Connect with us

የቦረና ብሄራዊ ፓርክ እና የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን በተመለከተ

የቦረና ብሄራዊ ፓርክ እና የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን በተመለከተ
አዲሱ አረጋ ቅጤሳ

ነፃ ሃሳብ

የቦረና ብሄራዊ ፓርክ እና የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን በተመለከተ

የቦረና ብሄራዊ ፓርክ እና የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክን በተመለከተ

አዲሱ አረጋ ቅጤሳ (ከቦረና)

ሰሞኑን በቦረና ብሄራዊ ፓርክ ያደረግኩትን ጉብኝት ተከትሎ ‹‹ነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ወደ ቦረና ብሄራዊ ፓርክ ተቀይሮ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተካሏል›› የሚል ቅሬታ አዘል አስተያየቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች አስተዉያለሁ፡፡  ጉዳዩን  ለማብራራት ያህል፡- 

የቦረና ብሄራዊ ፓርክ በቀድሞ ስያሜዉ  የያቤሎ የዱር እንስሳት መጠለያ (Yabello wild life sanctuary) ተብሎ የሚታወቅ ሲሆን   በ2500 ስኩዌር ኪሎሜትር ቦታ ላይ ያረፈ ሆኖ በቦረና ዞን ያበሎ፣ ኤልወዬ እና ድሬ ወረዳዎች ዉስጥ የሚገኝ ነዉ፡፡ በፓርኩ ዉስጥ ትልቁ የሜዳ አህያ (Gravy’s Zebra) ጨምሮ መደበኛ የሜዳ አህዮች፣ ብርቅዬ አዕዋፋት እና ሌሎች የዱር እንስሳት ይገኛሉ፡፡  

እነዚህ የዱር እንስሳት እና በፓርኩ የሚገኙ የቱሪዝም መስዕቦች ተጠብቀዉ የላቀ ሀገራዊ ጥቅም እንዲያስገኙ በማሰብ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለሚለመለከታቸዉ አካላት ያቀረበዉ ተደጋጋሚ ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ የዱር እንስሳት መጠለያዉ ህጋዊ አግባብን ተከትሎ  ወደ ብሄራዊ ፓርክ አድጓል፡፡

ይህ የዱር እንስሳት መጠለያ ወደ ብሄራዊ ፓርክ ማደጉ የሀገራችንን የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማሳደግ የምናገኘዉን ሀገራዊ ጥቅም ከፍ ከማድረግ ዉጪ ማንም ላይ የሚያስከትለዉ ጉዳት የለም፡፡ የቦረና ብሄራዊ ፓርክ ከነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ጋር ምንም የሚያገናኘዉ ወሰን የለዉም፡፡ በመቶዎች ኪሎሜትሮች የሚራራቅና ወሰን የማይጋራ ፓርክ ነዉ፡፡   እዉነቱን ለመናገር የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ፣ ቦረና ብሄራዊ ፓርክም ሆነ ሌሎች የሀገራችን ብሄራዊ ፓርኮቻችን የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሀብት እንደመሆናቸዉ በጋራ ልንከባከባቸዉ፣ ልናለማቸዉ እና እና ለሀገራዊ ጥቅም ልናዉላቸዉ ይገባል፡፡

ሆኖም ‹‹የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ ወደ ቦረና ብሄራዊ ፓርክ ተቀይሯል ይህንንም ያደረጉት ተረኞች ናቸዉ ›› ተብሎ ከተነዛዉ ወሬ እና ሌሎች መሰል ፕሮፓጋንዳዎች መጠንቀቅ ያስፈልገናል፡፡ እንደዚህ አይነት የሀሰት ፕሮፓጋንዳ በመንዛት በህዝቦች መካከል መጠራጠር እና ቁርሾን ለመፍጥር የሚንከላወሱት ሰሞነኛ አፍላ ጽንፈኛ ብሄርተኞች መሆናቸዉን ልብ ልንል  ይገባል፡፡

እነዚህ ጽንኞች በኦሮሞ ህዝብ እና በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ላይ ‹‹ተረኞች›› የሚል የሀሰት ዉንጀላ ሳይታክቱ በማቅረብ ህዝብን ከህዝብ የማቃቃር ስራ በመስራት  እንደሚገኙ ማስተዋል ይገባል፡፡

  • ህዝባችንን አስተባብረን በየትምህርት ቤቱ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎችን ስንገነባ ‹‹ተረኞች›› ይሉናል፡፡
  • ከ300 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በመስኖ ስንዴ አልምተን ሀገራችንን ከስንዴ ልመናና ተረጂነት ለማዉጣት ስንታትር ‹‹ተረኞች›› ይሉናል፡፡
  • ለትምህርት ቅድሚያ ሰጥተን ከሌሎች ፕሮጀክቶቻችን ቀንሰን የኢፋ ቦሩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ገንብተን ስናጠናቅቅ‹‹ተረኞች›› ይሉናል፡፡
  • በሀገር ደረጃ ሜካናይዜሽንን ለማበረታታት የወጣዉን የማትጊያ ፖሊሲ እና የብድር አገልግሎት ተጠቅመን  ትራክተሮች አስመጥተን ለአርሶ አደሮቻችን ስናደረስ ‹‹ተረኞች›› ይሉናል… ወዘተ ወዘተ…

እነዚህ ጥቂት ቡድኖች  ስናስነጥስ እንኳ ‹‹ተረኞች ስለሆኑ አስነጠሱ›› ከማለት ወደ ኋላ የማይሉ ነዉረኞች እንደሆኑ   ይታወቃል፡፡  አፍላ የብሄር ጽንፈኝነት ያሳዉራልና፡፡

ሳጠቃልል የቦረና ብሄራዊ ፓርክ እና የነጭ ሳር ብሄራዊ ፓርክ በእጅጉ የተራራቁ ናቸዉ፡፡ ሆኖም ሁለቱም የሀገራችን ሀብቶች ናቸዉ፡፡ ለግንዛቤ እንዲረዳ ቀጥሎ ያለዉን ካርታ አያይዛለሁ፡፡

ከሰላምታ ጋር

አዲሱ አረጋ ቅጤሳ (ከቦረና)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top