Connect with us

የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል  ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. ተሸጠ

የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. ተሸጠ
የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

ዜና

የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል  ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. ተሸጠ

የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል  ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. ተሸጠ

በፍል ውሃ አገልግሎት ድርጅት ስር ሲተዳደር የቆየው የላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል ለቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. በብር 54,525,000.00 (ሃምሳ አራት ሚሊዮን አምስት መቶ ሃያ አምስት ሽህ) ተሸጠ፡፡ የሽያጭ ስምምነቱ መጋቢት 3 ቀን 2013 ዓ.ም. በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተከናውኗል፡፡

በሽያጭ ስምምነት ሰነዱ ላይ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በኩል የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካኤል እና በቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. ወገን ደግሞ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ መሐመድ አብዲ አህመድ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡

ሪዞርት ሆቴሉ ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዛወሩ ከተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ቢሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሁቴሉን በተሻለ ሁኔታ በማልማት የአካባቢውን ወጣቶች የበለጠ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ እንዲችል በሽያጭ እንዲተላለፍለት የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤትን ጠይቆ በተፈቀደለት መሠረት ዝውውሩ በቢፍቱ አዱኛ ቢዝነስ አ.ማ. በኩል ሊፈጸም እንደቻለ የሽያጭ ውሉ ያስረዳል፡፡

 የሽያጭ ዋጋውን ከፊርማው በፊት ገዥው ሙሉ በሙሉ ገቢ ማድረጉ ታውቋል፡፡

የሪዞርት ሆቴሉን ቋሚና ኮንትራት ሠራተኞች በሙሉ ገዥው ተረክቦ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ እና በኅብረት ስምምነት እንዲሁም የሙያ ደህንነትና ህግጋት ወይም መመሪያዎች መሠረት እንደሚያስተዳድር በውሉ ላይ ተጠቅሷ፡፡

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ኃይለ ሚካል በፊርማ ሥነሥርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር ላንጋኖ ሪዞርት ሆቴል ታላቅ የቱሪስት መስህብ ባለው የዝዋይ ሐይቅ ዳርቻ የሚገኝ መሆኑን  ጠቅሰው፣ አክሲዮን ማኅበሩ የቦታውን ደረጃ በሚመጥን መልኩ ይዞታውን አልምቶ ሆቴሉን  ተወዳዳሪ በማድረግ የአካባቢውን ማኅበረሰብና ሀገርን የበለጠ ተጠቃሚ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል፤ ለዚህም ኤጀንሲው ተገቢውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ (የመንግስት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ)

 

Continue Reading
Advertisement News.et Ad
You may also like...
Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top