Connect with us

“አትምጡብኝ?!”

"አትምጡብኝ?!"

ነፃ ሃሳብ

“አትምጡብኝ?!”

“አትምጡብኝ?!”

(የአርቲስት ሙኒት መስፍን ~  ተማፅኖ)

እባካችሁን እዚህ ስትመጡ ለመሳደብ ከሆነ ባትመጡ ይመረጣል። እኔንም ፣ ሌሎችንም ፣ ህዝብንም ፣ በዘር ፣ በሃይማኖት ወዘተ ለመሳደብ የምትመጡ ከሆነ ብሎክ ወደማድረግ ልጓዝ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ብሎክ ላለማድረግ እጥራለሁ። ግን አሁን ትንሽ ደከመኝ። ሰለቸኝ።

ስድብ ፣ መነታረክ ፣ ሰውን ማሳነስ ፣ ጠብ ለመቀስቀስ ፣ ወዘተ ከሆነ አላማው ወይ አትምጡ አለበለዚያ ደህና ሁኑ አያልኩ ብሎክ ለማድረግ ወስኛለሁ። ያደክማል። ነገር ነገር ነገረኝነት። አብሮ ለማዘን ሳይሆን ፣ መፍትሄ ለማምጣት ሳይሆን ፣ ዝም ብሎ ጊዜ ለማባከን ፣ ስድብ ለመሳደብ ፣ ብልግና ተናግሮ ለመሄድ … ግድ የለም ፣ ይቅርብን!

መንግስት አይደለሁም። እንደናንተ ሰው እንጂ። ሁሉንም ነገር በሁሉም ሰዓት የማወቅ ኃይል የለኝም። ሳውቅ ማውቀውን እና የተሰማኝን እፅፋለሁ። ግን ስለሁሉም ነገር ሁሌም አልፅፍም… ማሺን አደለሁም። 

ጋዜጠኛም አይደለሁም! ሙሉ ሰዓቴንም ፌስቡክ ላይ እና ዜና ፍለጋ ላይም አይደለሁም። ተቋም አይደለሁም።  እንደናንተ ፣ ሥራ ፣ ልጆች ፣ ህይወት ፣ ወዘተ መሃል ነኝ ።  እንደናንተ ምችለውን አደርግና ፣ ምለውን እልና ፣ ምሠራውን እሠራና ቀኑ ሲያልቅ በሰላም ያዋልክኝ በሰላም አሳድረኝ ብዬ እተኛለሁ። ልክ እንደናንተ።

አብሮ ማዘን። ሰላም ይሁን ማለት። ወደ ሰላም የሚወስዱን መፍትሄ የሚመስለንን ሃሳቦች ላይ መወያየት ፣ ወዘተ ከሆነ አሪፍ! ሌላው ይቅርብን።

ለመሪዎቻችን ፣ ለሁላችን ልቦና ይስጠን።

ሰላሙን ያብዛልን።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top