Connect with us

የኤርትራ ጦር ይወጣል!

የኤርትራ ጦር ይወጣል!
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

የኤርትራ ጦር ይወጣል!

የኤርትራ ጦር ይወጣል!

የህወሓት ጁንታ በሰሜን  ዕዝ ላይ የፈፀመውን ጥቃት ተከትሎ የኢትዮጵያን ድንበር ይዞ  የነበረውን የኤርትራ ጦር ለማስወጣት የአገሪቱ መንግስት መስማማቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ  ትላንት ወደ አስመራ አቅንተው ከኤርትራው ፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ ባደረጉት ውይይት ድንበር ሲጠብቅ የነበረው የኢትዮጵያ ጦር በህወሓት መጠቃቱን ተከትሎ የኤርትራ ጦር ይዞት የነበረውን  ድንበር ለቆ ለመውጣት ከስምምነት መደረሱን አስታውቀዋል።

ይህን ተከትሎም በኤርትራ ጦር ተይዞ የነበረውን ድንበር  በኢትዮጵያ ሠራዊት እደሚጠበቅ ጠቅላይ ሚንስትሩ በመግለጫቸው አመልክተዋል ። 

ጠቅላይ ሚንስትሩ  ትላንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ አስመራ ማቅናታቸው ይታወሳል ።(EBC)

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top