Connect with us

የአስመራው “ወዲ ስምኦን“ እንዳጫወተኝ !!

Social media

ነፃ ሃሳብ

የአስመራው “ወዲ ስምኦን“ እንዳጫወተኝ !!

የአስመራው “ወዲ ስምኦን“ እንዳጫወተኝ !!
(ገለታ ገ/ወልድ- ድሬቲዩብ )

እድሜው 44 አመት ገዳማ ነው ፡፡ ተወልዶ ያደገው ደግሞ አስመራ ከተማ ሲሆን ፣ የልጅነት ጊዜውን በአዲስ አባባ ማሳለፉን በሚገባ ያስታውሳል ፡፡

ኢትዮጵያን እንደ ሁለተኛ አገሩ፣ አማርኛንም እንደሚወደው ሁለተኛ ቋንቋ የሚቆጥረው ሀፍቱ ፤ በ1990ዎቹ መጀመሪያ ላይ ወደ አስመራ እንዲባረር ከመደረጉ በፊት ቄራ ጎፋ ሰፈር በርካታ የሸገር ጎደኞቹንና ያሳለፋቸውን ጣፋጭ ጊዜዎች በፍቅር ያስታውሳቸዋል ፡፡

ዳግም አዲስ አባባን የማየት እድል የገጠመው ካለፉት ሶስት አመታት ወዲህ የኢትዮ- ኤርትራ የቀውስ ሀቲት ከተቀየር በኋላ ነው ፡፡ እናም አሁን በአጋጣሚ በፈጠርነው ጉርብትና ምክንያት እኔና ሀፍቱ ስምኦን( ለዚህ ፅሁፍ ሲባል ስሙ ተቀይሯል ) ወዳጅና ጎረቤታማች ሆነናል ፡፡ ከመቀራረባችንም ብዛት ስለአዲስ አባባና አስመራ ፣ስለወቅታዊ ፖለቲካ ፣ ስለትግራይና ኤርትራ… ብዙ ብዙ እንጨወታለን ፡፡

በዚህ ፅሁፍ የምመለከተው ግን ስለህወሀት መሪዎች ክፋትና ብዙዎቹ ኤርትራዊያንን ያሳዘነ ድርጊት የጠቃቀሰልኝን ነጥቦች ነው ፡፡

ወያኔና ሻአቢያ በትጥቅ ትግል ባሳለፉበት ጊዜያት መናናቅና መጠራጠር ሊኖር ቢችልም ፣ ለአንድ አላማ ታግለው ደርግን መጣላቸው አንድ በጎ እርምጃ ነበር፡፡ ነገር ግን በስልጣን ክፍፍልና የኤርትራ አገረ መንግስት ምስረታ ወቅት ወያኔ ክዳት እንደፈፀመ ታጋይ ከነበረው አባቴ ጀምሮ ብዙ ኤርትራዊያን ያምናሉ ይላል ሃፍቱ ፡፡

(ኤርትራዊያንን በቢዝነስም ሆነ በመንግስት ስራ ውስጥ መጠራጠርና ማግለል፣ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር አብረው መኖራቸው እየተተው በባእድነት እንዲሳሉ ማድረግ፣ በወደብና ንግድ ወደሚፈለገው ትብብር አለመምጣታቸው ፣ በድንበርና ኮንትሮባንድ መጋጨት መጀመራቸው ፣ በሆላም በፖለቲከኞች አለመግባባት ስበብ ዘርና ማንነት ተለይቶ ኤርትራዊያን ሀብታቸው ተዘርፎ ከኢትዮጵያ እንዲባረሩ መደረግን የማጠው በዋናነት ወያኔ መሆኑን አብዛኛው ኤርትራዊ ያምናል ባይ ነው፡፡)

የኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ለመቀስቀሱ ብቻ ሳይሆን አስፈላጊ ላልነበረ መስዋእትነት መከፈል የሁለቱም አገሮች መሪዎች ግትርነት እንደነበር ወዲ ስምኦን አይክድም ፡፡

ከዚያ በኋላ ግን ለ18 አመታት ገደማ በኤርትራ ላይ አለም ማእቀብ እንዲጥልና አገሪቱ ለከፍተኛ ችግር እንድትጋለጥ ያደረገው ፣ ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያ ወገኖቻቸው ጋር በጠላትነት እንዲተያዩና የትብብር በር እንዲዘጋ አጥር የሆነው ፣ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረን የኤርትራዊያን የግል ሀብት እየነጠቀ ለዘመዶቹ ያከፋፋለው ህወሀት መሆኑን ከሊቅ እስከደቂቅ ጠንቀቅን እናውቃለንም ነው ያለው፡፡

