Connect with us

የቀይ መስቀል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ እርዳታ ጥሪ 

የቀይ መስቀል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ እርዳታ ጥሪ
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር

ዜና

የቀይ መስቀል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ እርዳታ ጥሪ 

የቀይ መስቀል የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እና መልሶ ማቋቋም የገቢ ማሰባሰቢያ እርዳታ ጥሪ 

ግጭቶች ፣ የጎርፍ መጥለቅለቅ ፣ የአንበጣ መንጋ ፣ ኮቪድ 19 እና ሌሎችም ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች አገራችንን በማወክ ተከታይ ሰብአዊ ቀውስ አስከትለዋል ፡፡ ኢትዮጵያ በቅርቡ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ በአግባቡ ሳትወጣ  ትግራይ ፣ ኦሮሚያ ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ እና ደቡብ ክልሎችን ያዳረሰና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ህይዎት አደጋ ላይ የጣለ ውስጣዊ ግጭትና ብጥብጥ አስተናግዳለች፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች ፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናት ፣ ሴቶች ፣ አዛውንቶች ፣ አካል ጉዳተኞች እና ቁስለኞች የግጭት አካባቢዎችን እና ሌሎች የተፈጥሮ አደጋዎችን በመሸሽ ቤታቸውን ለቀው ለመሰደድ ተገደዋል ፡፡

ሁላችንም እንደምናውቀው የ 2012/13 ዓ.ም የአንበጣ ወረርሽኝ እስከ ጥቅምት አጋማሽ ድረስ በ መቶ ሺዎች የሚቆጠር ሄክታር የሰብል እና የግጦሽ መሬቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ፡፡ ይህም በአማራ፣ በትግራይ ፣ በኦሮሚያ ፣ በድሬዳዋ ፣ በአፋር ፣ በሐረሪና በሶማሌ ክልሎች ሰብዓዊ ድጋፍ የሚፈልጉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግለሰቦችን ለጉዳት አጋልጧል ፡፡ የብሔራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እ.ኤ.አ. በመስከረም 2020 ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው የጎርፍ አደጋም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ጎድቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመላ አገሪቱ ተፈናቅለዋል ፡፡ የኮቪድ -19 ወረርሽኝን አስመልክቶ በኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ ፣ ጤና ፣ ትምህርት እና ፖለቲካዊ ተፅእኖዎችን እያደረሠ ይገኛል ፡፡ በእነዚህ ሁሉ በተወሳሰቡ ተከታታይ የሰብአዊ ቀውሶች ላይ የተጨመረው የቅርብ ጊዜ ግጭት እና ሁከትም የሰብዓዊውን ምላሽ ውስብስብ አድርጎታል፡፡

አደጋዎች ባሉበት እና ሰብዓዊ ቀውስ በሚከሰትበት ቦታ ሁሉ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ሁል ጊዜም ቀድሞ ይገኛል! ስለሆነም በጎ ፈቃደኞቹንና ሠራተኞቹን  በማስተባበር ህይወትን ለማዳን እና ኑሮን ከመጠበቅ አንፃር የተለያዩ ሰብአዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል ፡፡ ማህበሩ በ 2012 የበጀት ዓመት አምቡላንስ እና የመጀመሪያ የአየር አገልግሎቶች ፣ የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎች ድጋፍ ፣ የስነ-ልቦናና ማህበራዊ ድጋፍ ፣ የቅድሚያ ማገገም እና የመልሶ ማቋቋም ድጋፍ ፣ የቤተሰብ ግንኙነቶችን ወደነበረበት መመለስ ፣ የኮቪ -19 ዝግጁነት እና ምላሽ ስራዎችን አከናውኗል፡፡ ባጠቃላይ በ2012 ዓ.ም ማህበሩ ከ 700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ከ 36 ሚሊዮን ለሚበልጡ ግለሰቦች ድጋፍ አድርጓል፡፡ በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ደግሞ በ70 ሚሊዮን ብር ወጪ 138 ሺህ ሰዎችን ደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ላለፉት ሁለት ወራት የተከሰቱትን ግጭቶች ተከትሎ በትግራይ ቤንሻንጉል ጉሙዝ ፣ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እና ኦሮሚያ በ 30 ሚሊዮን ብር ወጪ ከ 200 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የህክምና ፣ ምግብ ፣መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች አቅርቦቶች ፣ የስነ-ልቦና ማህበራዊ እና መልሶ የማቋቋም ቤተሰብ የማገኛኘት አገልግሎቶችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡ ማህበሩ 300 የበጎ ፈቃደኞች እና ሠራተኞችን እንዲሁም 100 አምቡላንሶችን በማሰማራት በቅርቡ በተከሰተው የአንበጣ መንጋ እና ከዚያ በኋላ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑትን ወገኖች ህይወት ለማዳን እና  ኑሯቸውን  መልሶ ለማቋቋም በንቃት ተሳትፏል፡፡ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በታህሳስ 2013 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በምዕራብ ፣ ደቡብ እና መካከለኛው ትግራይ ባካሔደው ወቅታዊ የግጭት እና የኃይል ግምገማ መሠረት በሰሜን ጎንደር ፣ በሰሜን ወሎ፣ በመተከል ዞን ፣ በኮንሶ እና ቤንቺ ሸካ አካባቢዎች አጠቃላይ እና ተጨማሪ ምግብ የሚፈልጉ ከ 2.53 ሚሊዮን በላይ ተጋላጭ ሰዎች አሉ ፡፡ በነዚህ

አካባቢዎች መጠለያ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች፣ መተዳደሪያ እና ቅድመ ማገገም፣ የመጀመሪያ ህክምና እርዳታና እና አምቡላንስ አገልግሎቶች ፣ የስነ-ልቦና ማህበራዊ እና መልሶ ማቋቋም እንዲሁም የቤተሰብ ማገናኘት ድጋፎች፣ በተጨማሪም የጤና ማዕከል ተቋማትን እና የቀይ መስቀል ቅርንጫፎችን ጥገና እና መልሶ መገንባት ያስፈልጋል፡፡ ለነዚህ አካባቢዎች በጠቅላላ የሚገመተው የገንዘብ ፍላጎት ከ 9 ሚሊዮን ብር በላይ ነው ፡፡

ሰብዓዊ ድጋፍ ለምታደርጉ ፡ – በአይነት ድጋፍ ማድረግ ለምትፈልጉ የብሔራዊ ማኅበሩ ዋና ማስሪያ ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ በገንዘብ የሰብአዊነት ድጋፍ ፈንድ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 1 000 000 902 008 ፣ እንዲሁም በኦንላይን ልገሳ ለማድረግ የማህበሩ ሊንክ https://donate.bankofabyssinia.com/dashboard/ercs.php  

ለተጨማሪ መረጃ፡-

ዶ/ር ሰለሞን አሊ – የኮሙኒኬሽን ኃላፊ – +251 911 252428

አቶ መሐመድ ዳዳ – የበጎ ፈቃደኞች አመራርና ቅርንጫፍ ልማት ኃላፊ – +251 911 411719

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top