Connect with us

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ አርተፊሻል ዝናቡ፤ እባክዎትን አርተፊሻልም ቢሆን ሰላም ያውርዱልን፤

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ አርተፊሻል ዝናቡ፤ እባክዎትን አርተፊሻልም ቢሆን ሰላም ያውርዱልን፤ እርስዎ ደመና ታግለው ሰማይን ሲያስፈስሱ፤ ሌሎች የደሃ ደም እያፈሰሱ ነው
Ethiopian press agency

ነፃ ሃሳብ

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ አርተፊሻል ዝናቡ፤ እባክዎትን አርተፊሻልም ቢሆን ሰላም ያውርዱልን፤

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ አርተፊሻል ዝናቡ፤ እባክዎትን አርተፊሻልም ቢሆን ሰላም ያውርዱልን፤

እርስዎ ደመና ታግለው ሰማይን ሲያስፈስሱ፤ ሌሎች የደሃ ደም እያፈሰሱ ነው

(ስናፍቅሽ አዲስ -ድሬቲዩብ)

ጠቅላዩ መቼም ሲናገሩ ጆሮ ገብ ናቸው፡፡ አይጠገቡምና ሳልሰለች ሰማኋቸው፡፡ ብዙ ፍሬ ያለው ነገር ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይና ፓርቲያቸው መተዋወቃቸውን እንድንጠይቅ የሚያደርገን እንዲህ ያሉ ሩቅ ተሻጋሪ ሀሳቦቻቸው ናቸው፡፡

ጠቅላዩ ዛሬ በሳይንስ ዘርፍ የደረስንበትን ነግረውናል፡፡ ዓለም ሰው ሰራሽ ዝናብን እንደሚያዘንብ ለማያውቅ ንግግራቸው ጥጋብ ይመስለው ይሆናል፡፡ የፕሮጀክቱ ሙከራዎች በጎጃምና በሰሜን ሸዋ ዞን ሰሞኑን ዝናብ እንዲጥል ማድረግ መቻሉንና የደመና ስብስብን ወደ እርጥበትና ውሃ መቀየር መቻሉን ነግረውናል፡፡

ስለ ደመና ዘር አንዳች እውቀት የሌለው ማህበረሰብ አንቂ ሲሳለቅ በመዋሉ ደስ ብሎኛል፡፡ እርስዎ የገቡበት ቤት የነበሩ ታላቅ ንጉሥ ውሃ በመዘውር ሲያወጡ እንዴት ቅንጡ ነው ተብለው ተስቆ ነበር፡፡ ሆቴልን በልምምጥ በለመደች ሀገር፣ ስልክ የሴጣን ስራ ባላገጠ ማህበረሰብ መካከል ደመናን ማስዘነብ ማላገጫ ቢያደርግ አይገርምም፡፡

ይልቁንም ለወደፊቱ ለእርስዎም ልንገርዎ ለሰው የማይመስል ነገር አይናገሩ፤ ይሄ ህዝብ በድሮውን ድል እስኪያደርጉ ለየሽማግሌው ተው ቆረጣ አንዋጋም ብለው ሲልኩበት የሳቀ መሆኑን እየረሱ ዳግም በደመና አሳቁት፡፡ ሲሆን እንዴት የሚል ማህበረሰብ እንኳን የእርስዎን ደመና አምኖ ሊቀበል፤ ከገባንበት ሁኔታ አንጻር እንደ አርተፊሻል ዝናቡ ሁሉ አርተፊሻል ሰላም ብናገኝም አንጠላም፡፡ ሀገር ለመልማት በምታደርግው ጥረት ልዩነት ባይኖረንም ብልጽግናችን በሰላም በኩልም ቢሳካለት እንመርጣለን፡፡

ጠቅላዩ አርተፊሻል ዝናብ ለማዝነብና ሰማይ ውሃ እንዲያፈስ ለማድረግ በቴክኖሎጂ መከራቸውን ቢያዩም የደሃ ደም በሚያፈሱ ድራማ ሰሪዎች ግን ተከበዋል፡፡ ሥርዓቱ መሪውን አይመስልም የምንለውም ለዚሁ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማው ላይ ከተናገሩት ንግግር ብዙውን ስናደምጠው መዋቅሩ በራሱ ኮተታምና እንቅፋት እንደሆነ የሚያሳየን ነገር አለ፡፡

በኢትዮጵያ አርተፊሻልም ቢሆን ውሎ ማደር የሚያስችል ሰላም ያስፈልጋል፡፡ መንግስትም በሰላም አበልጽጎ ወደ ጥሪት ብልጽግና ቢወስደን የሁላችንም ምርጫ ነው፡፡ ሰላም ያላትን ዋጋ ከምንም በላይ የተረዳ ህዝብ አለን፡፡ ሰላምን አስቀድሞ ከሰላም የሚበልጥ ነገር የለም የሚል መንግስትና ፖለቲከኛ ያስፈልገናል፡፡ ዝናቡ ሰው ሰራሽ ቢሆንም ሰው ሰላም ካልሆነ ጎርፍ እንጂ እህል አይሆንም፡፡ የተፈጥሮ ጸጋውን ብናለማው ጎብኚ መምጣት የሚችለው ሀገሩ ሰላም ውሎ ሰላም ሲያድር ነው፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top