( ከመነሻው በእምንት፣ በቋንቋ፣ በባህል ፣በደምና በጉርብትና ተሳስሮ ለዘመናት ከኖረው የትግራይ ህዝብ ጋር ኤርትራዊያንን ለማቋራረጥ እንደ ህወሀት እንቅፋት የሆነ አልነበረም ፡፡ የኤርትራ ህዝብ ግን ይህን ሁሉ በደል ተሸክሞ ፣ በሩን ዘግቶ አንድ ቀን ታሪክ እንደሚቀዬር እያሰበ በችግር ውስጥም ቢሆን ለመኖሩ መስክር ነኝ ሲልም በልበሙሉነት ነው፡፡)

“ ሌላውን ሁሉ ትተህ በሁለት ድሃ ግን አንድ የነበሩ አገሮች መካካል ያታከተን ፀብና ግጭት ፈትተን ወደ መደማማጥ እንምጣ የሚል የለውጥ መንፈስ ሲመጣ ፣ እንቅፋት መሆን የጀመረው ወያኔ አልነበረምን !!?” ይላል ወዲ ስምኦን ፣ እናዳውም ብዙዎች የአስመራ ልጆች እንደምንረዳው የዶ/ር አብይና የህወሀት አለመግባባት የተካረረው፣ አብይና ወዲ አፎም በአጭር ጊዜ በጀመሩት የሰላም መንገድ በመቅናቱ እንደሆነ ነው፡፡

እስኪ ከሰላም እንጂ ከጦርነት ምን ይገኛል ወገንን ከማስፈጀት በቀር ሲልም ዛሬን በመደመም እየታዘበ ነው ሀፍቱ፡፡

(እዚህ ላይ ላነሳልህ የምፈልገው አንድ ቁም ነገር ወያኔ ክፉና ቂመኛ ለመሆኑ በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ከሰማኒያ ሺ በላይ ኢትዮጵያዊያንን የሻአቢያ ምሽግ ላይ በመስደድ ሲያስፈጅ የነበረው በህዝብ ማእበል ነበር ፡፡ ብዙዎቹ ፈንጅ ማምከኛና የእሳት እራት የነበሩት ኢትዮጵያዊያን ግን የሌላ ብሄር ተወላጆች ነበሩ ፡፡

ኪሳራውም እጅግ የከፋና ወደኋላ ሁላችንንም የመለሰ ነበር ብሏል )
በእነዚህ ቂምና ቁርሾዎች ውስጥ የቆዩት አገራት ወደአዲስ ምእራፍ ገብተው ህዝባቸውን ማስማማት ሲገባቸው ፡፡ በቅርቡ የሰሜን ውጊያ “ የጦርነት ግብዥ “ ያደረገውስ ወያኔ አይደለም ማለት ይቻላልን !? የሚለው ወዲ ስምኦን ፣ ቀድሞ በኤርትራ ሰርጎ ገብ ልጆ መሪዎች ለማጥቃት የሞከረው ፣ በፕሮፖጋንዳ በኤርትራና በአብይ ጦር ተከበናል ያለው ፣ሚሳኤል ወደ ኤርትራ ያስወነጨፈው፣ በትግራይ ያሉ የኤርትራ ስደተኞችን ያጠቃው ወያኔ መሆኑን ስታይ ፣የሴራውን መጠን በሚገባ ትረዳለህ በማት ያስረዳል ፡፡

እንደሀፍቱ ጨዋታ ፣ የኤርትራ ጦር ራሱን ለመካላከልም ሆነ የቆየውን በደልና ቁጭቱን ለመበቀል ወደ ትግራይ ገብቶ ያደረገውን ቢያደርግ ሙሉ በሙሉ የማይፈረድበት ፣ ወያኔ በስራው ልክ መቀጣት ስላለበት ነው ፡፡ ህልውናውንም ለማረጋጋጥ ነው ፡፡ ምንም እንኳን መከራው ለህዝቡ ቢተርፍም ፡፡

በቀጣይም ህወሓት ካልተወገደ ወይም ሙሉ በሙሉ ከኖረበት ወንጀል ተንጠፍጥፎ ካልወጣ ያ ህዝብ እረፍት አያገኝም ሲል ይሰጋል ፡፡ “ፈጣሪ ይርዳው ከባቢውን !!“በማለት ፡፡

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top