ኔስሌ (Nestle) የኘላስቲክ ብክለትን ለመቋቋም የቆሻሻ አስተዳደር መርሃ ግብር ጀመረ
ኔስሌ ከአካባቢ ዘላቂነት አማካሪው ቲ.ኤስ. ኢንቫዮርመንት ጋር በመተባበር በኢትዮጵያ ውስጥ የፕላስቲክ ቆሻሻ ማስወገጃ መርሃ ግብር አዘጋጅቷል፡፡ የፕሮግራሙ ዓላማ በሚቀጥሉት 12 ወሮች ውስጥ የፕላስቲክ ገለልተኛነትን ማሳካት ነው ፡፡ ይህ ማለት ኔስሌ ከአጋሩ ጋር በመሆን በተሸጡት ምርቶቹ ያለውን ፕላስቲክ በመሰብሰብ ተጨማሪ የፕላስቲክ ፍሰት ወደ ቆሻሻ መጣያ እንዳይገባ አድርጓል ፡፡
በ 2020 ዓ.ም. ማጠቃለያም 40 ቶን የሚገመት የፕላስቲክ ቆሻሻ ተሰብስቦ ፣ ተስተካክሎ እንደገና ጥቅም ላይ እንዲውል ወይም እንዲቃጠል ተደርጓል ፡፡
መርሃግብሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የፕላስቲክ ቆሻሻን የመሰብሰብ ፣ መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል እና ዘላቂ የማስወገድ ስራን ያፋጥናል ፡፡
“ፕላስቲክ ብክነት ዛሬ ዓለም እያጋጠማት ካለው ትልቁ የዘላቂነት ችግር ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው ፡፡ እሱን መታገል የጋራ አመለካከት ይጠይቃል ፡፡ ፕላስቲክን ለመቀነስ ፣ እንደገና ለመጠቀምና ሪሳይክል ለማረግ የተሻሻሉ መፍትሄዎችን ለማግኘት ቁርጠኛ ነን፡፡ እናም ይህ አጋርነት ግባችንን ለማሳካት ይረዳናል“ ሲሉ የኔስሌ የአፍሪካ ቀንድ ክላስተር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ወሰንየለህ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡
አቶ ወሰንየለህ አክለውም “በቲ.ኤስ. ኢንቫዮርንመንት የአካባቢ ጥበቃ ቴክኖሎጂ እና እውቀት ላይ በመደገፍ በቅርብ ጊዜ ይህንን ስራ ከፍ ለማድረግ በማሰብ በአዲስ አበባ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ በማነጣጠር የሙከራ ፕላስቲክ ቆሻሻ መልሶ መሰብሰቢያ ስርዓት እንጀምራለን” ብለዋል ፡፡
የፕላስቲክ ቆሻሻው ተሰብስቦ በየአይነቱ ተመድቦ ከተመዘነ በኋላ እንደገና ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል ፕላስቲክ ሌሎች ፕላስቲክ ምርቶችን ለማምረት ይተገበራል ፤ እንደገና የማይታደስ ፕላስቲክ ቆሻሻ ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ በሆነ ሂደት እነዲወገድ ይደረጋል ፡፡
የኔስሌ ፕላስቲኮች የቆሻሻ አያያዝ ተነሳሽነት በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ ለተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የገቢ ማስገኛ ዕድሎችን ይፈጥራል ፣ ለምሳሌ የአከባቢው ነዋሪ እና ወጣቱ በመሰብሰብ ፣ በመለየት ፣ በመመዘን እና በትራንስፖርት አገልግሎቶች ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡
“እ.ኤ.አ. በኖቬምበር ይሄንን ስራ ከጀመርንበት ጊዜ ጀምሮ በአጭር ጊዜ ውስጥ -አዎንታዊ ተፅእኖ ተመልክተናል ፡፡ በግልጽ ከሚታዩ አካባቢያዊ ጥቅሞች በተጨማሪ ፣ በእሴቱ ሰንሰለት ውስጥ ላሉት ፣ በተለይም ከሁሉም በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ የሆናሉ ፡፡ እ.ኤ.አ. በ 2022 ፕሮጀክቱን ወደ ዘላቂ ሞዴልነት ለመቀየር በጉጉት እንጠብቃለን ብለዋል” የ TS ኢንቫዮርንመንት ጥበቃ ቴክኖሎጂ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሳሙኤል ኃይሉ ፡፡
ኔስሌ በዓለም ትልቁ የምግብ እና የመጠጥ አምራች ኩባንያ እንደመሆኑ መጠን የፕላስቲክ ቆሻሻን ችግር በመቋቋም ረገድ የመሪነት ሚናውን ለመወጣት ቁርጠኛ ነው ፡፡ እ.ኤ.አ በ 2018 ኩባንያው የሚያመርታቸውን ምረቶች ማሸጊያዎችን እ.ኤ.አ 2025 መቶ በመቶ እንደገና ጥቅም ላይ ለማዋል በሚችሉ ጥሬ ዕቃ ብቻ ለማምረት ቃል ገብቷል ፡፡