Connect with us

‹‹ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርገን መታገል አለብን›› የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

‹‹ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርገን መታገል አለብን›› የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር
(አሚኮ)

ዜና

‹‹ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርገን መታገል አለብን›› የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

‹‹ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርገን መታገል አለብን›› የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አገኘሁ ተሻገር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን ያሰማራው ቡድን ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እየደረሰበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አሸባሪው የትህነግ ቡድን በአማራና በአፋር ክልሎች ወረራ ከፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ የአማራ ክልል መንግሥት የክተት ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ከሰሞኑ ደግሞ የፌዴራል መንግሥት ሕዝቡ በተደራጀ አግባብ እንዲመክት ጥሪ አቅርቧል፡፡

የአማራ ክልልና መላው የኢትዮያ ሕዝብ ጥሪውን በመቀበል የሰጠው ምላሽ የሚደነቅ መሆኑን ርእሰ መሥተዳድሩ ተናግረዋል፡፡ በግፍ የተከፈተው ጦርነት በኢትዮጵያ ሕልውና ላይ ያንዣበበ መሆኑን በመገንዘብ ልዩ ልዩ ድጋፍ እያደረጉ ነው ብለዋል፡፡

በጦርነቱ በቀጥታ በመሳተፍ፣ ለጦርነቱ ደጀን በመሆን፣ በመምራት፣ በማስተባበር፣ በመደገፍና በማገዝ ሁሉም በባለቤትነት ላደረገው ርብርብ ምስጋና አቅርበዋል፤ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሸባሪው ትህነግ በአማራና በአፋር ክልሎች ላይ ከፈጸመው ግልጽ ወረራ በስተጀርባ ሌሎች ኀይሎች እንዳሉ ርእሰ መሥተዳድሩ አንስተዋል፡፡ ወራውን ለመቀልበስ የሚደረገው ትግል እንደተጠበቀ ሆኖ ጠላት በሰሜን ወሎ፣ በደቡብ ጎንደር እና በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች ሰርጎ መግባቱን ገልጸዋል፡፡ በጦርነቱም በርካታ የቡድኑ አባላት የተዋጊነት፣ ዝርፊያ የመፈጸምና ሕዝብ የመበደል ስምሪት ተሰጥቷቸዋል ነው ያሉት፡፡

የትግራይ ሕዝብ ኢትዮጵያዊነቱን ጠብቆ የሚኖር መሆኑን ጠቅሰዋል፤ ለአማራ ሕዝብም ወንድም ሕዝብ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም አሸባሪው ትህነግ የትግራይ ተወላጆችን ከኢትዮጵያ ሕዝብ ለመነጠል የሐሰት ወሬ እየነዛ ይገኛል ብለዋል፡፡ በጦርነቱ ግን በርካታ አርሶ አደሮችና ወጣቶች ተገድደውም ቢሆን መሰለፋቸውን ነው ርእሰ መሥተዳድሩ የገለጹት፡፡ 

ጉዳዩ የነጻነት ትግል አይደለም፤ የትግራይን ሕዝብ ከጥቃት ለመከላከልም አይደለም ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ በሕዝብ ላይ ቀጥታ ወረራ መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊረዳ ይገባል ብለዋል፡፡ ዓላማውም የአማራ ሕዝብን አንገት ማስደፋት እና ኢትዮጵያን ማፈራረስ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም የትኛውንም አማራጭ እየተጠቀመ ነው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያን ለማፍረስ አሸባሪው ትህነግ  ከሸኔ ጋር ጋብቻ መፈጸሙን ጠቅሰዋል፤ የሁለቱ ግንኙነት ከበፊቱም ተደብቆ የነበረ አጀንዳ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡ አሸባሪው ትህነግ ከሕዝብ ጋር ጸብ የለኝም በሚል ሕዝቡን ለማታለል ቢሞክርም ጦርነቱ በተከፈተባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ከግማሽ ሚሊዮን ያላነሰ ሕዝብ ተፈናቅሏል፡፡ ከፍተኛ ዝርፊያም ተፈጽሟል፡፡ ቅርስም መዘረፉን አንስተዋል፡፡ የተዘረፈውም ወደ ትግራይ እየተጫነ ነው ብለዋል፡፡ 

