Connect with us

 5 ሺ 794 ለሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት ተሰጣቸው

5 ሺ 794 ለሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት ተሰጣቸው
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት

ዜና

 5 ሺ 794 ለሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት ተሰጣቸው

 5 ሺ 794 ለሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለቤት መስሪያ የሚሆን መሬት ተሰጣቸው

 የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት  ከ5ሺህ 700 በላይ ለሆኑ ሞዴል አርሶ አደሮች በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በተለያዩ ከተሞች ላይ ለቤት መስሪያ ቦታ የሚሆን የመሬት ርክክብ እያካሄደ ነው።

በመርሀ ግብሩ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እና ሞዴል አርሶ አደሮች ተገኝተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ከዚህ ቀደም በነበሩት ስርዓቶች አርሶአደሩ በተለያዩ ምክንያቶች አላግባብ መሬቱን ሲነጠቅና ለከፋ ችግር ሲጋለጥ መቆየቱን አንስተዋል።

አሁን ላይ ግን አርሶ አደሮቹ ህጋዊ በሆነ መልኩ ተደራጅተው የቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው መደረጉን ነው ርዕሰ መስተዳድሩ መናገራቸውን ፋና ዘግቧል፡፡

ኦቢኤን   በበኩሉ በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን በመኖሪያ ቤት ማህበር ለተደራጁ  ሞዴል አርሶ አደሮች፣ ሴቶችና ወጣቶች 5 ሺ 794 ናቸው ብሏል፡፡

የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የከተማና ቤቶች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ ጌታቸዉ የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታዉ የሚሰጠዉ በሰንዳፋ፤ በኮሎቦ፣ በሱሉልታ፣ በሰበታ፣ በገላንና በዱከም ከተሞች ዉስጥ መሆኑን ተናግረዋል።

የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ ካርታ የመስጠት ሥነ ሥርዓትም ከስድስቱም ከተሞች የተዉጣጡ አርሶ አደሮች፣ ሴቶችና ወጣቶች በተገኙበት በበራክ ወረዳ ሰንዳፋ በኬ ከተማ በመካሔድ ላይ ይገኛል።

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top