Connect with us

ግዳጅ ላይ እያሉ በህወሓት ጥቃት የተፈጸመባቸዉ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ከተማ ገቡ

ግዳጅ ላይ እያሉ በህወሓት ጥቃት የተፈጸመባቸዉ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ከተማ ገቡ
Photo: Social media

ዜና

ግዳጅ ላይ እያሉ በህወሓት ጥቃት የተፈጸመባቸዉ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ከተማ ገቡ

ግዳጅ ላይ እያሉ በህወሓት ጥቃት የተፈጸመባቸዉ 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ደባርቅ ከተማ ገቡ

 

ስግብግቡ ጁንታ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል መቀሌ ላይ ከሚገኘዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት እና በጠገዴ አርማጭሆ በኩል ደግሞ በአማራ ልዩ ሀይል አባላትና ገበሬዎች ላይ የወረራ ሙከራ እንዲሁም በተከዜ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ ጥበቃ ላይ በነበሩ የፌደራል ፖሊሰ አባላት ጥቃት መሰንዘሩ ይታወሳል፡፡

ከጥቃቱ የተረፉት 11 የፌደራል ፖሊስ አባላት ዛሬ ህዳር 01/2013 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን መቀመጫ ደባርቅ ከተማ ገብተዋል፡፡ ጥቃቱ እንዴት እንደተፈጸመ የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች አናግሯቸዋል፡፡ ካነጋገራቸዉ የፖሊስ አባላት መካከል ዋና ሳጅን ወልደሰንበት ካፊሶ እንዲህ ይላል፡፡

የፌደራል ፖሊስ የየትኛዉም ፓርቲ አባልና ደጋፊ አይደለም፡፡ ህግና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን የሚያስከብር የብሄር ብሄረሰቦች ስብስብ ነዉ፡፡ እኛ የተለመደዉን መደበኛ ስራችን እያከናወን ነበር፡፡ በፕሮጀክቱ እስከ 30 የሚደርሱ የፈደራል ፖሊስ አባላት አሉ፡፡ ሃላፊዉ የትግራይ ተወላጅ ተወልደ ግደይ ይባላል፡፡ ጥቃቱ ከመፈጸሙ ከ3 ቀናት በፊት የፌደራል ዋናዉ መስሪያ ቤት ሳያዉቀዉ ሃላፊዉ መቀሌ ሄዶ ለ3 ቀናት በቆየዉ ስብሰባ ተካፍሎ መጥቷል፡፡ መብራትና ኔት ወርክ በወቅቱ አልነበረም፡፡ 

ይሁን እንጅ ምንም ይፈጠራል ብለን ባላሰብነዉና ባልጠበቅነዉ ሁኔታ ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም 4፡15 ከ250 እስከ 300 የሚሆኑ የትግራይ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት በብሬንና በዲሽቃ የታገዘ ተኩስ ከፈቱብን፡፡ እኛም የመከላከል ሙከራ አድርገናል፤ የተጎዱ አባላቶቻችንም ለማውጣት ብንሞክርም አልቻልንም፡፡ ራሳችንን ለማትረፍ ተታኩሰን አምልጠናል ብለዋል፡፡

ሌላኛዉ ያነጋግርነዉ አባል ኮንስታብል ኪዳነማርያም ጥጋቡ አብረዉን የነበሩት የትግራይ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላትና አመራሮች መቼ ጥቃት መፈጸም እንዳለባቸዉ፣ በየት በኩል መግባት እንደሚችሉ፣ ምሽጋችንና የመሳሪያ ክፍሉን ቀድመዉ መረጃ ስላደረሷቸዉ ባላሰብነዉና ባልጠበቅነዉ ሁኔታ አብረዉን ሲኖሩና አብረዉን ሲበሉ በነበሩ አባላት ክህደት ተፈጽሞብናል፡፡

ምንም እንኳ በጓደኞቻችን ጥቃት ቢፈጸምብንም፤ ከጠለምት እስከ ደባርቅ ባለዉ የአማራ ህዝብ የተደረገልን አቀባበል ድጋፍና እንክብካቤ ችግሩን አስረስቶናል፡፡ በዚህም ለእኛ ለአባላቶቹ ያልሆነዉ የህወሃት ቡድን በምንም ሁኔታ ለትግራይ ህዝብ ሊሆን አይችልም፡፡

የህወሃት ስብስብ የሰዉ ሳይሆን የጭራቅ ስብስብ ነዉ፡፡ የትግራይ ህዝብም ይህን አረመኔ ቡድን ቀሚስ ሆኖ ሊሸሽገዉ አይገባም፡፡በዚህ አጋጣሚ ከፌደራል መንግስት ጎን ተሰልፎ ከህወሃት ቀንበር መላቀቅ አለበት ብለዋል፡፡(የሰሜን ጎንደር ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top