Connect with us

በአዲስ አበባ ድምፅ ግብፅ ስትሸበር

በአዲስ አበባ ድምፅ ግብፅ ስትሸበር
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

በአዲስ አበባ ድምፅ ግብፅ ስትሸበር

በአዲስ አበባ ድምፅ ግብፅ ስትሸበር

(ሠላም ሙሉጌታ)

🔹 ” ስለግድቡ መልዕክት ያሰሙት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመንግስት ቅጥረኞች ናቸው ” ሃኒ ረስላን

አዎ መልዕክቱ በሚገባ ደርሷቸዋል ፤ ግባችን ተሳክቷል። የትላንቱ የህዝብ ሙስሊሙ ሃገራዊ የህዳሴ ግድብ ድምፅ ካይሮን አሸብሯል።

የዘመናት የፍጅት ካርዳቸው እንደተቃጠለ ተገንዝበዋል። ( ዘር እና ሃይማኖት ዋንኛው ኢትዮጵያን ማዳከሚያ ካርዳቸው እንደ ነበሩ እሙን ነው)

ግብፃውያኑ ንዴት እና ድንጋጤያቸውን መደበቅ አልቻሉም።

አዲስ አበባ ላይ የታየው ትዕይት እንቅልፍ የነሳው የግብፅ መንግስት ፀረ ኢትዮጵያ -ስትራቴጂስቱ ሃኒ ረስላን ንዴቱን ተንፍሷል።

ሰውዬው አዲስ አበባ ላይ የተመለከተውን እና የሰማውን ማመን ተስኖት፤ በፌስቡክ ገፁ የጨለማ ዘመን ፓርሮፓጋንዳውን ለመድገም ሞክሯል።

ሃኒ ረስላን ፥ በኢድ ስርአተ ፀሎት ላይ መልዕክት ያስተላለፋት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ፦

🔹የመንግስት መልዕክተኞች…ቅጥረኞች ናቸው

🔹የኢትዮጵያ ተዳክማለች ……ተከፋፍላለች

🔹አማራ ኦሮሞ ….ቅብርጥስ  እያለ ዘር እየጠራ በለመደበት ሲሽከረከር አድሯል ….

የለመደውን ከፋፋይ መርዝ ለመርጨት ተንደፋድፏል ፤ ደግነቱ እርሱም ሆነ መንግስቱ ህዝባዊ ማዕበሉ  በግድባችን ጉዳይ የመርፌ ቀዳዳ ያህል ዕድል እንደማይሰጣቸው ተገንዝበውታል !!

ሃኒ ረስላን Al ahram center for political and strategic studies የተባለው ዋንኛው የግብፅ የደህንነት ጥናት ተቋም  ከፍተኛ ሃላፊ የሆነ ሰው ነው።

አምና የዲጂታል ሚድያ ዘመቻችን የግብፅን አጥር ገና መነቅነቅ እንደ ጀመረ ” የሙስሊም ወንድማማች ሃይሎች ናቸው ፥ ኢትዮጵያዊያን አይደሉም ፣ ተከፋዮች ናቸው እንጂ ኢትዮጵያዊያን ህብረት የላቸውም….” ብሎ በአደባባይ የተናገረ ሰው ነው ።

በአባይ ጉዳይ የግብፅ ዲኘሎማሲ እና  ፓሮፓጋንዳ ዋና  መሀንዲስ፥

የፀረ ኢትዮጵያ ዘመቻዎችን በተለያዩ አለምአቀፍ ሚድያዎች ላይ የሚመራ ስትራቴጂስት ነው፣

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top