Connect with us

ቤተልሄም ታፈሰ የምታውቀው ኢየሱስ የቅፍርናሆሙን ወይስ የናዝሬቱን ?

ቤተልሄም ታፈሰ የምታውቀው ኢየሱስ የቅፍርናሆሙን ወይስ የናዝሬቱን ?
Photo: ማለዳ ሚዲያ

ነፃ ሃሳብ

ቤተልሄም ታፈሰ የምታውቀው ኢየሱስ የቅፍርናሆሙን ወይስ የናዝሬቱን ?

ቤተልሄም ታፈሰ የምታውቀው ኢየሱስ የቅፍርናሆሙን ወይስ የናዝሬቱን ?

( ኃይሌ ተስፋዬ )

የሰዎችን አመለካከትና ሐሳብ አከብራለሁ። በተለይ አመለካከታቸውን ወደ ህዝብ (Public) አውጥተው ሐሳባቸውን ለሚሸጡ ሰዎች ከበሬታዬ ከፍ ያለ ነው ። ይሁንና ሰዎች የነገሩንን ሐሳቦች ሁሉ ሳናላምጥ የመዋጥ፣ ሳንመረምርም የመጋት ግዴታ የለብንም። ምክንያቱም ሐሳቦች ሲሰነዘሩ፣ ተጨባጭ ማጣቀሻ (concrete reference) እና ኅሊናዊ ሚዛን ኖሯቸው ሳይቀርቡ ሲቀሩ፣ “ወጥ የረገጠ” ከንቱ ድፍረት ከመሆን በዘለለ አቅም አይኖራቸውምና ነው ።

በቀድሞው ”ኤክሶዶስ” ላይ መንፈሳዊ ሰዎችን በማቅረብ፣ ኋላም በኤልቲቪ፥ ፖለቲከኞችን እና የፓርቲ አመራሮችን በመጠየቅ የምትታወቅ አንዲት ደፋር ሴት አለች። እርሷም ቤተልሄም ታፈሰ ትባላለች።

የቤተልሄም ትጋትና ድፍረት  በመልካም መንገድ ለሚወስደው ሁሉ የሚበረታታ ጉዳይ ቢሆንም፥ አንዳንድ ጊዜ ግን በተለይ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ መሠረት የሌላቸው፣ አየር ላይ የሚበኑ ሐሳቦችን እና ሚዛናቸው ቀሊል የሆነ ገለባ አባባሎችን እዚህም፣ እዚያም ስታራግብ እየሰማንም፣ እያየንም ነው።

ቤተልሄም ሰሞኑን በፃፈችው መጽሐፍ ላይ ፥ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማን የጠንቋይ ምንትስ ይመስላል ከማለቷም በዘለለ፥ ትላንት ደግሞ ማለዳ ሚዲያ በተሰኘ የቴሌቪዥን ቃለ መጠይቅ ላይ ቀርባ ፥  ከኢየሱስ ክርስቶስ የተማርኳቸው በጣም በርካታ ጉዳዮች አሉ ካለች በኋላ፤ “ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢሆን ከኦሮሞ ጎን እንደሚሆንና ኦሮሞ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ። ሌላ ሊሆን አይችልም። እርሱ ለተጨቆኑት ነው” ስትል እጅና እግር የሌለው፣ ጥራዝ ነጠቅ፣ የተንሻፈፈ የሥነ መለኮት ሐሳብ አቅርባለች።

በዚህ በቤተልሄም ሐሳብ ላይ ሁለት ጽንፍ የረገጡ ስህተቶች አሉ። የመጀመሪያው የኢየሱስን ባህርይ (ማንነት) ያለመረዳት ድካም ሲሆን፥ ሁለተኛው ደግሞ ኢየሱስ ክርስቶስን በራስ ዕውቀት፣ ማንነትና ስንፍና ገድቦ ወንጌልን ባልተገባ መልኩ ለሰዎች መግለጥ ነው።

በወንጌል እንደተረዳነው ኢየሱስ ዘረኝነትን ያፈርሳል እንጅ፣ ከዘረኝነት ጋር ሕብረት የለውም። ኢየሱስ ኀጢአትን ያፈርሳል እንጅ፣ ከኀጢአት ጋር ሕብረት የለውም። ኢየሱስ ወገንተኝነቱ የአባቱን ፈቃድ መፈጸሙ ላይ ብቻ ነው። የአባቱ ፈቃድም የዘላለም ሕይወት ስትሆን፥ በብዙ ምክንያትም የተለያዩ ሁሉ አንድ ይሆኑ ዘንድ ነው። ዮሃ 17፥ 11

