Connect with us

የዝናቡ ነገር!…

የዝናቡ ነገር!...
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የዝናቡ ነገር!…

የዝናቡ ነገር!…

(ዶ/ር ያሬድ አግደው)

አንዳንድ ጊዜ ያለማወቅ በጎ ነው። ልክ እንደ ዛሬው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ስትዝናና ትውላለህ። “ዝናብ በጎጃም እና በሰሜን ሸዋ እኛ ነን ያዘነብነው” የሚለው ንግግራቸው በቃ ብዙ ሰው አስቆታል። ያሳዝናል! ለመሆኑ ሰው ሰራሽ ዝናብ እንዴት ነው ሚዘንበው? ኢትዮጲያ ውስጥ ያለው artificial intelligence ምን ደረጃ ላይ ደርሷል? ብሎ የሚጠይቅ አዕምሮ አለመኖሩ ገራሚ ነው!

እኔ በግሌ በዚህ ተቋም (AI) በህክምና ጥሩ ነገሮች እየተሰሩ እንደሆነ አውቃለው። በአመጋገብ ስረዓት ፣ በጭንቅላት ቀዶ ህክምና (ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለፁት) ፣ በቆዳ ህክምና ፣ በጡት ካንሰር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ጥሩ ደረጃ ላይ እየደረሱ እንደሆነ በቂ መረጃ አለኝ።

የዝናቡስ ነገር?

ሰው ሰራሽ ዝናብ ለማዝነብ ብዙ የቴክኖሎጂ አቅም የሚጠይቁ መንገዶች ቢኖሩም ቀላሉ የሆነው በአካባቢው የሚገኘውን ደመና በመጠቀም የሚደረግ “Cloud seeding” የሚባለው መንገድ ነው። Cloud seeding የተለያዩ ኬሚካሎችን በመጠቀም ደመና በዝናብ ወይም በበረዶ መልክ ወደ መሬት እንዲወርድ ማድረግ ሲሆን ለምሳሌ silver Iodide, potassium iodide, እንዲሁም Dry ice (ብናኝ በረዶ) በመጠቀም ሰው ሰራሽ ዝናብ ማዝነብ ይቻላል። 

በቅርብ የተደረጉ ግኝቶች እንደሚያሳዩት የምግብ ጨው በደመና ላይ በመጠቀም የተሻለ ዝናብ ማዝነብ እንደሚቻል ያስረዳሉ። እንግዲህ የእኛን ሀገር ዘዴና ደረጃ እርሳቸው እንዳሉት ሲመረቅ እናየዋለን።

የከርሞ ሰው ይበለን!

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top