Connect with us

“በኦሮሚያ ጫናዎች እየደረሱብን ነው”  ኢዜማ

#የኢዜማ_መግለጫ
ሸገር ራዲዮ

ነፃ ሃሳብ

“በኦሮሚያ ጫናዎች እየደረሱብን ነው”  ኢዜማ

“በኦሮሚያ ጫናዎች እየደረሱብን ነው”  ኢዜማ

– “በ52 የኦሮሚያ ወረዳዎች እጩዎችን ማቅረብ አልቻልንም፣”

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትኅ (ኢዜማ) በኦሮሚያ ያለው ድባብ መጪው ምርጫ ፍትኃዊ ለማድረግ የማያስችል ነው አለ፡፡

ኢዜማ ዛሬ በሰጠው መግለጫ፤ ኢዜማ ከምርጫው እንዲወጣ በኦሮሚያ የተለያዩ ጫናዎችን እየደረሱበት ነው ብሏል፡፡

ይሁንና ፓርቲው ሁሉንም ተቋቁሞ ይቀጥላል፤ አሁን ባለው ሁኔታና በሚታየው የተግባር እንቅስቃሴ፣ ብልፅግና ኦሮሚያ ላይ ብቻውን ለመወዳደር ቆርጦ የተነሳባቸው ብዙ መገለጫዎችን እያየን ነው ሲል ፓርቲው ተናግሯል፡፡

በመላው አገሪቱ 1 ሺ 385 እጩዎችን ማስመዝቡን የተናገረው ኢዜማ በ52 የኦሮሚያ ወረዳዎች እጩዎችን ማቅረብ አልቻልኩም ብሏል፡፡

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እጩ ማስመዝገብ ያልቻልኩበት አካባቢ በልዩ ሁኔታ እጩዎቹን ማስመዝገብ እንድችል ሲል ኢዜማ ቦርዱን ጠይቋል፡፡

ኢዜማ በኦሮሚያ ላሉ የምርጫ ወረዳዎች ባቀረብኳቸው እጩዎቼ ላይ ከምርጫ ጀምሮ ዛቻና ማስፈራሪያ እየደረሰባቸው ነው፤ የፀጥታው ሁኔታም እጩ ማስመዝገብ የማይቻልባቸው ቦታዎች አሉ፤ እጩ ሆነው ከተመዘገቡ በኋላ እንዲሰረዙ ወይም ራሳቸውን እንዲያገሉ ማስፈራሪያ ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡

እጩ ሆነው ከተመዘቡ በኋላም ያለመከሰስ ሙሉ መብት እንዳላቸው እየታወቀ እስርና ድብደባ ደርሶባቸዋል ሲል ፓርቲው በዛሬው መግለጫ ተናግሯል፡፡

መንግስት በምስራቅ ወለጋና በምዕራብ ወለጋ እንዲሁም ቤንሻንጉል ክልል ምርጫን ለማካሄድ የሚያስችል የፀጥታ ሁኔታ መፍጠር አለበት ከዚህ በተጨማሪ በየክልሉ ላሉ ካድሬዎችና የፀጥታ መዋቅሮች እንዳለፉት ምርጫዎች የይስሙላ ምርጫ እንዲደረግ የሚሞክሩ ካድሬዎችም ከማዋከብና ከማስፈራራት እንዲቆጠቡ በይፋ ትዕዛዝ ይሰጥልኝ ሲል ጠይቋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በሰላማዊ መንገድ ከተሸነፍን እናስረክባለን እያሉ የምርጫው ሒደት ግን ከጅምሩ ችግር እየገጠመው በመሆኑ አስቸኳይ ማስተካከያ በካድሬዎች በኩል እንዲደረግ ትዕዛዝ እንዲሰጡልንም ሲል ፓርቲው ጠይቋል፡፡(ሸገር ራዲዮ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top