Connect with us

ትህነግ ጦርነቱን የከፈተችው በአማራ ላይም ነው፤

ትህነግ ጦርነቱን የከፈተችው በአማራ ላይም ነው፤
Photo: Social media

ዜና

ትህነግ ጦርነቱን የከፈተችው በአማራ ላይም ነው፤

ትህነግ ጦርነቱን የከፈተችው በአማራ ላይም ነው፤

ትናንት ለአማራ መስዋዕትነት የከፈሉ ዛሬ ከትህነግ አንዋጋ ብለው ቢቀሰቅሱ ባለ ጥሪቷ ትህነግ በገንዘብ ገዝታቸው ነው፡፡

ስማቸው ዋጋው ከጎንደር

ትህነግ ምክንያት ፈልጋ መሬት ወራሪ አማራን አጥቂ ናት፡፡ አሁንም የጦርነቱን ቀጠናዎች በዘረፈቻቸው የቀድሞ መሬት አጎራባች አካባቢዎች ማድረግ ፈልጋለች፡፡ ዛሬም አማራን በመግደል ማዕከላዊ መንግስትን የመጉዳት ድራማ ትተውናለች፡፡

አማራ ሳይሞት የትህነግ መሪዎች ያሰቡትን ማሳካት አይችሉም፡፡ሶሮቃና ቅራቅር እየተወጋ የአማራ አንቂዎች ነን ባዮች ጦርነቱን ገለልተኛ እንሁንበት ሲሉ ሰማን፡፡ እነዚህ ሰዎች ከዚህ ቀደም ለአማራ ብዙ መስዋዕትነት ከፍለው ሊሆን ይችላል፡፡

በዚህ የመከራ ሰዓት የአማራ ድንበር ዜጎች በሚያልቁበት ጦርነት ዳቦ ቆሎ ለትህነግ ሰራዊት ቁረጡለት ማለት ሲቀራቸው አየን፡፡ ትህነግ እጇ ረጅም ነው፡፡ እነኚህ አክቲቪስቶች መወጋቷን የጠሉት ተገዝተው ካልሆነ በስተቀር በምን ህግ ሶሮቃ ሲደበደብ አድሮ ከመከላከያ ጎን አትቁሙ ይባላል፡፡ በምን ህግስ ቅራቅር መግባት የፈለገ የሽፍታ ቡድንን የኛ ጉዳይ አይደለም ተብሎ ይቀሰቀሳል?

አሁን በአማራ ክልል ጠንካራ እንቅስቃሴና ዝግጅት ይፈልጋል፡፡ ትህነግ ትግራይ አይደለችም፡፡ ለጊዜው ግን አድራሻዋ ትግራይ ነው፡፡ መገንጠል አትችይም ተብላ አይደለም፤ ክልልሽን አትመሪም ተብላ አይደለም፡፡ ጠግባ የገባችበት ጦርነት ነው፡፡

የጦርነቱን በራፍ አማራ ክልል አድርጋው ግን ገለልተኛ እንሁን ማለት አማራን ከሽማግሌዎች ጋር ሆኖ መውጋት ነው፡፡

መከላከያ የተባለው ሠራዊትስ የአማራ ልጅ አይደለም? የኦሮሞ ልጅ አይደለም? የሱማሌ አፋር ደቡብ ጋምቤላ ቤኒሻንጉል ልጅ አይደለም? ይህ ቃታህን መልስ መሳሪያህን ዘቅዝቅ መባል ያለበት ለግለሰብ ጥቅም ወደ ሞት የሚገባው የትህነግ ሰራዊት እንጂ እንዴት የአማራ ህዝብ ሊሆን ይችላል? ደብረ ታቦርም ይወለድ ደባርቅ ለአማራ ታስሮም ይወቅ ተገድሎ በዚህ ቀን አማራን ዝም በል የሚል ግን ከገዳዮ እኩል ነው፡፡

 

Click to comment

More in ዜና

Trending

Advertisement News.et Ad
To Top