Connect with us

#ሰበር_ዜና

#ሰበር_ዜና
ጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት

ዜና

#ሰበር_ዜና

#ሰበር_ዜና

የኢትዮጵያ መንግስት የመጨረሻ ጥሪ ለህወሓት አመራሮች እና ለትግራይ ህዝብ!

የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ የሚኖሩ ሰላማዊ ዜጎች በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ወደቀደመ ኑሮአቸው እንዲመለሱ ጥሪ ሲያቀርብ የህወሓት ሰዎች በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን እንዲሰጡ ጠይቋል።

የጠ/ሚኒስትር ፅ/ቤት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ እንደጠቆመው በወንጀል ተግባራት ጉልህ ተሳትፎ የሌላቸው እና የፍርድ መያዣ ከወጣባቸው የወንጀል ተጠርጣሪዎች በስተቀር ሌሎች የክልሉ ነዋሪዎች ከአጥፊው ቡድን ራሳቸውን ለይተው ወደሰላማዊ ኑሮአቸው እንዲመለሱ አሳስቧል።

ወደሰላማዊ ኑሮ የሚመለሱ ወገኖች የትኛውም አይነት የህግ ተጠያቂነት እንደማይኖርባቸውም መግለጫው አትቷል።

በሌላ በኩል የጥፋት ቡድኑ አካል ሆነው በተፈፀመው ወንጀል ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው እና በፍርድ መያዣ ትዕዛዝ የወጣባቸው የህወሓት ወታደራዊና ፓለቲካዊ አመራሮች በሰላም እጃቸውን እንዲሰጡ የጠ/ሚኒስትሩ ፅ/ቤት  በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል።(ሙሉ መግለጫው ተያይዟል)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top