Connect with us

አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞ ፓርላማ አባል እንደጻፉት

አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞ ፓርላማ አባል እንደጻፉት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞ ፓርላማ አባል እንደጻፉት

አብዱራህማን አህመዲን የቀድሞ ፓርላማ አባል እንደጻፉት

ይድረስ ለትምህርት ሚኒስቴር፣

ይድረስ ለባህል ሚኒስቴር፣

ይድረስ ለሴቶችና ህፃናት/ወጣቶች ሚንስቴር፣

ጉዳዩ የልጆች ቴሌቪዥን ጣቢያን ይመለከታል።

ባለፉት 30 ዓመታት ካጠፋናቸው ተቋማት ውስጥ ሁለቱ የቄስ ት/ቤት እና የቁርዓን ት/ቤት ናቸው። እነዚህ ተቋማት በዋናነት የልጆችን ግብረ ገባዊ እና ስነ ምግባራዊ ሰብእና የምናንጽባቸው ነበሩ።

እነዚህ ተቋማት በመፍረሳቸው ዛሬ ከአባገዳ ላይ ማይክሮፎን የሚቀማ፣ ሙፍቲና የመስጅድ ኢማም የሚሳደብ፣ ጳጳስ በየአደባባዩ የሚዘልፍ፣ ሽማግሌዎችን በካራቴ የሚማታ … ትውልድ አፍርተናል።

በቅርብ ጊዜ ይህንን ክፍተት የሚሞላ “የኢትዮጵያ ልጆች” የሚባል ቴሌቪዥን ጣቢያ ተከፍቶ ነበር። ጥሩ ጥሩ ልጆችን የሚያንፁ ፕሮግራሞች ነበሩት። ባላወቅነው ምክንያት ጣቢያው ተዘጋ። እንደዚያ ዓይነት ጣቢያዎች ዱሮውንም በግለሰብ ሳይሆን በመንግስት በጀት መተዳደር የነበረባቸው ናቸዉ።

ሁለቱ ሚኒስቴር መ/ቤቶች ትውልድን በእውቀትና በስነ ምግባር የማነጽ ኃላፊነት ያለባችሁ በመሆኑ ነገ ዛሬ ሳትሉ የሚከተለውን ታደርጉ ዘንድ በኢትዮጵያ ልጆች ስም እጠይቃለሁ፦

– የኢትዮጵያ ልጆች ቴሌቪዥን ይጠቀምበት የነበረውን ፎርማት ሙሉ በሙሉ ተደራድሮ መግዛት፣ በባለሙያዎች ታይቶ ማሻሻያና ተጨማሪ የጎደሉትን ማሟላት፣

– መንግስት 24 ሰዓት የሚሰራ የልጆች ቻናል መክፈት ወይም ካሉት ቻናሎች አንዱን 24 ሰዓት ለልጆች አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ፣

ከአክብሮት ጋር

አብዱራህማን አህመዲን

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top