Connect with us

ሳምሪ የሰካራሙ የትህነግ አንጃ ቡድን የበኩር ልጅ …

ሳምሪ የሰካራሙ የትህነግ አንጃ ቡድን የበኩር ልጅ
Photo: Social media

ነፃ ሃሳብ

ሳምሪ የሰካራሙ የትህነግ አንጃ ቡድን የበኩር ልጅ …

ከሳምሪ ንጹሃንን ከሸሸጉ የትግራይ ደግ ልቦች ጋር ተባብረን ሳምሪን ከምድራችን እናጠፋዋለን፡፡ ነውሩ ብቻ ለታሪክ ይኖራል፡፡

(ከስናፍቅሽ አዲስ)

ሳምሪ የሰካራሙ የትህነግ አንጃ ቡድን የበኩር ልጅ ነው፡፡ እነሱን የመሳሰሉ ልጆች አፍርተዋል፤ ንጹህ የሚያርድ ሰው በላ ሃይማኖት የለሽ ትውልድ ተክተዋል፡፡

የትግራይ ምድር እንዲህ ባሉ ሰው በላዎች አትገለጽም፡፡ እነኚህ የእኒያ ማምከን፣ ማኮላሸት፣ ዘር ማጥፋት፣ ቤተ ክርስቲያን ማሳደድ፣ ኢስላም ሰላም እንዳያገኝ ማድረግ ስራቸው የሆነ የዘራፊዎች ልጆች ተግባር ነው፡፡

ዓለም ስለ ትህነግ መሪዎች በቂ ግንዛቤ ጨብጧል፡፡ ሰው የሚያርድ በካናቢስ የደነዘዘ የምድራች ጭራቅ ስብስብ መሆኑን በተጨበጠ ማስረጃ አረጋግጧል፡፡ ጁንታውና ትግራይ ምንም አያገናኛቸው፡፡ ይሄንን ከሳምሪ ነፍስ ለማዳን ጉያቸው የሸሸጉ ደግ ልቦች አጋልጠው የሰብእናቸውን ጫፍና ጫፍ አሳይተውናል፡፡ ቄራቸውን ቀየሩ እንጂ ኢትዮጵያን ሲያርዷት የኖሩት የሳምሪ አባቶች ነበሩ፤ ልጆች ተተክተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ምድር ላይነሱ ይጠፋሉ፡፡

ከሳምሪ ንጹሃንን ለማዳን ጉያቸው ከሸሸጉ ደግ የትግራይ ልቦች ጋር ሆነን በትግራይ ስም ከሚነግዱ እምነትና ሰዋዊነት የለሽ አውሪዎች ትግራይን ነጻ እናደርጋለን፡፡

ሳምሪ ከዚህ በኋላ በጀግኖች ምድር የበቀለ የባንዳ ፍሬ መሆኑ በታሪክ ይተረካል፡፡ አክሱም ጽዮን ደጃፍ የንጹሃንን ደም ይጠጣ የነበር አውሬ መደምሰሱን ልጆቻችን በታሪክ ይማሩታል፡፡

በወለጋም ሆነ በጉራ ፈርዳ በመተከልም ሆነ በቴፒ በኢትዮጵያ የትም ጥግ ደም እየጠጣ ዘርፎ ሀገር ያወደመው ጁንታ ደም እንዳሰከረው ወደ መቃብር ሊወርድ ነው፡፡

እንዲህ ያሉ ሰሞነኛ ጥፋቶቹ የዘለዓለሙና የመቃብር መውረጃው ስንቆቹ ናቸው፡፡ ከዚያ በኋላ እኛ ኢትዮጵያውያን በመካከላችን አንዳች የልዮነት ግንብ አይኖርም፡፡ ደም አፍስሶ የሚነግስ ጠላት ዳግም አይነሳብንም፡፡ እያባላ የሚበላንን ለዘለዓለም እናስወግደዋለን፡፡

ሳምሪ ከዚህ በኋላ ታሪክ የጥቁር ጠባሳ ታሪክ፡፡ ከ97 ምርጫ ጀምሮ ኢንተር ሃሞይ እያለ ደጋግሞ በዜማ ያለማመድን ጁንታ ሰው ማረድና ሰውን በዘር ማጥፋት እንዴት እንደሆነ ያሳየበት የትውልድ ቅብብሎሽ፡፡ ግን መጨረሻው ሆነ፡፡ አባትና ልጅ ጋር አቆመ፡፡ የልጅ ልጅ የሌለው ክፋት መጨረሻው ሆነ፡፡ ሳምሪ ያልሰመረ ክፉ ሀሳብ፡፡

 

Click to comment

More in ነፃ ሃሳብ

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top