Connect with us

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ
ኢት ንግድ ባንክ

ዜና

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ፈፀመ

  • ሀገር አቀፍ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት ከመጋቢት 15 እስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም ይካሄዳል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ ግዢ ፈጽሟል፡፡ ባንኩ የቦንድ ግዢውን የፈጸመው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ እና በታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዛባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት አዘጋጅነት  ከመጋቢት 15 አስከ 25 ቀን 2013 ዓ.ም በሚካሄደው ሀገር አቀፍ የቦንድ ሽያጭ ሳምንት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ነው፡፡

“ግድባችን የሀገራችን አንድነት መገለጫ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረውን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መሠረት የተጣለበትን 10ኛ ዓመት በማስመልከት ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካካል አንዱ የሆነውን የቦንድ ሽያጭ መርሀ-ግብር  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ፍቃዱ ደግፌን ጨምሮ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በይፋ አስጀምረዋል፡፡

አቶ ፍቃዱ በመክፈቻ መርሀ-ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር እንዳሉት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 79 በመቶ መድረሱን ጠቅሰው ይህም መላው ህብረተሰብ በገንዘብ፣ በጉልበቱ እና በእውቀቱ ባደረገው ድጋፍ የመጣ ውጤት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ምክትል ገዢው አክለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመላ ሀገሪቱ ባሉት በርካታ ቅርንጫፎች ቦንድ በመሸጥ ህብረተሰቡ ለግድቡ ድጋፍ እንዲያደርግና የቁጠባ ባህሉን እንዲያዳብር ከፍተኛ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል፡፡

ከመጋቢት 15 እስከ 25 ቀን 2013 በሚደረገው መርሀ ግብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ  ቅርንጫፎች እንዲሁም ድንኳኖችን በመትከል ከ50 ብር ጀምሮ የቦንድ ሽያጭ እንደሚካሄድ አቶ በፍቃዱ ገልፀው ህብረተሰቡ ቦንድ በመግዛት በታላቁ ህዳሴ ግድብ ላይ በድጋሜ አሻራውን እንዲያሳርፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የገዛውን የ200 ሚሊዮን ብር ቦንድ በፕሮግራሙ ላይ ያስረከቡት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቅርንጫፍ እና የዲጂታል ባንኪንግ ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ፍቅረሥላሴ ዘውዱ  ባደረጉት ንግግር ባንኩ ለግድቡ ዋነኛ የፋይናንስ አቅራቢ እንደሆነና እስካሁንም የ101 ቢሊዮን ብር የፋይናስ አቅርቦት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

የቦንድ ሽያጭ መርሀ-ግብሩን የተሳካ ለማድርግ ባንኩ ከ1,660 በላይ በሆኑት ቅርንጫፎቹ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የገለጹት አቶ ፍቅረሥላሴ በቀጣይም ባንኩ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፍፃሜ ለማድረስ የሚያስችለውን የፋይናንስ አቅርቦት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡

በቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሄራዊ ምክር ቤት ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አረጋዊ በርሔ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ላበረከተው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ እንደ ሀገር የሚጠበቅበትን የሚወጣ ባንክ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሉአላዊነትና የፍትሀዊነት ጥያቄ፣ የአንድነት ጉዳይ እና ወደተደላደለ እድገት አሻጋሪ ፕሮጀክት መሆኑንን የተናገሩት ዶ/ር አረጋዊ  የግድቡ ፕሮጀክት እንዲከሽፍ በውስጥም በውጪም ያሉ ተቃራኒ ሀይሎች እየተፈታተኑን ይገኛሉ ብለዋል፡፡ “ያለንበት ሁኔታ በጣም ከባድ ነው” ያሉት ዶ/ር አረጋዊ ትብራችንን ልክ አያቶቻችን እንዳደረጉትና አድዋ ላይ የውጭ ወራራ ኃይልን እንዳሸነፉት በማድረግ ለማሸነፍ መዘጋጀት አለብን ብለዋል፡፡  በርትተን ግድቡን እንደጀመርነው እንጨርሰዋለንም ነው ያሉት ዶ/ር አረጋዊ ፡፡

ያለምንም የውጪ እርዳታና ድጋፍ በህዝብና በመንግስት የጋራ ትብብር በሀገራችን የውስጥ አቅም በመገንባት ላይ ላለው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ባለፉት 10 ዓመታት ከህብረተሰቡ እና ከተቋማት በስጦታ፣ በቦንድ ግዥ እና በአጭር የጽሁፍ መልእክት እስካሁን ከ14∙8 ቢሊዮን ብር በላይ እንደተሰባሰበ ለማወቅ የተቻለ ሲሆን የህዝብ ባንክ የሆነው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቁጠባ ከህብረተሰቡ ከሚያሰባስበው ገንዘብ ግድቡ በስኬት እንዲጠናቀቅ 101 ቢሊዮን ብር  ማቅረቡም ነው የተገለፀው፡፡(ኢት ንግድ ባንክ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top