Connect with us

ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን፤ ለሰላም እድል እንስጥ?!

Social media

ነፃ ሃሳብ

ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን፤ ለሰላም እድል እንስጥ?!

ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን፤ ለሰላም እድል እንስጥ?!
(ያሬድ ኃ/ማርያም)

ለሰላም እድል መስጠት አይከፉም። ደምሳሽም፣ ተደምሳሽም እኛው ነን። የእርስ በርስ ጦርነት ክፉቱ፤ ሀዘኑ ከቤት አይወጣም። “… ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ” እንደሚባለው ነው ዛሬ ኢትዮጵያ የገጠማት ፈተና።

ስለ ሰላም ሲወራ ደሙ የሚንተከተክ ብዙ ሰው እንዳለ አውቃለሁ። አንዳንዶችም የሰላሙ ነገር ህውሃትን ለማዳን የተመረጠ መንገድ አድርገው ያስቡታል። ይሄ ጦርነት በህውሃት መደምሰስ ብቻ ይጠናቀቃል ከሚል እሳቤ የመነጨ ይመስለኛል። በእኔ እይታ ጦርነቱ በድምሰሳ ይጠናቀቃል ብዬ አላምንም። ያ ጊዜ ያለፈ ይመስለኛል። ህውሃት ከአቧራነት ተመልሳ ትግራይን እንድትቆጣጠር ከተደረገ ወዲህ ነገሮች ተገለባብጠዋል። ህውሃት የትግራይ ወጣቶች እና እጻናት ቢያልቁ ግድ እንደማይሰጠው አሳይቷል።

ጦርነቱ ለተራዘመ ጊዜ መቀጠሉ ደግሞ እስካሁን ካለቀው በላይ በአሥር ሺዎች የሚቆጠር የሰው ህይወት እናጣለን። በአገሪቱ ኢኮኖሚም ላይ እስካሁን ከደረሰው ጉዳት እጅግ የከፋ ጉዳት ይደርሳል። ቢዘገይም አሁንም ለሰላም እድል መስጠት እና የአገር ሉዐላዊነትን በማይነካ እና ተጠያቂነትንም ባረጋገጠ መልኩ ለውይይት እድል መስጠት የአሸናፊነት ምልክት ነው ብዬ አስባለሁ።

ዞሮ ዞሮ በግራም፣ በቀኝም ሟችም ገዳይም፣ ደምሳሽም ተደምሳሽም እኛው ነን።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top