Connect with us

የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ማን ናቸው?

የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ማን ናቸው?
Photo: Social media

ጥበብና ባህል

የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ማን ናቸው?

የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ማን ናቸው?

ሕልፈተ ሕይወታቸው ዛሬ የተሰማው ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ የመድረክ ፈርጥ፣ የተውኔት ፀሃፊ እና አዘጋጅ እንዲሁም ምሁር ነበሩ፡፡ በሃገር ፍቅር እና በብሄራዊ ቴአትር እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማዕከል /ቤተ ኪነ ጥበባት ወ ትያትር/ በሰራተኝነት እና በኃላፊነት ስርተዋል፡፡ ለረጅም አመታትም በመምህርነት ሙያ አገልግለዋል፡፡ በጥበቡ አለም ከ60 አመታት በላይ ያገለገሉ ሲሆን በእነዚህ አመታትም ከ100 በላይ የጥበብ ስራዎችን ለህዝብ አቅርበዋል፡፡

-የመጀመሪያ ዲግሪያቸውንም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በ1951ዓ.ም አግኝተዋል፡፡

-የሁለተኛ ዲግሪያቸውን ወደ አሜሪካ በመሄድ በቴአትር ጥበባት ተምረዋል፡፡

-በውጪ ተምረው ከመጡ በኋላ በቀድሞው ቀዳማዊ ኃይለስላሴ /የአሁኑ ብሔራዊ ቴአትር/ የመድረክ አስተባባሪ ወይም ስቴጅ ማናጀር ሆነው አገልግለዋል፡፡

– ከ 1973-1975 ዓ.ም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ዋና ስራ አስኪያጅ ሆነው ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል፡፡

-የጋሽ ፀጋዬ ገ/መድህን “የእሾህ አክሊል” ቴአትርን በአዘጋጅነት እና በመሪ ተዋናይነት ሰርተዋል፡፡ከዚህም በተጨማሪ በርከት ያሉ ስራዎች ላይ በተዋናይነት ፣ በደራሲነት እና አዘጋጅነት ተሳትፈዋል፡፡ ለአብነትም ፡- 

–    እዮብ – ሀምሌት –  ጴጥሮስ ያቺን ሰዓት   –  የእሾህ አክሊል

–    ኡመር ኻያ  – ፍርዱን ለእናንተ  – የገና ገበያ   – የሺ   – ቴዎድሮስ

–    አሉላ አባነጋ  – አጎቴ ቫኒያ  – ሮሚዮና ዡሌት  – ባለካባ እና ባለዳባ

–    ጠልፎ በኪሴ  – ላቀችና ማሰሮ   –  አባት እና ልጆቹ እና ተሀድሶ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

ጋሽ ተስፋዬ ከተውኔት ፀሀፊነት: አዘጋጅነት እና ተዋናይነት ባሻገር በጋዜጠኝነት ሙያም በኢትዮጵያ ሬዲዮ “በኪነ ጥበባት ጉዞ” እና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “ህብረት ትርኢት” የተሰኙ ፕሮግራሞች ላይ ሰርተዋል፡፡

– “ህልም እና እውነት” የተሰኘ የሬዲዮ ድራማ ድርሰታቸው በ1988ዓ.ም በኢትዮጵያ ሬዲዮ ቀርቧል፡፡

-“አባት እና ልጆቹ” የተሰኘ ድርሰት ባለቤት ነበሩ፡፡

-የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማዕከል/ቤተ ኪነ ጥበባት ወ ትያትር/ በሚመሰረትበት ወቅት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡

-ጋሽ ተስፋዬ ገሠሠ “የመድረክ ተውኔት ነፍሱ ተዋናይ ነው” የሚል እምነትም አላቸው፡፡ በኪነ ጥበቡ ውስጥ ላበረከቱት አስተዋፅኦም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አግኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሚገኘው ባህል ማዕከልም በስማቸው ተሰይሞላቸዋል፡፡

ከ10 በላይ መፅሃፍትን ለአንባቢ አድርሰዋል፡፡ እነሱም ፡-

  1. ዕቃው (ተውኔት) 1961ዓ.ም
  2. መተከዣ (ግጥም እና አጭር ልቦለድ) 1967ዓ.ም
  3. መልክአ ዑመር (አዛማጅ ትርጉም) በ1986ዓ.ም
  4. የወጣቱ ቨርተር ሰቀቀኖች (ትርጉም) 1997 ዓ.ም
  5. የዑመር ኻያም ታሪካዊ ልቦለድ (አዛማጅ ትርጉም) 1999ዓ.ም
  6. ጥንወት (ልቦለድ) 2000ዓ.ም
  7. ጎህ ሲቀድ (የግጥም መድብል) 2001ዓ.ም
  8. ሽልማቱ (ልቦለድ) 2002ዓ.ም
  9. ይሉኝታ እና ፍቅር (ልቦለድ) 2002ዓ.ም
  10. ረጅም ጉዞ ወደ ነፃነት (ትርጉም) 2009ዓ.ም
  11. የመጨረሽታ መጀመርታ (ልቦለድ) 2010ዓ.ም
  12. አሰብ እና ክበር (አዛማጅ ትርጉም) 2011ዓ.ም
  13. መደበሪያ (ልቦለድ) 2013 ዓ.ም – ይህ መፅሃፍ የ84ኛ አመታቸውን ባከበሩበት ወቅት ለአንባቢያን ያበቁት ነው፡፡

– በአንጋፋው የቲያትር ባለሙያና መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ተዘጋጅቶ ዘወትር ቅዳሜና ረቡዕ በናሁ ቴሌቪዥን የሚቀርብ “ስነ – ስኬት” የተሰኘ ፕሮግራም ነበራቸው፡፡

የቴአትር ምሁር፣ ደራሲና ተርጓሚ ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገሠሠ ለኢትዮጵያ ኪነጥበብ፣ ትምህርት፣ ሚዲያ ዕድገት ዘርፈ-ብዙ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሀገራችን ታላቅ ባለውለታ፣ አንጋፋና ታዋቂ ባለሙያ ነበሩ፡፡(የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቲያትር)

 

Click to comment

More in ጥበብና ባህል

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top