Connect with us

” ለብልሆቹ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች እጅ ሰጥተናል” የግብፃውያን አስተያየት

" ለብልሆቹ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች እጅ ሰጥተናል" የግብፃውያን አስተያየት
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

” ለብልሆቹ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች እጅ ሰጥተናል” የግብፃውያን አስተያየት

” ለብልሆቹ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች እጅ ሰጥተናል” የግብፃውያን አስተያየት

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

ማጣፊያው አጥሯቸዋል

(ሰላም ሙሉጌታ)

ቁጣ ፣ ጥርጣሬ ፣ ክፍፍል፣ ውንጀላ ፣ ተስፋ መቁረጥ የግብፅ ሚዲያ የሃሳብ ምልልስ መድረኩን ሞልቶታል። የግብፅ ህዝብ ተለምዷዊው የባለስልጣናቱን መግለጫ መስማት እንደታከተው ከብዙዎች አስተያየት ይደመጣል። ያልተጨበጠ ተሰፋ እና ዛቻን በማፈራረቅ ሲያሰሙ የነበሩ የግብፅ ባለስልጣናት  ከሰሞኑ ቃላቸው ተቀባይ እና አድማጭ  ወደ ማጣት ተሸጋግሯል። የግብፅ ህዝብ የመንግስታቸው ከንግግር ያላለፈ፣ በተግባር ያልተገለፀ  የአመታት የቃላት ጋጋታ አሁን ” በቃን” እያሉ ነው።

በህዳሴ ግድብ ድርድር የመጨረሻው ዕድል ( Last chance ) ሲሉት የነበረው የኪንሻሳው ድርድር  የእስከዛሬውን ጨዋታ የሚቀይር አንዳች ውጤት ያመጣል የሚል ተስፋ ነበራቸው። ግን ምንም ሳይገኝ ቀረ !! ምንም ካለመገኘቱ በላይ ለነገ ሌላ ተስፋ የሚሆናቸውን ጭላጭል ዕድል እንዃን አልፈነጠቀላቸውም ። በተቃራኒው ቀናት መንጎዳቸውን፤ ወደ  ክረምቱ መገስገሳቸውን ቀጠሉ።

አሁን ሚዲያ እና ኘሮፓጋንዳቸው የሸፈነውን እውነት ጊዜ እየፈታው መጥቷል ። የግብፅ መንግስት በህዳሴ ግድብ ዲኘሎማሲ መረታቱን ህዝባቸው ማመኑን በየሚዲያዎቻቸው ላይ እየገለፀ ነው። የግብፅ መግለጫ እና ማስፈራሪያ ኢትዮጵያን እንዳላስቆመ  ተገንዝበዋል።

የግብፅ ሚድያን በቅርበት ስከታተል በቆየሁባቸው ጊዜያት እንደአሁኑ  ህዝባቸው ተስፋ የቆረጡበትን ወቅት አላየሁም። ከዚያም በላይ የሚፈሩትን ጨፍጫፊውን የአልሲሲን መንግስት እንዲህ በገሃድ ሲዘልፋ እና ሲተቹ አልተመለከትኩም ። በግብፅ ህዝብ እና መንግስት መካከል በቋፍ ላይ የነበረው መተማመን ይበልጥ ተሸርሽሯል። በህዳሴ ግድብ ላይ ነገሮች ሁሉ ከቁጥጥራቸው ውጭ መሆኑን እያመኑ ነው። በየሚዲያው ከሚሰጡት አስተያየት ያላቸውን የሃሳብ መዘባረቅ እና ክፍፍል እንዲሁም በመንግስት ላይ እየጨመረ የመጣውን እምነት ማጣት መገንዘብ ይቻላል።

ባለፋት ሰባት ቀናት ግብፃውያን ዜጎች አስተያየት በመስጠት በስፋት የሚሳተፋባቸውን አራት ሚድያዎች ለመከታለል( monitor ማድረግ) ሞክሬያለሁ ። የአስተያየቶቹ ይዘት የግብፅ መንግስት መሸነፉን ፣ የግብፅ  መንግስት ሹማምንት ብሄራዊ ጥቅማቸውን እንደሸጡ ፣ ኢትዮጵያ አስር አመት እንዳታለለቻቸው ፣ የግብፅ ህዝብ በሃገሬው ባለስልጣናት ላይ የነበረው  እምነት እንደተሟጠጠ እንዲሁም የእስራኤል እጅ ከኢትዮጵያ ጀርባ እንዳለ እና የግብፅ መሪዎችም በእስራኤል እንደተደለሉ የሚገልፁ ናቸው።

ከተመለከትዃቸው አስተያየቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል ፦

አብዱል ፈታ አልሲሲ ንፁህ ግብፃዊ አይደሉም ። ቅድመ አያታቸውን በመጥቀስ ዝርያቸው አይሁድ ነው ፤ ስለዚህም የግብፅን ጥቅም ከእስራኤል ጋር ተመሳጥረው አሳልፈው እየሸጡ ነው። ሳማ ሽኩሪም (ው/ጉ/ሚኒስትሩ ) የአይሁድ ጉቦኛ ነው።

ከአስር አመት በኋላ ኢትዮጵያዊያን  አሳስቀው ወሰዱን ። የግብፅ ወኪሎች አሁን ለብልሆቹ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ሙሉ በሙሉ እጅ ሰጥተዋል። ከዚህ በኋላ ተስፋ ምንናደርግበት አግባብ የለም።

ግብፅን ኢትዮጵያዊያን አያውቋትም ፥ ፈጣሪ የሚወዳት በቅዱስ መፅሃፍት ላይ የተጠቀሰች ሃገር ናት ፥ እርሱ ፈጣሪ አለልን።

ኑ ሲሏቸው ሲሄዱ…ሲደራደሩ ፣ ኑ ሲሏቸው ሲሄዱ…ሲደራደሩ…ቆይተው  በመጨረሻ ግብፅ በአሳዛኝ ሁኔታ ተሸንፋለች ፤ የሁሉም በር ዝግ ነው ከዚህ በኋላ።

እስራኤል ነበረች ግድቡን ያስጀመረችው ፣ይህ እየታወቀ አስር አመት የእኛ መንግስት ተታለለ ። ከአሁን በኋላ እንደሚፈልጉት ሊያደርጉን ነው በቃ።

የግብፅ መንግስት አምና ሲያደርግ የነበረውን ነገር ነው ዘንድሮም ሲደግም የከረመው፣ መግለጫቸው እንዃን ተመሳሳይ ነው። አማራጬ ጦርነት ነው።

ይህ መንግስት ግብፅን ወደ ኋላ እየወሰዳት ነው ሃገራችንን የምትፈራ ነበረች ፣ አልሲሲ ደካማ አደረጋት ።

ሃያል ጦር እያለን ዝም አንልም አማራጫችን እርሱ ነው። መንግስታችን አቅሙን ማሳየት አለበት ፤ በጥም ከማለቅ በውጊያ መሞት ይሻለናል።

የአልሲሲ መንግስት ከውስጥም ከውጭም ማጣፊያው አጥሮታል። ግድቡን ለውስጥ ፖለቲካው ድጋፍ ማሰባሰቢያነት የሚያውልበት ዕድል ተሟጧል። የግድቡ ሙሌት አይቀሬ በመሆኑ ” ያ ሁሉ ዛቻ እና ቃል የትገባ? ” ለሚለው የግብፃውያን አይቀሬ ጥያቄ  ማምለጫ ፍለጋውን የተያያዘው ይመስላል።

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top