Connect with us

ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚከበረው ሰው አክብሮ የተከበረ ሥራ ሠራ፡፡

ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚከበረው ሰው አክብሮ የተከበረ ሥራ ሠራ፡፡ አብደላህ ሸሪፍ ሀረርን የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡
ሄኖክ ስዩም

ነፃ ሃሳብ

ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚከበረው ሰው አክብሮ የተከበረ ሥራ ሠራ፡፡

ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ የሚከበረው ሰው አክብሮ የተከበረ ሥራ ሠራ፡፡

አብደላህ ሸሪፍ ሀረርን የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡

ከሄኖክ ስዩም በድሬ ቲዩብ

ስለ ሰውዬው ምን እንመሰክራለን፡፡ በጨለማው ዘመን ብርሃን ሆነዋል፡፡ ሀገር ከሶሻሊዝም ወደ ካፒታሊዝም ሥርዓት ገባች ተብሎ ህዝቤ ንግድና መሬት መቀራመትን የብልጽግናው ጎዳና ባደረገበት የብልጦች ሳምንት እንደ ሞኝ ሀገር የሚያበለጽግ ትውልድ የሚያስከብር ሥራ ሰርተዋል፡፡

እንደ እብድ የታዩበት ጠባይ ሀገር የጎደላትን የመሙላት አበሳቸው ነበር፡፡ ብቸኛው ባለ ግል ሙዚየም፡፡ ብቸኛው ገንዘብ ለማስላት ተምረውና ተቀጥረው ቅርስ ሰብሳቢ በመሆን ኮተታም የሚል ስም የተለጠፈባቸው፡፡ ዛሬ ግን በቅርስ ስብስቡ ሀገር የምትኮራበት ሙዚየም ባለቤት ሆነዋል፡፡ የራስ መኮንንን ሀውልት በጣለችው ከተማ ከንጉሠ ነገሥት ምኒልክ እስከ ዛሬ የቆየ የታሪክ አሻራዎችን በክብር አስቀምጠዋል፡፡ ቅርስ መግዛትና ማኖር ብቻ ሳይሆን ቅርስ መጠገንን የተካኑ ባለሙያ ናቸው፡፡ ሌላ ህይወት የላቸውም፡፡ ህይወታቸውን በኖሩለት የቅርስ ሰብሳቢነት ሙያ ሀገር ሀብቷን ከተበተነበት ወደ አንድ ቤተባዊ ዓለም ያከበረው ሙዚየም አስገብተውታል፡፡

ይሄ ወንጀል ሆኖ ብዙ ማስፈራሪያዎች ሲደርሳቸው ኖሯል፡፡ የፌውዳሉን ቅራቅንቦ ሰብሳቢ ተደርገው መውጫ መግቢያ አጥተዋል፡፡ የቀድሞ ሥርዓት ናፋቂ የሚለው አሽሙር ደርሶባቸዋል፡፡ ደመወዛቸው ተቋርጧል፡፡ የሚወዷቸውም ቢሆኑ ምን ሊያደርገው ነው? ከማለት አልቦዘኑም፡፡

ሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ እኒህን ሰው ነው ያከበረው፤ ሊከበር የሚገባውን ማክበር ያስከብራል፡፡ ዛሬ በሀረር ከተማ ከሚገኙ አራት ሙዚየሞች አንዱ አብደላ ሸሪፍ ሙዚየም ነው፡፡ በቅርስ ስብስቡ ደግሞ መንግሥት ጭምር የኔ ከሚላቸው በርካታ ሙዚየሞች በብዙ እጥፍ ይበልጣል፡፡ በሰበሰባቸው ቅርሶች የታሪክና የብዝሃነት ተለያይነትም እንዲሁ፡፡

ወታደራዊው ሥርዓት ሲወድቅ ቅርስ የሚሰበስበው የአብደላ ሸሪፍ ሙዚየም አንድ ብሎ በይፋ ተነሳ፡፡ ዛሬ አስራ አምስት ሺህ የሚጠጉ የቅርስ ስብስቦች አሉት፡፡ እስከ 3000 ሺህ ዘመን እድሜን ያስቆጠሩ፡፡

ሀሮማያ ለአብደላ ሸሪፍ የክብር ዶክትሬት ሰጥቷል፡፡ ለሚገባቸው የሚገባውን በማድረጉ ክብሩ ለራሱም ነው፡፡ እኛ ግን የምናከብረውን ስላከበረልን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top