Connect with us

የሀገራችንን ህልውና በጋራ ክንዳችን እናስከብራለን ❗️

የአብን አስቸኳይ የህልውና ማረጋገጫ ህዝባዊ ጥሪ!!
Social media

ዜና

የሀገራችንን ህልውና በጋራ ክንዳችን እናስከብራለን ❗️

የሀገራችንን ህልውና በጋራ ክንዳችን እናስከብራለን ❗️
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ለክልላት ልዩ ኃይሎቻችን የዘመቻ ተሳትፎ የተሰጠ የእውቅናና ምሥጋና መግለጫ
===============
ለውድ የኢትዮጵያ ህዝብ !

መላው ህዝባችን የአሸባሪውን የትህነግ የክህደት ወረራ ለመመከት ከዳር እስከዳር በመነቃነቅ ህልውናውን ለማስከበር ዘመቻውን እየተቀላቀለና እየደገፈ ይገኛል። በዲያስፖራው በኩልም ሰፊ የሆነ አማራዊና ሀገራዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን ከገንዘብና ቁሳቁስ ድጋፍ ባሻገር ጉልህ የአድቮኬሲና የዲፕሎማሲ ስራዎችን ለማከናወን ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን ተረድተናል።

በሌላ በኩል የትህነግ ስብስብ በአማራ ህዝብና በሀገራችን ላይ የከፈተውን ዘርፈብዙ ጥቃት በጋራ ለመመከት ሁሉም ክልሎች ዘመቻውን በይፋ መቀላቀላቸውን በመግለፅ የልዩ ሀይልና የፖሊስ ሰራዊታቸውን ወደ ግንባር እያንቀሳቀሱ መሆኑ ታውቋል ።
መላው ኢትዮጵያውያን በአንደኛቸው ላይ የሚፈፀም ጥቃት በሁላቸውም ላይ እንደተፈፀመ አድርገው በመውሰድ የሀገራቸውን ህልውና በተመለከተ ወጥ የሆነ የጋራ አቋም እንዳላቸው ያረጋገጡበት ታሪካዊ ትብብር ለፅንፈኛና ለጥላቻ ሀይሎች ጠንካራ መልእክት አስተላልፏል።

በተለይ ኢትዬጵያዊ ማንነትና አርበኝነት ሊጠፋ የማይችል የጋራ እሴት መሆኑን ከማረጋገጡም በላይ የጥላቻ ሀይሎች ለዘመናት ሲያሰራጩት የነበረው ስሁት ትርክት በማያወላዳ መልኩ ግብአተመሬቱ እንደሚፈፀም አይነተኛ ማሳያ ነው።
ኢትዬጵያውያን ዘመናትን የተሻገረና ለነፃነት የተደረገ የጋራ ተጋድሎና የአርበኝነት ታሪክ እንዲሁም የበጎ ማህበራዊ ቁርኝት ባለቤቶች መሆናቸውን በተግባር ያረጋገጠ ነው።

ንቅናቄያችን አብን ይሄን የጋራ ሀገራዊና ወገናዊ ስሜት አጠናክሮ ለማስቀጠል በሚደረገው ጥረት ንቁ ተሳታፊ እንደሚሆን እያረጋገጠ ፣ በሁሉም ኢትዬጵያዊ ወንድምና እህቶቻችን ላይ የሚፈፀም ጥቃት ቢኖር በእኛ ላይ እንደተፈፀመ የምንቆጥረውና አብረን በግንባር ተሰልፈን የምንታገለው እንደሚሆን ሀገራዊ ቃልኪዳን መያዛችንን ስንገልፅላችሁ በኩራትና በደስታ ነው።

ደሴ፣ ወሎ፣ ኢትዮጵያ
ሀምሌ 10/2013 ዓ.ም

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top