Connect with us

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ኢትዮጵያ ገባ

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ኢትዮጵያ ገባ
Ethiopian News Agency

ኢኮኖሚ

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ኢትዮጵያ ገባ

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ኢትዮጵያ ገባ

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ኢትዮጵያ ደርሷል።

የዲ.ኤች.ኤልና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽርክና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ኩባንያ ከአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ ጋር በመሆን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የጭነት እቃ ማስተናገጃ ተርሚናል በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የጭነት አገልግሎትን ዛሬ በጋራ አስጀምረዋል።

በጭነት አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ የበላይ ጠባቂ ሃይለማርያም ደሳለኝ፣ የአፍሪካ ህብረት የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ የስራ ክፍል የማህበረሰብ መረጃ ንዑስ ዘርፍ ሃላፊ ሞክታር የድላይና ጥሪ የደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ወደ ስራ በገባበት ዕለት የጭነት አገልግሎት መጀመሩ የዛሬውን ቀን ልዩ እንደሚያደርገው ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በንግድ ቀጠናው የታሸጉ እቃዎችና የተለያዩ ምርቶችን እንደሚያጓጉዝም ተናግረዋል።

በዓመት ከአንድ ሚሊዮን ቶን በላይ የካርጎ ጭነት ስለሚያጓጉዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የጭነት አገልግሎት መልካም የገበያ ዕድል እንደሚፈጥርለት አመልክተዋል።

አየር መንገዱ በአፍሪካ አገራት ጭነቱን በማጓጓዝ ለአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት ስኬታማነት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታልም ብለዋል።

የአየር መንገዱ የካርጎና ሎጂስቲክ አገልግሎት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ፍጹም አባዲ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የሚጓጓዘው የመጀመሪያው የጭነት እቃ ከአፍሪካዊቷ አገር እስዋቲኒ በአየር መንገዱ አማካኝነት ተጓጉዞ ትናንት ኢትዮጵያ መድረሱን ለኢዜአ ገልጸዋል።

አየር መንገዱ በቅርብ ጊዜ ውስጥ የጭነት ዕቃውን ናይጄሪያ፣ ጋና፣ ጊኒ፣ ግብጽና ኒጀር እንደሚያጓጉዝም ተናግረዋል።

በቀጣይ በሌሎች አገራት የታሸጉ እቃዎችን ወደ ሌሎች አገራት እንደሚያጓጉዝ ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕና የጀርመኑ ዓለም አቀፍ የሎጂስቲክ አገልግሎት ዲ.ኤች.ኤል እ.አ.አ በ2018 በተፈራረሙት ስምምነት የዲ.ኤች.ኤልና የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሽርክና የሎጂስቲክስ አገልግሎት ኩባንያ በዚያው ዓመት ማቋቋማቸውን አስታውሰዋል።

በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የጭነት አገልግሎት የአፍሪካ ኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ የኤሌክትሮኒክስ ግብይትና ሽያጭ ስራ እንደሚያከናውን ገልጸዋል።

የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትርና የአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ የበላይ ጠባቂ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የጭነት አገልግሎቱ በአፍሪካ 2063 አጀንዳ ማዕቀፍ የምንፈልጋትን አፍሪካ መፍጠር ለሚለው ራዕይ በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና ለማሳካት አስተዋጽኦው የጎላ ነው ብለዋል።

የጭነት አገልግሎቱ መጀመር የአፍሪካ አገራትን የእርስ በእርስ የንግድ ትስስር ለማሳለጥ ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት አገራት ለነጻ የንግድ ቀጠናው ተፈጻሚነት በቁርጠኝነት ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የአፍሪካ የኤሌክትሮኒክስ ትሬድ ግሩፕ ሶኮኩ /በስዋህሊኛ የጋራ ገበያ/ በሚል ስያሜ ያዘጋጀው የኤሌክትሮኒክስ መገበያያ ዘዴ ዛሬ በይፋ መጀመሩንም አብስረዋል።

ግብይት ዘዴው የአፍሪካ አገራት ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ዘመናዊና በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ ያለው ሚና ወሳኝ ነው ብለዋል።(ኢዜአ)

 

Click to comment

More in ኢኮኖሚ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top