Connect with us

ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን  ከፓርቲነት  መሰረዙ አግባብ ነው አለ

ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን ከፓርቲነት መሰረዙ አግባብ ነው አለ
FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.)

ዜና

ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን  ከፓርቲነት  መሰረዙ አግባብ ነው አለ

ፍርድ ቤት የምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባርን  ከፓርቲነት  መሰረዙ አግባብ ነው አለ

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 9ነኛ የምርጫ ጉዳዮች ችሎት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር  ከፓርቲነት  መሰረዙ አግባብ ነው ሲል ውሳኔ ሰጠ።

ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የተሰጠው   በኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር እና በኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ መካከል   የነበረውን ክርክር የሁለቱንም ተከራካሪዎች ማስረጃን መርምሮ  ነው ።

የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር  በየካቲት 19 ቀን 2013 ዓ.ም ለፍርድ ቤቱ  ባስገባው የክስ መመስረቻ  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በታሳስ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ከተወዳዳሪ ፓርቲነት ሰርዞኛል፣  ቦርዱ  በማጣራት ሂደቱም ለእኔ አሳውቆ አስተያየት አልሰጠሁበትም ይህ ደግሞ የመከላከል መብቴን ያለጠበቀ ነው ሲል  ክስ አቅርቦ ነበር።

ፍርድ ቤቱም  የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ  የመስራች አባላት መረጃን የማጣራት ስራን ተከትሎ ቦርዱ ያገኘውን ግኝት የሚያሳይ ሪፖርት ማህደር እንዲያቀርብ ትዛዝ ሰጥቶት ነበር።

ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባቀረበው ማሰረጃ  መሰረት ÷ የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር  የመስራች አባላት   በሃረሪ ክልል በተወደሰ ሁለት የአባላት ናሙና  እና በድሬደዋ አስተዳደር ደግሞ በተወሰደ 10 የአባላት ናሙና  ሁሉም የሌሉ መሆናቸውን አመላክቷል።

 እንዲሁም  ከአማራ ክልል 10 የአባላት ናሙናዎችን ተወስዶ ሁሉም በቦታው የሌሉ መሆናቸውን ቦርዱ  ባቀረበው ማስረጃ ገልጿል።

 በኦሮሚያ ክልልም 98 የአባላት ናሙና ተወስደው 25ቱ  ብቻ መኖራቸውን እንዲሁም 53ቱ አባላት ደግሞ ኗሪ አለመሆናቸውን  የሚገልጹ 20 ሰነዶች አቅርቧል።

በተጨማሪ ቦርዱ ባዘጋጀው ዝርዝር ላይ  18 አድራሻቸው ያልታወቀ  ወይም ተገኝተው ሊረጋገጡ ያልቻሉ መሆናቸውን በማስረጃ  ያቀረበ ሲሆን÷ በዚህ ሂደትም አባላቱ ይኖራሉ  ከተባለበት አስተዳደር ፣ወረዳ፣ቀበሌ በሃላፊዎች ተፈርመው በማህተም የተረጋገጡ ማስረጃዎቸን ቦርዱ  ለችሎቱ አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም ይህን ማስረጃ ለኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር  እንዲደርሰው ካደረገ በኋላ ለትከክለኛ  ፍትህ አሰጣጥ እንዲረዳ በማለት ፓርቲው ያለውን አሳማኝ ማስረጃ እንዲያቀረብ  ፍርድቤቱ  አዟል።

ፓርቲውም  የቤት ኪራይ ውል፣ኦዲተር የቀጠረበት ውል 2 ገጽ ተያያዥ ማስረጃ፣  እንዲሁም በህዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም ያከናወነውን የጠቅላላ ጉባኤ 39 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የማአከላዊ ኮሚቴ አባላት የተሰጣቸውን ሃላፊነት ለመወጣት የገቡትን ቃል 2 ገጽ ሰነድ እና በ450 ሰዎች የተፈረመበት 8 ገጽ ሰነድ የመስራቸ አባላት ዝርዝር ያለበት ሰነድ አቅርቧል።

በዚህ መልኩም ፍርድ ቤቱ  ባደረገው የማስረጃ ምዘና ፓርቲው ያቀረበው መስራቾቹን  የመዘገበበት ሰነድ የቦርዱን የማጣራት ግኝት የሚያስተባበልና ዋጋ የሚያሳጣ ማስረጃ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል አይደልም ብሏል።

በመሆኑም ምርጫ ቦርዱ ፓርቲውን በመሰረዝ የሰጠው ውሳኔ አግባብ ነው ሲል የኦሮሞ ነጻነት ዲሞክራሲያዊ ግንባር ያቀረበው ክስን ውድቅ አድርጓል።

 የምርጫ ቦርዱን ውሳኔ ሊሻር አይገባም በማለትም አጽንቶታል።(ኤፍ ቢ ሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top