Connect with us

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2013 በጀት ዓመት መጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2013 በጀት ዓመት መጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ
በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ

ኢኮኖሚ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2013 በጀት ዓመት መጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2013 በጀት ዓመት መጀመሪያ አጋማሽ ዕቅድ አፈጻጸም ተገመገመ

በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ካሉ የልማት ደርጅቶች መካከል በትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዘርፍ የተሰማራው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የ2013 በጀት የመጀመሪያ አጋማሽ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም የካቲት 8 ቀን 2013 ዓ.ም በኤጀንሲው መሰብሰቢያ አዳራሽ  በተካሔደ ስብሰባ ተገመገመ፡፡

የግምገማ መድረኩን የመሩት የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ደ/ር እዮብ ተካልኝ ሲሆኑ፣ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ሀብታሙ ኃ/ሚካኤል፣ምክትል ዋና ዳይሬክተሮችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱና የኤጀንሲው የሥራ ኃላፊዎች፣የአየር መንገድ ግሩፕ ቦርድና የማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በበጀት ዓመቱ አጋማሽ  አብዛኛዎቹን ዕቅዶች በተሻለ መልኩ ያከናወነ ሲሆን፣  በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ ተጽዕኖ የፈጠረውን ኮቪድ-19 ተጽዕኖ ተቋቁሞ በተለይ በካርጎ ትራንስፖት እና በመልዕክት አገልግሎት በዓለም አቀፍና በአህጉራዊ የምዘና መስፈርቶች መሰረት ጥሩ አፈጻጸም ማስመዝገቡ ተገልጿል፡፡ 

በግምገማው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዓመታዊ ዕቅዱን ማከናወን የሚያስችል ደረጃ ላይ እንዳለ ለመረዳት ተችሏል፡፡

በአጋማሽ ዓመቱ ዕቅዱን ማሳካት የቻለውም ወጪውን በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ከካርጎ ትራንስፖት፣ ከመንገደኞች እና ከኤርፖርቶች አገልግሎት እንደሆነ በግምገማው ተገልጿል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ ኮቪድ-19 በአየር መንገዶች መንገደኞችን የማጓጓዝ አገልግሎት ላይ ጫና አሳድሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ መንገደኞች የሚጓዙባቸው ርቀቶችም እንዲቀንሱ አድርጓል፡፡ በመሆኑም ይህ በገቢያቸው ላይም ጫና አሳድሯል፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ እነዚህን ጫናዎች መቋቋም የሚያስችሉ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ተግባራዊ አድርጓል፡፡ ወጪ ቆጣቢ አሰራርንም በመከተል ገቢውን ማሳደግ ችሏል፡፡

በግምገማው ማጠቃለያ ላይ ክቡር ዶ/ር እዮብ ተካልኝ የአየር መንገድ ግሩፑ በአቬሽን ኢንዱስትሪው ላይ ኮቪድ-19 ያስከተለውን ከፍተኛ ጫና ተቋቁሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ስኬታማ መሆን መቻሉ የሀገር ኩራት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

ወደፊት ሁኔታው እየተሻሻለ ሲመጣም በገበያው ውስጥ የያዘውን የተወዳዳሪነት ብቃት ጠብቆ መቆየት እንዲችል በየጊዜው ሁኔታዎችን እየገመገመና አዋጭ ስልቶችን እየቀየሰ መሄድ እንደሚኖርበት አስገንዝበዋል፡፡ በግማሽ ዓመቱ ለተገኘውም ስኬት የቦርድና የማኔጅመንት አመራሮችን እና መላውን የአየር መንገድ ግሩፑን ሠራተኞች አመስግነዋል፡፡

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top