Connect with us

እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ ከተቆፈረበት በተአምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር፡፡

አሚኮ

ነፃ ሃሳብ

እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ ከተቆፈረበት በተአምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር፡፡

እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ ከተቆፈረበት በተአምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር፡፡
የምንመካበትን አላወቁም-ግሸን ደብረ ከርቤ!!

(ሄኖክ ስዩም ~ድሬ ቲዩብ)
የእነሱ ዘርዐ-ሠራዊቶች ኃይል ያድነናል ብለው ለሠራዊታቸው ያላቸውን ሲሰፍሩ እኛ ግን የሚያድነን ከክንዳችን ይልቅ እውነትና እምነት ነው የሚሉት ነገሥታቶቻችን ሩቅ አስበው ነበር፡፡

እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ ከተቆፈረበት በተአምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር፡፡ ለዚህ ነው የምንመካበትን ስለማያውቁ በጉልበታቸው በመመካት በየዘመናቱ ሊደቁሱን ከሚጎዳን ነገር ጎን የቆሙት፡፡
ግን ልዩነታችን ሩቅ ነው፡፡ ግዙፍ የጦር መሳሪያዎችን ለማምረት አንቀድም ይሆናል፤ ታሪክ ለጸሎት ጥሪ /አዛን/ መቅደማችንን ግን ቀድሞ ነግሮልናል፡፡ ያ ጥሪ ዛሬም ዋጋ አለው፤ ዛሬም ይሰማል፡፡

ዛሬ ግሸን ማርያም ናት፡፡ እነሱ ባህር ላይ ከጠመዷቸው ዓለምን ያጠፋል ያሉት ግዙፍ መሳሪያ በላይ እኛ ከዓለም ጥፋት እንድንባታለን ብለን የምናምናት፤ እንደ ጽዮን፣ እንደ ተድባበ ማርያም እንደ ብዙ ቅዱሳት መካናት፤

መቼም ግሸንን ረግጦ የወሎን ልብ ሳያገኝ የመጣ የለም፡፡ የወሎ ደግ ልብ አንድም ከሀገሬ ሰው ጋር የተገናኘው ግሸን ብሎ የሄደ የሚያየውን እያየ ነው፡፡ አርሂቡ ነው ወሎ፡፡ ወሎ ዛሬ የሆነውን እናውቃለን፡፡ ግን ደግሞ ወሎ ነው፡፡ እንግዳ ይመጣል ብሎ ዛሬም ለግሸን ሰው ተፍ ተፍ ይላል፡፡
የሄዱ ሰዎች ወሎን ሲረግጡ የሆነውን ደውለው ነገሩኝ ምንኛ የታደለ ልብ ነው፡፡ በዚህ አበሳ ውስጥ ሰው ይመጣብኛል ብሎ ለሰው መሆንና ለሰው መዘጋጀት፡፡

የአምባሰል ተራሮች ዛሬም የእንግዳ ነጭ ልብስ በስስት ናፍቋቸው የሰነበቱ ናቸው፡፡ ደሴና ኮምቦልቻ የታል እንግዳችን ሲሉ ከርመዋል፡፡ እንዲህ ያለ ልብን የሰጣቸው ፈጣሪ ይመስገን፡፡

ግሸን ደብረ ከርቤ እንዴት ባለ ሁኔታ ከርሞ እንግዳውን የሚቀበል ደግ ሰው ምድር ያረፈች እንደሆነች አይተናል፡፡
የሚመጣው ዘመን መከራ ገደል ገብቶ ደስታ አደባባይ የሚቆምበት ይሁን፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top