Connect with us

ሱሌማን አብደላና የቲዊተር ዲፕሎማሲ “Twiplomacy”

ሱሌማን አብደላና የቲዊተር ዲፕሎማሲ "Twiplomacy"
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሱሌማን አብደላና የቲዊተር ዲፕሎማሲ “Twiplomacy”

ሱሌማን አብደላና የቲዊተር ዲፕሎማሲ “Twiplomacy”

(ሱልጣን አባጊሳ)

የ 21ኛው ክፍለ-ዘመን ዲፕሎማሲ “Twiplomacy” ወይም ” Hashtag Diplomacy” ወይም  የቲዊተር ዲፕሎማሲ የቲዊተርንያ ቴክኖሎጂን እንደመሳሪያ በመጠቀም የዲፕሎማሲ ስራን መስራት እንደማለት ነው፣ በአሁኑ ወቅት በዓለም ላይ ከ Conventional  ወይም የግንባር ለግንባር ዲፕሎማሲ ባለተናነሰ መልኩ የዓለም የዲፕሎማሲ አቅጣጫ የቀየረ የዲፕሎማሲ ዘርፍ ነው። 

በጣም አዋጭ፣ እነ ባራክ ኦባማ ለምርጫ ቅስቀሳ፣ እነ ዶናልድ ትራምፕ ተፅኖ የፈጠሩበት፣ እነ ዳግማዊ ጆን ፖል ለምዕመኖቻቸው መልዕክት የሚያስተላልፊበት፣ እነ ዘዊኬንድ አልበሞቻቸውን የሚያስተዋወቁበት፣ ከጆ ባይደን እስከ ጀስቲን ትሪዶ፣ ከ ማክሮን እስከ መርክል፣ ከ አብዱል ፍታህ አልሲሲ እስከ ጠ/ሚኒስትር አብይ ፣ ከኡሁሩ ኬንያታ እስከ ፖልካጋሚ ፣ከውሮፓ እስከ አሜሪካ ፣ ከአፍሪካ እስከ ኤዢያ የመንግስት ተቌማት፣ የሀገር መሪዎች፣ ሚኒስትሮች በተቌማቸውና በግላቸው ይጠቀሙበታል፣ የቲዊተር ዲፕሎማሲ!

በኛ ሀገር የቲዊተር ዲፕሎማሲ አጭር እድሜ ነው፣ አንዳንድ ተቌማትና ግለሰቦች ቀድመው ጀምረውታል፣ ነገር ግን በሀገራችን ቲዊተርን በመጠቀም  በዓለም ላይ ተፅኖ መፍጠር የተጀመረው ባልፉት አምስት ወራት ነው፣ በሀገር ወዳድ ዜጎች በራስ ተነሳሽነት የሀገራቸውን ጥቅም ለማስጠበቅ ስሉ ጀምረውታል፣ ከነዚህ ተፅኖ ፈጣሪ የቲዊተር ሰራዊት ቁንጮ መካከል ሱሌማን አብደላ አንዱ ነው።

የሱሌማን አብደላ የቲዊተር ገፅ በአውኑ ወቅት በሀገራችን የቲዊተር ታሪክ ከክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቲዊተር ገፅ ቀጥሎ ተፅኖ ፈጣሪ ነው።

ሱሌማን አብደላ የማይደክም፣ የማይሰለች፣ ድፕሎማት ያልሆነ ድፕሎማት ነው፣  ሚዲያ ሞኒተር ያደርጋል፣ ከዕድሜው በላይ ለሀገር ሀሳቢ፣ የአገራችን የዲጂታል ዲፕሎማሲ ላይ Paradigm Shift ያመጣ ወጣት ነው።

በቲዊተር መልዕክት ፖስት ስታደረግ ተፅኖ ፈጥሯል ከተባለ ሱሌማን አብደላን የሚወዳደር ባለፉት 4-5 ወራት ተወዳዳሪ አልተገኘለትም፣ የሱ መልዕክቶች ሚሊዮኖች ጋር ይደርሳል።

በአንድ ፖስት ከ 15k በላይ ሪቲዊትና ሼር የሱሌማን አብደላ መታወቂያ ነው። ለዚህም በዲጂታል ዲፕሎማሲ በአሁኑ ውቅት ሱሌማን ኢብደላ ተፅኖ ፈጣሪ ነው።

እድሜና ጤና ይስጥህ!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top