Connect with us

የህወሓት ቅጥረኞች እየተያዙ ነው

የህወሓት ቅጥረኞች እየተያዙ ነው
Fana Broadcasting Corporate S.C

ዜና

የህወሓት ቅጥረኞች እየተያዙ ነው

የህወሓት ቅጥረኞች እየተያዙ ነው

 

ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን በከተሞች ጥቃት እንዲፈፅሙ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው በሰጡት መግለጫ ፅንፈኛው የህወሓት ቡድን አዲስ አበባን ጨምሮ በአገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ጥቃት ለማድረስ ያሰማራቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር እየዋሉ ያሉት በህብረተሰቡ ትብብርና ጥቆማ እንዲሁም በፀጥታ ሃይሉ ጠንካራ ክትትል መሆኑንም ገልጸዋል።

የህወሓትን እኩይ ተግባር ለማክሸፍ በቀጣይም የተጀመረው ጠንካራ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኮሚሽነር ጀነራል እንደሻው ጣሰው አክለውም፥ እብሪተኛው ቡድን ለተቋማት ጥበቃ ያደርግ በነበረው የፈዴራል ፖሊስ ላይ ጥቃት ሰንዝሮ እንደነበረም ገልፀዋል።

ሆኖም ግን በትግራይ ህዝብ እና በፀጠታ አካሉ ቅንጅት በቁጠጥር ስር ውሏልም ብለዋል።

ቡድኑ ጥቃት ከመፈጸሙም በተጨማሪ በጥበቃ ስር በነበሩ ተቋማት ላይ ዘረፋ መፈጸሙን እና ይህም እጅግ አሳፋሪ ተግባር መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።(FBC)

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top