በመተከል ዞን የህወሓትን ተልዕኮ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ወጣቱ መዘጋጀት እንዳለበት ኮማንድ ፖስቱ አስታወቀ።
የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሚገነባበትን ቀጠና ለማተራመስ የተነሳውን ሃይል የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ ወጣቱ ከሰራዊቱ ጎን በመቆም ህግን ማስከበር እንዳለበት የ22ኛ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሰይፈ ኢንጌ አሳስበዋል።
በመተከል ዞን የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዛሬ ጀምሮ ያላቸውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ በቀጠናው እየተንቀሳቀሰ ያለውን ሽፍታ ቡድን ማስወገድ አለበት በማለት ኮማንድ ፖስቱ ጥሪ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትሩን ጥሪ በመቀበልና ተግባራዊ ለማድረግ የጁንታውን ተልዕኮ ይዘው በመተከል ዞን የሚንቀሳቀሱ ሽፍቶችን በጋራ ማስወገድ መንግስት እንደማይታገስ ተገልጿል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት የጸጥታ ዘርፍ አማካሪ አቶ አብደላ ሸኸዲን በበኩላቸው የሽፍታው ቡድን በመንገድ ላይ በማስቆም ሰላማዊ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ በመሆኑ ይሄን ለማስወገድ በቁርጠኝነት መነሳት እና በመመከት የቀጠናውን ሰላም ማስመለስ ይገባል ብለዋል።
የሀገርን ሉዓላዊነት የደፈረው የህወሓት ቡድን በሰሜኑ ክፍል አደብ ሲገዛ መተከል ላይ ያለው በተመሳሳይ አውድ እየሄደ ግን ደግሞ በመንግስት በኩል የተኩስ አቁም ሲነሳ በመተከል ዞን የሚገኘው ቅርንጫፍ አሁንም የጥፋት ተልዕኮ ይዞ በመነሳቱ ይሄን ለማስወገድ የሁሉም ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ አብደላ ተናግረዋል።
የመንግስትን ትዕግሥት እንደ አቅም ማነስ በመቁጠር በተደጋጋሚ የንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለውን ሽፍታ ቡድን ሞት ምን እንደሆነ ለማሳየት ወጣቱ በቁርጠኝነት መነሳት እንዳለበት የተናገሩት ደግሞ የመተከል ዞን ዋና አስተዳደሪ አቶ ጋሹ ዱጋዝ ናቸው።
ቀጠናው የልማት ኮሪደር በመሆኑ ይሄን ለማስተጓጎል የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን አጀንዳ ተቀብለው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ወጣቱ ከሰራዊቱ ጋር በመሰለፍ ኢትዮጵያን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል።
የግልገል በለስ ከተማ ወጣቶች በበኩላቸው የህወሓትን አጀንዳ ለማስፈጸም እየተንቀሳቀሰ ያለውን ሽፍታ በማስወገድ የአካባቢውን ሰላም ለመመለስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።(መተከል ዞን ኮምኒኬሽን)