Connect with us

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም የ2 በመቶ፣ በአፍሪካ የ10 በመቶ፣ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም የ2 በመቶ፣ በአፍሪካ የ10 በመቶ፣ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል - የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት
Ethiopian Broadcasting Corporation

ዜና

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም የ2 በመቶ፣ በአፍሪካ የ10 በመቶ፣ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል

በኮሮናቫይረስ የመያዝ ምጣኔ በዓለም የ2 በመቶ፣ በአፍሪካ የ10 በመቶ፣ በኢትዮጵያ የ12 ነጥብ 8 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል – የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት 

      ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ  ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፣

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ስርጭት አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ ነው ነው ሲል የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስጠነቀቀ፡፡

ኢንስቲትዩቱ እንዳለው ባሳለፍነው ሳምንት (ከየካቲት 22 እስከ 28/2013) በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ቁጥር የ2 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል።

በአፍሪካም በዚሁ ሳምንት በቫይረሱ የመያዝ ምጣኔ በ10 በመቶ የጨመረ ሲሆን በተለይ በኢትዮጵያ ደግሞ ከዚህም አልፎ በ12 ነጥብ 8 በመቶ አድጓል፡፡

በትናንትናው ዕለት የኮቪድ-19 የላቦራቶሪ ምርመራ ካደረጉ 7 ሺ 819 ሰዎች መካከል 1 ሺ 543ቱ የኮቪድ-19 ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ይህ ማለት ከተመረመሩት 100 ግለሰቦች 20 ያህሉ ወይም 20 በመቶ ኮሮናቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ከፍተኛ ቁጥር የተመዘገበው በነሐሴ ወር 2012 ዓ.ም ማህበረሰብ አቀፍ ንቅናቄና የምርመራ ዘመቻ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ ያለው የፅኑ ሕሙማን ቁጥርም ትናንት 438 ደርሷል፡፡

ይህ ቁጥር ኮቪድ-19 ወደ አገሪቱ ከገባ ጀምሮ ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በትናንትናው እለት ብቻ 15 ግለሰቦች በኮቪድ-19 ምክንያት ሕይወታቸውን ያጡ ሲሆን የሟቾች አጠቃላይ ቁጥር 2 ሺ 446 ደርሷል፡፡

የቫይረሱ ስርጭት በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች በፍጥነት እና በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተዛመተ መሆኑን ተገለጸው ኢንስቲትዩቱ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ማስክ በመልበስ እንዲሁም አካላዊ ርቀታቸውን እና የእጃቸውን ንጽህና በመጠበቅ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያደርሰውን ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት በጋራ እንዲከላከሉ ኢንስቲትዩቱ ጥሪውን አቅርቧል፡፡(ኢቢሲ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top