Connect with us

የካፍ መስፈርትን ማሟላት የተሳነው ዘመናዊ ስታዲየም

የካፍ መስፈርትን ማሟላት የተሳነው ዘመናዊ ስታዲየም
አብመድ

ነፃ ሃሳብ

የካፍ መስፈርትን ማሟላት የተሳነው ዘመናዊ ስታዲየም

የካፍ መስፈርትን ማሟላት የተሳነው ዘመናዊ ስታዲየም

የመሀመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲን ስታዲየም አለም አቀፍ ውድድሮችን እንዲያስተናግድ ለማስቻል በወልዲያ ከተማ ደረጃቸውን የጠበቁ ባለኮኮብ ሆቴሎች እንደሚያስፈልጉ ተገልጿል፡፡

ስታዲየሙ ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ሙሉ ወጪ ተገንብቶ ጥር 6/2009 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ከሆነ አራት ዓመት ሞልቶታል፡፡ ዓለም አቀፍ መስፈርቶችን አሟልቶ የተገነባም ሲሆን በምሽት የሚደረጉ ውድድሮችንም ማስተናገድ ይችላል፡፡

ከ95 እስከ 100 በመቶ በሀገር በቀል እውቀትና ቁሳቁስ የተገነባው ሁለገብ ማዘውተሪያው ከጥር 7/2009 ዓ.ም ጀምሮ የተለያዩ ሀገር አቀፍና ክልል አቀፍ ውድድሮችን አስተናግዷል፡፡

ኢትዮጵያ የካፍን ዝቅተኛ የውድድር ቦታነት መስፈርትን የሚያሟላ ስታዲየም ባጣችበት በዚህ ጊዜ የመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም እፎይታን በፈጠረ ነበር፡፡ የካፍ የስታዲየም ግምገማ ባለሙያዎች በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋባዥነት ስታዲየሙን ተመልክተው፤ ከተማዋን በጎበኙበት ወቅት በቦታው ውድድር ለማስኬድ የሚጎድሉ መሰረተ ልማቶችን በተመለከተ አስተያየት መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን የመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም አለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ የተገነባ ቢሆንም በከተማዋ ደረጃቸውን የጠበቁ ለእንግዶች ማረፊያነት የሚያስፈልጉ ባለአራትና ባለአምስት ኮከብ ሆቴሎች ባለመኖራቸው የካፍ መስፈርቶችን እንዳናሟላ አድርጎናል ይላሉ፡፡ ከአየር መጓጓዣ አንጻር ላልይበላ ላይ አየር ማረፊያ መኖሩን በማንሳትም አዲስ እስከ ወልዲያ የሚገነባው መንገድ ከተጠናቀቀ የካፍ የየብስ ላይ ትራንስፖርት መስፈርትን ማሟላት እንደሚቻልም ጠቁመዋል፡፡

የወልዲያ ከተማ ከንቲባ አቶ መሀመድ ያሲን ደግሞ በካፍ ገምጋሚዎች የተሰጡ ወደ ስድስት የሚደርሱ ጉድለቶችን ለማሟላት ከክልሉ መንግሥትና ከሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ጋር በጥምረት እየሠራን ነው ብለውናል፡፡

አቶ ባህሩ ጥላሁን ‹‹በባሕር ዳርና መቀሌ ብሄራዊ ቡድኖችና ክለቦቻችን ጨዋታዎች ያደረጉትም ስታዲየሞቻችን የካፍ ዝቅተኛውን መስፈርት ሳያሟሉ ነው፤ይባስ ብሎም ምንም አይመጥንም በተባለው የአዲስ አበባ ስታዲየም ለመጫወትም ተገደዋል፡፡ ስለዚህ ስታዲየሙን የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶችና የሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ከፍተኛ አመራሮች ደረጃውን አስጠብቀው ገንብተው ካስረከቡ፤ሌሎች ባለሀብቶች ደግሞ እነርሱም በሚያተርፉበት የሆቴል ኢንቨስትመንት እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርባለሁ›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንና አህጉራዊ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ወደጎረቤት ሀገር ተጉዞ የሜዳ ላይ ጨዋታን የማድረግ ስጋት ውስጥ እንዳሉም ይታወቃል፡፡ ምክንያቱም ካፍ ከከፍተኛ ማስጠንቀቂያዎች ጋር ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ውስጥ እንዲደረጉ እየፈቀደ መሆኑ ይነገራልና፡፡

የመሀመድ ሁሴን አሊ አላሙዲን ስታዲየም ኢትዮጵያ ውስጥ የመጀመሪያው አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ወንበርና ጣሪያ የተገጠመለት እንዲሁም ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ያሟላ ነው፡፡ 4 ዓመት ተኩል በፈጀ የግንባታ ሂደት የተጠናቀቀው ስታዲየሙ 22 ሺህ ተመልካቾችን በወንበር የመያዝ አቅም አለው፡፡ (ምንጭ፡-አብመድ)

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top