Connect with us

በአዲስ አበባ ከተማ ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ቁጥር ቀነሰ

በአዲስ አበባ ከተማ ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ቁጥር ቀነሰ
የኢት መድን ፈንድ

ዜና

በአዲስ አበባ ከተማ ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ቁጥር ቀነሰ

በአዲስ አበባ ከተማ ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ቁጥር ቀነሰ

 የመድን ፈንድ አስተዳደር ኤጀንሲና ጤና ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የተሽከርካሪ አደጋ አስቸኳይ ህክምና አፈጻጸማቸውን ገመገሙ፡፡

  በአዳማ ከተማ በተካሄደው መድረክ ላይ ሚኒስቴሩና የኤጀንሲው የሚመለከታቸው ባለሙያዎች እንዲሁም ከክልሎችና  የከተማ አስተዳደሮች የፖሊስና የጤና ቢሮ ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን መድረኩን ዶ/ር ኃይለሚካኤል ፍቅሬ በጤና ሚኒስቴር የድንገተኛና ጽኑ ህክምና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲካሄድ ውሏል፡፡ 

 የተሽከርካሪ አደጋ አስቸኳይ ህክምና በዋነኝነት በጤና ሚኒስቴርና የክልል ጤና ቢሮዎች እንዲሁም በፖሊስ የተጠናከረ ቅንጅት የሚተገበር ሲሆን በግምገማው መድረክ ላይ የየክልሎቹ ጤና ቢሮና የፖሊስ ኮሚሽን ተሳታፊዎች ባቀረቧቸው  የዘጠኝ ወራት ሪፖርቶች ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

  ከቀረቡት ሪፖርቶች መረዳት እንደተቻለው አብዛኞቹ የህክምና ተቋማት የተሽከርካሪ አደጋ ነጻ አስቸኳይ ህክምና አገልግሎትን ከሞላ ጎደል እያከናወኑ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በጤና ሚኒስቴርና በኤጀንሲው ለየቢሮዎቹ የሚላከውም ተዘዋዋሪ ፈንድ በአግባቡ እየተወራረደ መሆኑ ታውቋል፡፡

  የመድን ፈንድ አስተዳዳር ኤጀንሲ ገጭተው ባመለጡና 3ኛ ወገን የመድን ሽፋን በሌላቸው ተሽከርካሪዎች ጉዳት ለሚደርስባቸው ሰዎች ተገቢውን ካሳ የሚከፍል ሲሆን ከዚህ ጋር በተያያዘም በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ ገጭተው የሚያመልጡ አሽከርካሪዎች ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየቀነሰ መምጣቱን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ካቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል፡፡

  ከሪፖርቱ መረዳት እንደተቻለው በ2013 ዓ/ም ባለፉት 9 ወራት ብቻ 40 ሰዎች ገጭተው ባመለጡ አሽከርካሪዎች የሞት አደጋ የደረሰባቸው ሲሆን በህብረተሰቡና በፖሊስ ያላሰለሠ ክትትልና አሰሳ 9 የሚሆኑት ተይዘው ለህግ ተላልፈው መሰጠታቸው ታውቋል፡፡ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ገጭተው ባመለጡ አሽከርካሪዎች የሞት አደጋ የደረሰባቸው ተጎጂዎች ቁጥር ከ 61 ወደ 40 የቀነሰ ሲሆን ተይዘው ለህግ የቀረቡትም ከ 9 ወደ 11 ከፍ ማለቱም ታውቋል፡፡(የኢት መድን ፈንድ)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top