በከተሞች የቤት ጣሪያ ሳይቀር ተነቅሎ እየተወሰደ ነው፣ የግለሰብ ቤቶች እየተዘረፉ ነው፣ ጤና ተቋማት፣ የሕዝብ መገልገያ መሰረተ ልማቶች እየወደሙ ነው፡፡ ሕጻናትና ሴቶችን ጨምሮ ሰዎች በዘግናኝ ሁኔታ በግፍ እየተገደሉ ነው ብለዋል፡፡ እናቶች፣ ታዳጊዎች እየተደፈሩ እንደሆነም ጠቅሰዋል፡፡ ሕዝቡም ይህንን አውቆ እየታገለ ነው ተብሏል፡፡ በዚህ ረገድ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚያስቀምጡት የተፈናቃይ ቁጥር እውነታውን ያልዋጀ እንደሆነም አስገንዝበዋል፡፡ በመሆኑም ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርተው ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠይቀዋል፡፡

አቶ አገኘሁ እንዳሉት የወገን ኀይል በሁሉም አካባቢዎች እየመከተ በጠላት ላይ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ እያደረሰ ነው፡፡ መከላከያ ሠራዊት፣ የአማራ ልዩ ኀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ከሕዝቡ ጋር በመሆን እየተፋለመ ይገኛል ብለዋል፡፡ ወጣቶችም እየተፋለሙ እንደሆነ ነው የተናገሩት፡፡

አርሶ አደሮችም በቡድን እና በተናጠል ዋጋውን እየሰጡት ነው ብለዋል፡፡ አየር ኀይሉ ከፍተኛ ጀብድ እየፈጸመ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም አሸባሪው ቡድን ያሰማራቸው አካላት የጥይት ማብረጃ ሆነዋል፤ ውጊያ በሚደረግባቸው አካባቢዎችም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጠላት ኀይል እየረገፈ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

‹‹ጠላት ሰተት ብሎ ገብቷል ሰተት ብሎ እንዳይወጣ እያደረግን ነው›› በማለትም ትግሉ ጠላት ለፈጸመው ወረራ በሚመጥን መልኩ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል፡፡

“ጠላት ጦርነቱን ሕዝባዊ አድርጎታል፤ እኛም ሕዝባዊ እንድናደርገው ጥሪ አስተላልፋለሁ” ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡ ሕዝቡ አርበኛ ሆኖ መታገል እንደሚገባውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዲጂታል ወያኔ በሚለቃቸው የሐሰት ወሬዎች ሕዝቡ ሊሸበር እንደማይገባውም አስገንዝበዋል፡፡ ለዚህም መንግሥት ትክክለኛውን መረጃ በየጊዜው ይሰጣል ነው ያሉት፡፡ ሰርጎ ገቦች የኀይማኖት አባት በመምሰል፣ የሚሊተሪ ትጥቅ ለብሰው፣ የሚሊሻ ዩኒፎርም ለብሰው፣ ሕዝብን ፍርሃት ውስጥ የሽብር ወሬ ይነዛሉ፡፡ ወደ ከተሞች በርካታ ሰርጎ ገቦች መግባታቸውንም አመላክተዋል፡፡ 

ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች ጭምር አጀንዳ ያላቸው በሰርጎ ገቦች እንደተያዙ በመግለጽም በሰርጎ ገቦች ላይ የሚደረገው ልዩ ቁጥጥር መጠናከር እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

በሁሉም ዘርፍ አንድነትን ማጠናከር ይገባል ያሉት አቶ አገኘሁ ጦርነቱን በመጠቀም አንድነትን ለመከፋፈል የሚደረግን ሙከራ መቀበል አያስፈልግም ብለዋል፡፡ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደ ትናንቱ መስዋእትነት እየከፈለ የኢትዮጵያን አንድነት ያስቀጥላል ብለዋል፡፡ ትግሉ የቱን ያህል ከባድ፣ መራራና ውስብስብ ቢሆንም ኢትዮጵያን ከመፍረስ እንታደጋታለን ነው ያሉት፡፡(አሚኮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top