Connect with us

ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ
የገቢዎች ሚ/ር

ዜና

ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድን ለመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

የጉምሩክ ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ የፍትህ አካላት ጋር የጸረ-ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ንቅናቄ አካሂዷል፡፡

ለሁለት ቀናት በአዳማ ከተማ በተካደው መድረክ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ኮንትሮባንድ በዘርፈ ብዙ መንገድ ማህበረሰብን የሚጎዳ፤ ለሀገር አለመረጋጋት መንስኤ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ ውይይቱ የኮንትሮባንድን ጉዳት ለማስገንዘብ የንቅናቄ መድረኮች በተለያዩ የኢትዮጵያ ከተሞች እንደሚካሄዱ ጠቁመዋል፡፡

ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ በማሳጣት፣ ህጋዊ ነጋዴዎችን ከገበያ በማስወጣትና ኢንቨስትመንት እንዳይስፋፋ በማድረግ ሀገራችን የጀመረችውን የብልጽግና ጉዞ ያደናቅፋል ያሉት የኢንተለጀንስና ኮንትሮባንድ መከላከል  ዳይሬክተር አቶ ተገኔ ደረሰ ፓለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳቶችን በማድረስ ለግጭት መንስኤ በመሆን የአገር ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ ችግሩን የሚያባብሱ ሁኔታዎችን በመቆጣጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ በኮሚሽኑ የተከናወኑ ተግባራትን ለመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን በተሰሩ በመከላከል ስራዎችም በህገወጦች ምክንያት ባለፉት ስድስት ወራት መንግስት ሊያጣው የነበረን 19.313 ቢሊየን ብር ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡

ኔትወርኮችን በመበጣጠስና የስነ-ምግባር ችግር ያለባቸው ሰራተኛና አመራሮች ላይ እርምጃ በመውሰድ የህግ ማሻሻያዎችና የግብይት ስርዓቱን ለማሻሻል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የተናገሩት አቶ ተገኔ በቀጣይ ለፍትህ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር፣ ለመከላከል ስራው የሚያግዙ ግብዓቶችን በሟሟላት፣ የአሰራርና የህግ ማሻሻያዎችን በማደረግ፣ የጠረፍ ንግድ አሰራርን በማሻሻልና በየጊዜው የሚቀያየሩ ኮንትሮባንድ ስልቶች ላይ ጥናት በማድረግ የቁጥጥር ስራን የማጠናከር ስራ ይሰራል ብለዋል፡፡ 

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሠ መስተዳደር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ ህግን በአግባቡ በማስከበር ጥቂቶችን ብቻ ጠቅሞ አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል ለጉዳት የሚያጋልጥ በመሆኑ በጋራ ልንከላከለው ይገባል ብለዋል፡፡

የገቢዎች ሚነስቴር የህግ ተገዢነት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘመዴ ተፈራ ጉዳዩ የብዙ አካላትን ትብብር የሚፈልግ በመሆኑ በቅንጅት በመስራት ጉዳቶችን በመቀነስ ለልማት የሚውለው ገቢ እንዲሰበሰብ በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር አቶ መላኩ ፈንታ በበኩላቸው የሀገር ደህንነትና ጸጥታን ለማስጠበቅ የፌደራል ፖሊስ አባላት እስከ ህይወት መስዋትነት በመክፈል እየሰሩ መሆኑን ተናግረው በተለይ ወደ ሀገር በኮንትሮባንድ የሚገቡ እቃዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ተሳታፊዎች እየደረሰ ካለው ጉዳት አንጻር የፀረ ኮንትሮባንድና ህገወጥ ንግድ ንቅናቄው ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረው ወንጀለኞችን ተከታትሎ አስተማሪ ቅጣት ሊሰጥ እንደሚገባ ተናግረው በቅንጅት በመስራት ለውጥ ማምጣት ይቻላል ብለዋል፡፡(የገቢዎች ሚ/ር)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top