Connect with us

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ
ሸገር ራዲዮ

ዜና

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ

የቀድሞ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም በዋስ ተለቀቁ

እንዲሁም ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የትግራይ ክልል የቀድሞው ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት በዋስ ከእስር እንዲወጡ ተወሰነ።

በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የክስ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን በፍ/ቤት ሲከታተሉ የነበሩት የክልሉ የቀድሞው  ጠ/ፍ/ቤት ፕሬዝደንት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና በመዝገቡ 8ኛ ተጠርጣሪ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ ዐቃቤ ህግ ለከፈትኩት የምርመራ መዝገብ  የሚያስጠረጥር በቂ ማስረጃ  ባለማግኘቴ  በዋስ  ይለቀቁ  ሲል  ለፍ/ቤት አመልክቷል።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋን ጨምሮ አቶ ሰሎሞን ኪዳኔ ቅዱሳን ነጋና ሌሎች የመዝገቡ ተጠርጣሪዎች ጉዳይ በቀዳሚ ምርመራ እንዲታይ ዐቃቤ ህግ  ለፍ/ቤቱ  አመልክቷል።

ጉዳዪን የተከታተለው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት አቃቤ ህግ ባቀረበው መሠረት ወ/ሮ ሀሪቲ ምረተአብ እና አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ እያንዳንዳቸው  በ30000 ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ አዟል።

አቶ ስብአት ነጋን ጨምሮ የመዝገቡ ሌሎች ተጠርጣሪዎች ጉዳያቸው በቀዳሚ ምርመራ መዝገብ  እንዲታይና  እስከዛው  በማረሚያ  ቤት  እንዲቆዩ ፍ/ቤቱ  ዛሬ ትዕዛዝ ሰጥቷል።(ሸገር ራዲዮ)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top