Connect with us

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ምክክር አደረጉ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ምክክር አደረጉ
አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ

ሳይንስና ቴክኖሎጂ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ምክክር አደረጉ

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በሰላም ግንባታ ዙሪያ ምክክር አደረጉ

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ካውንስል ከኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ኮንሰርቲየም ጋር በመተባበር በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያተኮረ የግማሽ ቀን ኮንፈረንስ ከትላንት በስቲያ በአአዩ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋክልቲ አዳራሽ አካሄደ፡፡

በመድረኩ ላይ ፕሮፌሰር ካሳሁን ብርሃኑ የከፍተኛ ትምህር ተቋማት ሰላምና ደህንነነት ጉዳይ ፣ ፕሮፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ – ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ስለሰላም ያላቸው ሚና፣ ዶ/ር አለማየሁ አረዳ በሰላምና ዴሞክራሲ ግንባታ የምሁሩ ሚና በሚል ርዕሰ ጉዳዮች የውይይት መነሻ ሃሳቦች ያቀረቡ ሲሆን በአወያይነት ፕሮፌሰር ሀብታሙ ወንድሙ መድረኩን መርተውታል፡፡

ፕሮፌሰር ካሳሁን በከፍተኛ የትምህር ተቋማት የሚያጋጥሙ አለመግባባቶችና ግጭቶች ምክንያታዊ የሆኑትን መቀበልና ማላሽ መስጠት፣ ምክንያታዊ ያልሆኑትንም በፍጥነት የእርምት እርምጃ በመውሰድ መጓዝ እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡

ፕሬፌሰር ብርሃኑ አበጋዝ በበኩላቸው የአለማ አቀፍ የሰላም መለኪያ (Peace index) አንስተው በቅርቡ ኢትዮጵያ ከ163 ሀገራት 131 ኛ ደረጃ ላይ እንደነበረች በማመልከት በሰላም ጉዳይ ብዙ እንደሚቀረን ጠቅሰዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ኃላ እነናይጄሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሶርያ እና የመሳሰሉ ሀገራት የሚከተሉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ሰላም በምን ምክንያት ይጠፋል የሚል ጥያቄ ያነሱት ፕሮፌሰሩ ጦርነት፣ የሀገር ኢኮኖሚ መውደቅ፣ የአካባቢ መበከል፣ የተፈጥሮ አደጋ መከሰት፣ የዝናብ እጥረት፣ የመንግስት አስተዳደር ችግሮችና የመሳሰሉ ሰላምን ሊያሳጡ የሚችሉ ናቸው ብለዋል፡፡

ዶ/ር አለማየሁ አረዳ፤ ምሁር እና የተማረ ሰው የአፍና ከንፈር ያህል ቅርበት ቢኖራቸውም አንድ አይደሉም ብለዋል፡፡ አያይዘውም ምሁር የሌላት ሀገር ጭንቅላት እንደሌለው ሰው ይቆጠራል በማለት ምሁራን የሀሳብ ምንጭ መሆናቸውን በተግባር ማሳየት እንደሚጠበቅባቸው ጠቅሰዋል፡፡

ዶ/ር አለማየሁ አያይዘውም አንዳንድ ሚዲያዎች የህብረተሰቡ ዓይንና ጆሮ ነን ይላሉ፤ ትክክል አይደለም፤ የህብረሰተቡ አይንና ጆሮ ምሁሩ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ ጥሩ ውይይት መደረጉንና ተወያዮቹ እንዲናገሩ የሚጎተጉቱ ሀሳቦች መነሳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ የሰላምና ደህንነት ካውንስል ስንመሰርት በአጭርና በረዥም ጊዜ ባለሙያዎችን ተጠቅመን ለሀገር የሚበጁ ሀሳቦችን ለማፍለቅ በማሰብ መሆኑን ነው ብለዋል፡፡  በአሉባልታና በወሬ ሰላም አይመጣም ያሉት ፕሮፌሰር ጣሰው የዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሚያወጡዋቸው ምርምሮችና ጥናታዊ ጽሑፎች ሳይንሳዊ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

በቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳቦች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በኮንፈረንሱ ላይ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛ አመራሮች፣ የአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

 

Click to comment

More in ሳይንስና ቴክኖሎጂ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top