ጌታቸው ረዳ ደመሰስኩ አለ ብሎ የሚቦርቀው ነው፤ ነገ ምርኮኛና ሟች ሲሰማ ጦርነት አያስፈልግ እንዴት ወገን በወገኑ ላይ የሚለን?
(ስናፍቅሽ አዲስ)
ጦርነት እውነት ነው ምኑም ደስ አይሉም፤ ሲኮንኑት ግን መሆን ያለበት በሁሉም ወገን ቃታ ሳቢውን ነው እንጂ ተጋጥመው ሲያሸንፉ አምበር ተጋዳላይ ሲመቱ ደግሞ ጄኖሳይድ በማለት አይደለም፡፡
ከዚህ ቀደም ጦርነት ደም አፍሳሽ ነው የሚል መልእክት ሲቀሰቅሱ የነበሩ ሰዎች ወዲያው የእኛ ያሏቸው ሰዎች ድል ያደረጉ ሲመስላቸው መልሰው እኛ እንዲህ ነን በማለት የሞራል ስንቅ አቀባይ ይሆናሉ፡፡
በእነ አቶ ስዩም መስፍን ሞት ምን አደረጉ ፖለቲከኞቹ ብለው ሞታቸውንና ግድያቸውን ስም ሲሰጡት የከረሙት ዛሬ የጌታቸው ረዳ ድምጽ ተሰማ ብለው እንዲህ ነን ማለት አሁንም ያስተዛዝባል፡፡
በሌላ በኩል ጌታቸው ረዳ እንዳሉት ምርኮኛ ጭምር እየቀለቡ አንዱን ሰው ሁለቴ እየማረኩ በውጊያ ድል እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ እውነት ከሆነ በገጠሙ ሃይሎች መካከል እንደ ዓላማው ጎራ ለይቶ መደገፍ እንጂ እንደ መርህ ለምን ብሎ ማለት ጅልነት ነው፡፡
በትግራይ ጦርነት ባይኖር ጥቅሙ ለሚሰደደው ለሚፈናቀለውና ወገናችን ብቻ አይደለም፡፡ አንድ ህዝብና አንድ ሀገር ነን፡፡ በትግራይ መድማት የሚያምርባት ኢትዮጵያ የለችም፡፡ ግን ያንን የማይፈልጉ ብዙ ወገኖች አሉ፤ ከእነዚያ አንዱ ደግሞ ህወሃት ነው፡፡
ህወሃት ነፍሷ እስኪያልፍ መከራን በትግራይ ህዝብ ጫንቃ ከመጫንና መሞቷን ካመነች ሰርዶ እንዳይበቅል ለማድረግ አትቦዝንም፡፡ የዚያ ውጤት ትርጉም አልባው ጦርነትና የሞተው ይሞታል እንጂ እኛ እጅ ሰጥተን አንዋረድም ባይነት ነው፡፡
ብዙ የጦርነት ኮናኒያን የጌታቸው ረዳ ድምጽ ተሰማ ብለው ሳኒታይዘር ከሚሉት አይከናቸው ጋር ዳግም ፍቅራቸው አገርሽቷል፡፡ ወገናችንን ለስደት ዳረገ ብለው የኮነኑት ጦርነት ድል በእኛ በኩል አለ፤ የኢትዮጵያ ሠራዊት እያለቀ ነው በሚል የእናት ጡት ነካሽ ሀሰተኛ ወሬ ልባቸው በደስታ ልትፈርጥ ነው፡፡ ነገ ደግሞ መልሰው ሌላ መራር ዜና ሲሰሙ የጦርነትን አላስፈላጊነት ይነግሩናል፡፡
እኔ ጦርነት በየቱም ወገን ቢሆን ልክና መፍትሔ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እንደ ህወሃት ተላላኪዎች ሀሳቡን የምደግፈው መንግስት እንኳን ድል አደረኩ ሲለኝ ስለሚሞት ንጽህ አስባለሁ፡፡ ጦርነትን መጥላት ከድል ውጤት ጋር የሚገናኝ አይደለም፡፡
ሰላም ምትክ የላትምና፤ ይልቁንስ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በዚህ ችግር ላይ ባለው ወገን ጣልቃ እንዳይገባ የሚያደርግ ስቆቃ በዚያች ምድር ባይኖር መልካም ነበር፡፡ ትናንት ዛሬ አይደለምና፤