Connect with us

ሳይገድሉ፤ ገድለዋል በሚል የተፈረደባቸው ግለሰብ ከአምስት ዓመት እስር  በኋላ ተለቀቁ

ሳይገድሉ፤ ገድለዋል በሚል የተፈረደባቸው ግለሰብ ከአምስት ዓመት እስር በኋላ ተለቀቁ
የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት

ዜና

ሳይገድሉ፤ ገድለዋል በሚል የተፈረደባቸው ግለሰብ ከአምስት ዓመት እስር  በኋላ ተለቀቁ

ሳይገድሉ፤ ገድለዋል በሚል የተፈረደባቸው ግለሰብ ከአምስት ዓመት እስር  በኋላ ተለቀቁ

በሀሰተኛ ማስረጃ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት የተፈረደባቸው ግለሰብ በልዩ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ ከእስር ነፃ መውጣታቸውን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መስሪያ ቤት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዓለምሸት ምህረቴ እንደገለፁት በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የሰላ ድንጋይ ከተማ ነዋሪ የሆኑት ግለሰብ ከአምስት ዓመት በፊት በእንጀራ እናቷ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ  ተገድላለች በሚል ግለሰቧ መሞቷ በሃሰተኛ ማስረጃ ተረገግጦ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ የ20 ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት ተጥሎባቸው ነበር።

ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ  የእንጀራ ልጇን ገድላለች በሚል የሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ የወንጀል መዝገብ ቁጥር 134/2008 ክስ መስርቶባቸው ሲከራከሩ መቆየታቸውን ይታወቃል። የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም የቀረበውን ክስና ማስረጃ በመመርመር ጥፋተኛ ናቸው ብሎ በ20 ዓመት ፅኑ እስራት እና በአምስት ዓመት ከማንኛውም ማህበራዊ ግንኙነት እንዲገለሉ ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወቃል ብለዋል።

በተሠጠው ውሳኔ መሠረት ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ አምስት ዓመት በደብረብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር ከቆዩ በኋላ ሞተች ተብላ በሀሰተኛ ማስረጃ የተረጋገጠላት ግለሰብ ከሌላ አካባቢ በሕይወት ቆይታ በቅርብ ጊዜ ወደ ትውልድ አካባቢዋ በመምጣቷ ሞተች ተብላ ጥፋተኛ ያልሆነችን ግለሰብ እንደ ጥፋተኛ ቆጥሮ ማረሚያ ቤት እንድትወርድ ያደረገችው ግለሰብ ማንነቷ በአካባቢው ህብረተሰብ አና በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

በሃሰተኛ ማስረጃ ተፈርዶባቸው በሰሜን ሸዋ ዞን በደብረ ብርሃን ማረሚያ ቤት በእስር የቆዩት ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በሰሜን ሸዋ ዞን ዐቃቤ ሕግ መምሪያ እና ሌሎች የፍትሕ አካላት ጋር በጋራ በተደረገ የጣቢያ እና የማረሚያ ቤት ጉብኝት በተደረገው ማጣራት እና ሞተች የተባለችው ግለሰብ በሕይወት በመገኘቷ ምክኒያት ጉዳዩ የተገኘ ሲሆን በአማራ ክልል የተሻሻለው የይቅርታ አሰጣጥ መወሰኛ መመሪያ ቁጥር 30/2010 መሠረት ጉዳያቸው የሰሜን ሸዋ ዞኑ ደብረብርሃን ማረሚያ ቤቶች መምሪያ በአማራ ክልል ማረሚያ ቤቶች አማካኝነት ለአማራ ክልል ይቅርታ ቦርድ ቀርቦ የአማራ ክልል መስተዳድር ምክር ቤት ሰኔ 29 ቀን 2013ዓ.ም ባካሄደው 5ኛ ዙር 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛ አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ በልዮ ሁኔታ ያለ ቅድመ ሁኔታ የተፈረደባት በሃሰተኛ ማስረጃ መሆኑን በማረጋገጥ ከእስር በይቅርታ ነፃ እንዲወጡ የተጣለባቸው ገደብ እንዲነሳላቸው ወስኗል።

የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው አያይዘው የክልሉ የሕግ አስከባሪ አካላት የጣቢያ እና የማረሚያ ቤት ጉብኝት በማድረግ የማጣራት ስራ ትኩረት ሰጥተው በመስራትና የቅርብ ክትትል በማድረግ የወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ስርዓት ተግተው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበው፡፡የክልሉ መንግስትም  በወንጀል ፍትሕ አስተዳደሩ ላይ ዘርፈ ብዙ ማሻሻያዎች ማድረግ እንደሚገባ ታምኖበታል ብለዋል፡፡

በወ/ሮ አዛለች ቤተምንዳ ላይ የገጠመው ጉዳይ ያለ ማስረጃ የሚታሰሩ ታራሚዎች በሞራል፣ በኢኮኖሚ፣ በማሕበራዊ፣ በቤተሰብ ላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት ካሳ የሚካሱበት የሕግ ማዕቀፍ የሌሎች አገሮችን ልምድ በመቀመር  ማዘጋጀት እንደሚገባ አስተማሪ ሆኖ አልፏል ብለዋል፡፡(የአማራ ክልል ጠ/ፍ/ቤት)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top