Connect with us

የኢቢኤስ ቲቪ ነገር

የኢቢኤስ ቲቪ ነገር
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

የኢቢኤስ ቲቪ ነገር

የኢቢኤስ ቲቪ ነገር

(እሱባለው ካሳ)

በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በዋንኛነት በማህበራዊ ሚድያው (EBS TV) ስለተሰማው ሀይማኖታዊ ውዝግብ በግራ ቀኝ እየተሰነዘረ ያለውን አስተያየት፣ እርግማን…ከመከታተል ውጭ አስተያየት መስጠት አልፈለኩም ነበር።

አሁን ግን የነገሩ መጦዝ ስለከነከነኝ ጥቂት ነገር ልበል። እንደ አንድ የሚድያ ባለሙያ አንድ የግል ሚድያ ተቋም ቀርቶ የመንግስትም ቢሆን የራሱ የሆነ የሚመራበት የኤዲቶሪያል ፖሊሲ አለው። በዚህ ፖሊሲው የትኛውንም ሀይማኖት/እምነት የሚያንፀባርቅ/የሚወክል ምልክትም፣ አለባበስ፣ አቀራረብ…ሊከለክል ይችላል። 

ለምሳሌ የ ቢቢሲ (BBC) ኤዲቶሪያል ፖሊሲ የአንድን ሀይማኖት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያስተዋውቅ አቀራረብን ይከለክላል። 

“Where a religion or religious denomination is the subject of a religious programme or related content, the identity of the religion must be clear to the audience. Vulnerable audiences must be protected from exploitation, and religious programmes must not seek to promote religious views or beliefs by stealth…”

እንግዲህ የሚድያ ባለሙያው አስቀድሞ ይህን አውቆና ተቀብሎ መስራት ወይንም አለመስራት የእሱ ውሳኔ ይሆናል።

በእኔ እምነት ችግሩ ማተብ ማሰሩ አይደለም። ጣቢያው በይፋ ማተብ ማሰር ቢፈቅድ እንኳን የሌሎች እምነት ተከታዮች በተመሳሳይ ጥያቄ ቢያቀርቡ ወይንም ፈፅመውት ቢገኙ ሊከለክል አይችልም። ለአብነት ያህል አንድ የሙስሊም እምነት ተከታይ ሂጃብ ማድረግ መብቴ ነው ብትል የሚከለክላት አይኖርም። የካቶሊኩ፣ የኘሬቴስታንቱ እንዲሁ። 

በመጨረሻም ጣቢያው በዚህ አይነት ፉክክር ውስጥ ወድቆ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሆኖ ሊገኝ ይችላል። የተመሰረተበትን ዓላማ ይስታል። ባቀፋቸው ባለሙያዎች መካከል ያልተፈለገ ፉክክርና ግጭትም እንዲከሰት በር  ሊከፍት ይችላል። አድማጭ፣ ተመልካቹንም ይከፋፍላል። 

እናም የተነሳውን ጉዳይ በአግባቡ እንዲህ ዙሪያ ገባውን ጠለቅ ብሎ ማየት የሚድያ ተቋሙንም አጣብቂኝ ለመረዳት ያስችላል።

እናም ቅሬታ አቅራቢዋ አርቲስት በእኔ እምነት ከንቱ ውዳሴ ፍለጋ አለአግባብ ነገሩን ያጦዘችው ይመስለኛል። ምናልባትም ከጣብያው በመሰናበቷ ተበሳጭታም ሊሆን ይችላል። 

እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ቁምነገር አንድ ለሀይማኖቴ ቀናኢ ነኝ የሚል ሰው የደረሰበትን በደል ለመናገር ከስራ እስኪባረር መጠበቅ አይኖርበትም። ከዚህም አንፃር  አርቲስቷ ከስራ ስትባረር ጠብቃ  ውንጀላ ውስጥ መግባቷ የቀናነቷን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚጥል ሆኖ አግኝቼዋለሁ።

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top