በመጽሐፍም ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ በዘረኝነትና በቁርሾ ምክንያት የተጠላሉ እና የተለያዩ ወገኖች መሀል በፍቅር ገብቶ አንድ ሲያደርግ አይተናል እንጅ በአንዱ ረድፍ ተሰልፎ ሲወግን፣ አሊያም እነርሱን ለመምሰል ሲጨነቅ አላነበብንም። ለምሳሌ ያህል፦ እርሱ በተወለደበት ዘመን፥ በይሁዳና በገሊላ ሕዝቦች መካከል ከፍተኛ መናናቅ ነበር። የመናናቁ እና የመለያየቱ ምክንያት ደግሞ የአጥንት፣ የሃይማኖታዊ እይታና የባሕል ጉዳዮች ነበሩ። ኢየሱስ ግን ያደረገው የማይታለፈውን ድንበር አልፎ ወደ ሰማርያ በመሄድ የጥላቻን ግንብ በፍቅር ማፍረስ ነበር። ይህ ለሳምራውያን መወገኑን አሊያም እነርሱን መምሰሉን ሳይሆን የሚያሳየው ሁለቱን ህዝቦች የሚያገናኘውን፣ የተሰበረውን ድልድይ መጠገኑን ነው። ዮሃ. ምዕ . 4፥ 4

ሥለሆነም ቤተልሄም ወደ ተናገረችው ያልተገባ ቃል ስመለስ ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢሆን ኖሮ ከኦሮሞ ጎን አይሆንም። ኦሮሞም አይሆንም። ሊሆን የሚችለው የሰው ልጅ ነው። በርግጠኝነት መናገር የምንችለው ይሄንኑ ብቻ ነው። ደግሞ እርሱ ሰው ብቻ  ሳይሆን መሢሑ መሆኑንም አንርሳ ። ቤተልሄም ግን “ኢየሱስ ክርስቶስ አሁን በምድር ላይ ቢሆን ከኦሮሞ ጎን እንደሚሆንና ኦሮሞ እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ“ ብላለች። በዚህም አባባሏ ኢየሱስን ከአምላክነት፣ ከጌትነትና ከሰውነት ክብር አውርዳ ብሄርተኛ አድርገዋለች።    

ይሁንና መጽሐፍ እንደሚል የሥነ መለኮት መምህራንም እንዳስተማሩን ፦ ኢየሱስ  የሚለው ስም የትስብእቱ (የሰውነቱ) መጠሪያ ስም ነው። ክርስቶስ  የሚለው ደግሞ የብቸኛ ነጻ አውጭነቱ (የመሢሕነቱ ) ስም ነው። በመሆኑም ሐዋርያት ይህ ነጻ አውጭን ለህዝቡ ይገልጡ ዘንድ “ክርስቶስ” “ማሺያሕ” “የተቀባው” የናዝሬቱ ኢየሱስ መሆኑን ለይተው ተናግረዋል። ይህም በቅፍርናሆም አሊያም በሰማርያ አሊያም በኢየሩሳሌም እና በሌላ ቦታ ያሉ በዚህ ስም የሚጠሩ ሰዎችን እንደማይወክል ይገልጽልናል።

የቅፍርናሆሙም ሆነ የሰማርያው አሊያም የኢየሩሳሌሙ ኢየሱሶች ስም ብቻ ካልሆነ በቀር የናዝሬቱን ኢየሱስ የሚያክል ማንነትም  ሆነ ሥልጣን የላቸውም። በመሆኑም ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ከዘረኝነት፣ ከወገንተኝነት፣ ከብሄርተኝነት የተለየ ሲሆን የመጣበትም ዋና መንፈሳዊ ምስጢር  አንድን ዘር ለመምሰል አሊያም ለመሆን፣ ለአንድ ወገንም ለመወገን አይደለም። ይልቁኑ በኀጢአት የወደቀውን ዓለም ከኀጢአት ባርነት ነጻ ያወጣ ዘንድ ነው እንጅ።

ከዚህ አንጻር እህታችን ምንም እንኳ በሃይማኖት ቤት ኖሬያለሁ ብትለን፣ ለሃይማኖቷም እንደምትቀና ብናይም ቅሉ፥

ቤተልሄም ታፈሰ የምታውቀው ኢየሱስ የቅፍርናሆሙን ወይስ የናዝሬቱን ? ሳያስብለን አልቀረም።

 

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top