ ስራ እየሰራ ጎን ለጎን ደግሞ መንግስትን እና መከላከያን እየከሰሰ ቆይቷል ፡፡ የሰብዓዊ ቀውስ እንዳይባባስ ፤ ቀጣይ አመት የምግብ እጥረት እንዳይከሰት ለአርሶ አደሩ የእርሻ እድል ለመስጠት የተናጠል ተኩስ አቁም ውሳኔ በመወሰን ሰራዊታችን ከትግራይ እንዲወጣ ተደርጓል ፡፡

በአጠቃላይ ለክልሉ የጥሞና ጊዜ በመስጠት ህዝቡ የሚሻለውን አስቦ እንዲወስን እድል ለመክፈት ሲባል መንግስት ተኩስ በማቆም ሀላፊነት የተሞላው ውሳኔ ወስኖ እንደነበር ይታወቃል ፡፡

አሸባሪው ህወሀት ግን ተመሳሳይ እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ የመከላከያ ሰራዊታችንን ተከታትሎ በማጥቃት ግጭቱን ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በማስፋፋት በትግራይ እንዳይደርስ የተፈለገውን ቀውስ ወደ ሁለቱ ክልሎች  አስፋፍቶታል ፡፡

ግጭቱን ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች በማስፋፋት የህዝብ መሰረተ-ልማቶችን እያፈረሰ ወስዷል ፡፡ መውሰድ ያልቻለውን አውድሟል ፡፡ ንጹሀን ዜጎችን ገድሏል ፡፡ የአርሶ አደሩን እና የአርብቶ አደሩን ቤት አቃጥሏል ፤ ከብቶቻቸውን የሚበላውን በልቶ ቀሪውን ገድሏል ፤ እጸዋቶችን አጥፍቷል ፤ አዝዕርቶችን አጭዶ ወስዷል  ፡፡

ጁንታው “የጅቡቲን መስመር ለመቁረጥና ወልቃይት ጠገዴን በማጥቃት በሱዳን በኩል ኮሪደር ለማስከፈት” የሚል ዓላማ ይዞ ተደጋጋሚ እና መጠነ ሰፊ ማጥቃት ፈጽሟል ፡፡ “በሁለት ሳምንት አዲስ አበባ ለመግባት” በሚል በሰሜን ወሎ በኩል ሰፊ ማጥቃት ስያከናውን ከርሟል ፡፡ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን ይህንን ሀገር የማፍረስ የጁንታ እቅድ እንዲመክን አድርጓል ፡፡ እጅግ ከባድ ኪሳራም አድርሶበታል ፡፡

ከሦስት ቀን በፊት በራሳቸው አንደበት ሌ/ጀ ጻድቃን የተባለው የጁንታው አባል ፤ ” …ጦርነቱን እናሳጥረዋለን ፤ በሁለት ሳምንት አዲስ አበባ እንገባለን ፤ ፖለቲካዊ ፣ ወታደራዊና ዲፕሎማሲያዊ ሁኔታን እንቀይራለን …” በሚል ባወጀው ጦርነት በሁሉም ግንባሮች ውጊያ ከፍቶ ይገኛል ፡፡ ራሳቸውም በለኮሱት ውጊያ በጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን እና ሌሎች የፀጥታ ሀይሎች ጥምረት እየተቀጠቀጠ ይገኛል ፡፡

ያጁንታው መሪ ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል ከሦስት ቀን በፊት የሌ/ጀ ጻድቃንን መግለጫ በማጠናከር “…ኢትዮጵያውያንን እንደ አባቶቻቸው በመቅበር ሰላማችንን እናረጋግጣለን…” የሚል ዕቅድ እንዳላቸው በሚዲያ ገልጸው እቅዳቸውን ተግባራዊ ለማድረግ በሁሉም ግንባር ከሰኞ ጀምሮ ውጊያ ከፍተዋል ፡፡ በጀመሩት ውጊያ አይቀጡ ቅጣት እየደረሰባቸው ይገኛል ፡፡

የመከላከያ ሠራዊታችን የጁንታውን ጥቃት የመመከት ውጊያ እያካሄደ የጠላትን ወራሪ ሀይል መመከት ብቻ ሳይሆን እየደመሰሰ የኢትዮጵያን ደህንነት እና ህልውና የማስከበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ በጠላት ላይ ከባድ ኪሳራ እያደረሰና ሽንፈት እያከናነበው ይገኛል ፡፡ ይህንንም ገድል አጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡

ኢትዮጵያ በልጆቿ መስዋዕትነት ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች ፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top